>

የሳሙኤል አወቀ ገዳዮች በቁጥጥር ስር ዋሉ!!! (ብርሀኑ ተክለያሬድ)

 የሳሙኤል አወቀ ገዳዮች በቁጥጥር ስር ዋሉ!!!

 

 

ብርሀኑ ተክለያሬድ
 

የንጹህ ሰው ደም ከመቃብር በላይ ይጮሀል!

የሳሙኤል ገዳዮች ሳሙኤል እንዲገደል ትእዛዝ ሰጥቶ ገዳዮቹን የላከው (በፎቶው ላይ የቆመው) አቶ ነጋ እና ከተያዘው ገዳይ ጋር አብሮ በዱላ ደብድቦ የገደለው አቶ ጌታነህ (የተቀመጠው) ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ መጋቢት 3/2012 ተይዘዋል። ገዳዮቹ ማንነታቸው ከታወቀ አንድ አመት አካባቢ ሆኗቸዋል ይሁንና ከነበሩበት የስራ ሀላፊነትና ከወንጀሉ ረቂቅነትና አሰቃቂነት አንፃር ግለሰቦቹን በቁጥጥር ስር ለማዋል ብዙ ልፋትና ጊዜን ወስዷል።ሰማእቱ ሳሙኤል መሞቱን እያወቀ “ከሞትኩም ትግሌን አደራ” እያለ እየፃፈ ነው የተገደለው። ከገዳዮቹ መካከል አንዱ ወዲያው ቢያዝም ዛሬ በቁጥጥር ስር የዋሉት ግብረ አበሮቹ ያኔ የዞኑ ደህንነት ፅ/ቤት የሀላፊነት ቦታ ላይ ነበሩና በህዝብ ርብርብ የተያዘውን ገዳይ “ነገሩን ካልገለፅክ እናስፈታሀለን” በማለት ግድያውን  የፈፀመው በግል ፀብና በሳሙኤል ጥፋት እንደሆነ እንዲናገር አድርገው ከግድያው በላይ ለሰማእቱ ክፉ ስም በመስጠት ነገሩን አለፉ።
የንፁህ ሰው ደም ፈሶ አይቀርምና ነገሩ ከተፈፀመ ከ5 አመት በኋላ እውነት መቃብር ፈንቅላ ወጥታ ሊያዙ ችለዋል። በዚህ ሂደት ውስጥ ሳሙኤል እንዳይረሳ ሌት ተቀን ባለስልጣናቱን ስትወተውትና ገዳዮቹ እስከሚያዙ ድረስ ሌት ተቀን የህግ ሰዎች እንቅልፍ አጥተው እውነቱን እንዲያወጡ የሰራችው ዝናሽ ጫኔ የተባለች የሳሙኤል ቤተሰብ የአንበሳውን ድርሻ ትወስዳለች።
“ከብአዴን መረጃ አገኘን” የሚሉ ሰዎች የሳሙኤል ገዳይ ነው ብለው ስም ለጥፈው በየሚዲያው ያብጠለጠሉት ደረጄ አላምረው ፍረጃውን ሁሉ ተቋቁሞ እውነቱን ለማውጣት ከባልደረቦቹ ጋር ያደረገው ጉዞ ፈታኝ  ነበር በግድያው ወቅት በቁጥጥር ስር የዋለው ገዳይ እውነቱን እንዲያወጣ ከማሳመን ጀምሮ በስተመጨረሻም ኦፕሬሽኑን መርቶ ተሳክቶለታል።
“የትኛውም አካል ይሁን አሳደን እንይዘዋለን”ብሎ ቃል የገባው ኮሚሽነር አበረ  አዳሙ እውነቱን ለማውጣት የተጓዘው መንገድም ቀላል አልነበረም ተሳክቶለትም አረመኔዎቹን በእጁ አስገብቷል። (በእርግጥም ግለሰቦቹ እስከሚያዙበት ቀን ድረስ የደህንነት አባላት ነበሩ)
የግድያው መሪ አቶ ነጋ በቁጥጥር ስር በዋለበት ወቅት ተናገረው የተባለውን ነገር ስሰማ ምድር ዞሮብኛል።”ሀገር ለማዳን ብዬ በሰራሁት ስራ ዛሬ መጠየቅ አለብኝ?” አለ አሉ። “ሀገር ለማዳን” ብለው ወጣቶችን እንደ ቅጠል ያረገፉ አረመኔዎች ዛሬም ሳይፀፀቱ የቀደመ ግብራቸውን እንደ በጎ ስራ ቆጥረው ይንጎማለላሉ።
ወንጀለኞቹ እንዲያዙ የጣሩትን አካላት ከማመስገን ባሻገር አሁን ፍትህ ወዳዱ ህዝብ አጀንዳውን መረከብ አለበት ነገሩን በየሚዲያው መነጋገሪያ እንዲሆን ከማድረግ ጀምሮ ጉዳዩ በግልፅ ችሎት እንዲታይ ማድረግ በየችሎቱ እየተገኙም የሰማእቱ ደም ፈሶ እንዳልቀረ ማሳየት ይጠበቅበታል የሳሚን የየእለት የግል ማስታወሻ (ዲያሪ) እንደማንበቤ ከእነዚህ ነፍሰ ገዳዮች ምርመራ በኋላ ሌላ የማይጠበቅ ነገር ሊጎለጎል እንደሚችል ይሰማኛል። ለሁሉም እስከ ፍርዱ ፍፃሜ ነቅተን እንከታተል ባይ ነኝ!!!
******
ባንዳ እና ጉጅሌ.
************
እኔስ አምርሬአለሁ ተፍቼ በግሌ:-
ይሞቱ-ዘንድ አሁን ባንዳና ጉጅሌ::
ለምንስ ያድራሉ
ሕዝብ እያለው አቅሙ:-
የምን ዝምታ ነው.
ሲገድሉ እያደሙ::
ትናንት በዘመኑ ፋሺሽት የፈፀመው:-
ባንዳ-ሆኖ ጉጅሌ ዛሬም ያፋፋመው:-
ኢትዮጵያን ለማጥፋት አይደለም ወይ በዘር:-
ለፈረንጆች አድሮ በገንዘብ ሲቀጠር::
በይፋ ተሽጦ ዜጎቿን አዋርዶ.
ኢትዮጵያን ለትውልድ አስቀራት በባዶ::
እናም በዘመናት ልዩነት ያላቸው:-
ጉጅሌም ፋሺሽትም መግደል ነው ሥራቸው::
እኔስ አምርሬአለሁ ተፍቼ በግሌ:-
ይሞቱ-ዘንድ አሁን
ባንዳና ጉጅሌ::
ጣሊያን እያደነ ምሁራን ሲሰቅል:-
ጉጂሌም ስትገፋ በስደት ስትገድል:-
ይኸው መከራዋን ኢትዮጵያ ታያለች:-
እያሰኟት ድሮም “እሷ ያልታደለች::”.
የተመረጠች ናት ኢትዮጵያ ብርክት ነች:-
ግን በጡት ነካሾች ዛሬም ተነክሳለች::
ታሪክን የካዱ አሉ ያልተማሩ:-
ሕዝብ የሚወግራቸው ለጥፋት ያደሩ::
ዛሬም በትዕቢት ከዋልድባ አልፈው:-
ያቡነጴጥሮስን ሐውልቱን አፍርሰው:-
በሰበብ ሊያጠፉት ደግሞ ከጅለዋል:-
“ማን ደፋር ልብ አለው”ብለው ተዛብተዋል::
በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ስንቴ ቀልደዋል?
በሰላም ሥም ስንቱን እያየን ገድለዋል::
እናም ፋሺሽቶቹ እዚያ ሐውልት ሲያሰሩ:-
“ጎሽ!” ሳይሉ አይቀርም እንኳን ሊናገሩ::
ስለዚህ በተግባር ሳያቸው በግሌ:-
ፍጹም አንድ ናቸው.
ባንዳና ጉጅሌ::
ቆየሁ ካመረርኩኝ ተፍቼ በግሌ:-
ከምር እንዲጠፉ
ባንዳና ጉጅሌ::
Filed in: Amharic