የባልደራስ እና የመአህድ ጥምረት ምን ይዞልን ይመጣ ይሆን? ተስፋ ወይስ ስጋት???
አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
እነ እስክንድር ነጋ የፓርቲ ምሥረታ ጠቅላላ ጉባኤያቸውን በመኢአድ ጽ/ቤት ባደረጉ ወቅትና ባልደራስና መኢአድ መቀናጀታቸውን ወይም መጣመራቸውን ባስታወቁ ወቅት በጻፍኳቸው ሁለት ጽሑፎች እነ እስክንድር “ሀገር አቀፍ ፓርቲ ነን!” ከሚሉት የላቀ ሁሉን አቀፍ አቅም ስላላቸው ፓርቲ ሲመሠርቱ ፓርቲውን ሀገር አቀፍ ማድረግ ሲችሉ የአዲስ አበባ ፓርቲ አድርገው ስለመሠረቱትና ለውጥ ለማምጣት ደግሞ የግድ ከሀገር አቀፍ ፓርቲ ጋር መቀናጀት ስለሚኖርባቸው መኢአድ ችግር ያለበት ፓርቲ ቢሆንም አማራጭ የለምና እነ እስክንድር ሳይቸግራቸው ከበጣም መጥፎው መጥፎውን የመምረጥ ግዴታ ውስጥ ስለከተቱን ከመኢአድ ጋር መጣመራቸውን የግድ መቀበል እንዳለብን ገልጨ ትክክለኛ ምርጫ የሚደረግ ከሆነም ብቸኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ ተስፋ ይሄ ቅንጅት እንደሆነ ገልጨ ነበረ፡፡
ለካ እነ እስክንድር “ሀገር አቀፍ ፓርቲ ነን!” የተሻለ አቅምና ዕድል እያላቸው ማድረግ ያልፈለጉት ሆን ብለው ማለትም ደጋፊያቸውን ለማስጠለፍ ኖሯል ለካ፡፡ እድለኞች አይደለንም!!!
ባልደራስ ፓርቲ እንደሚሆን ከተነገረበት ጊዜ ጀምሮ ባልደራስ መኢአድን ጨምሮ ከአብንና ከእነ ልደቱ ጋር ሊጣመሩ እንደሆነ ወሬው ሲወራ እነ እስክንድር በተለይም ከአብንና ከእነልደቱ ጋር ፈጽሞ መቀናጀት ወይም መጣመር እንደማይኖርባቸው አበክረው ከመከሩና ካስጠነቀቁ ወገኖች አንዱ እኔ ነበርኩ፡፡
መኢአድና ባልደራስ እነ ልደቱንና አብንን ትተው ሁለቱ ብቻ ሲቀናጁ የእኛን ማስጠንቀቂያ አዳምጠው ወይም ተቀብለው መስሎኝ ነበር፡፡ ለካ ያልፈለገው አብን እንጅ እነሱ አልነበሩም ያልፈለጉት፡፡ አብንን እስከመጨረሻዋ ሰዓት ጠብቀውት “በምክር ቤት ስላላስወሰንኩ!” በሚል ምክንያት አብን ወደኋላ በማለቱና የምርጫ ቦርድ ያስቀመጠው የጊዜ ገደብ ሊጠናቀቅ በመሆኑ ሁለቱ ብቻ መቀናጀታቸውን ለማወጅ እንደተገደዱ የመኢአድ ሊቀመንበር አቶ ማሙሸት አማረ ለግዮን መጽሔት በሰጠው ቃለመጠየቅ ገልጿል!!!
አብን “በምክር ቤት አላስወሰንኩም!” በሚል ሰበብ ከመኢአድና ከባልደራስ ጋር መቀናጀት ያልፈለገው ደግሞ እስክንድር ከእነ ልደቱ ጋር ቢቀናጅ ከዳያስፖራው የሚያገኘውን ድጋፍ ሙሉለሙሉ ሊያሳጣውና ከባድ ተቃውሞ ሊገጥመው እንደሚችል ስለፈራ “ቅንጅቱን ከእነ ልደቱ ውጭ እናድርገው?” በማለቱና አብን ደግሞ ቅንጅቱ ውስጥ እነ ልደቱም እንዲካተቱ በመፈለጉ በዚህ ባለመግባባታቸው እንደሆነ የደረሰኝ መረጃ ያመላክታል!!!
ቅጥረኛው አብን እነ እስክንድርን በልደቱ ምክንያት ከተለየ በኋላ ግን ከእነ ልደቱ ጋርም መጣመር ሳይፈልግ ቀርቷል፡፡ የዚህ ምክንያት ደግሞ እነ እስክንድር ልደቱን መቀበል ካልፈለጉ አብን ከእነ ልደቱ ጋር እንዳይቀናጅ በብአዴን በመከልከሉ ነው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ እነ እስክንድርና መኢአድ ከጠሉት ወይም ከናቁት ከእነልደቱ ፓርቲ ጋር መቀናጀት ወይም መጣመር ለአብን የፖለቲካ ኪሳራ ስለሚያደርስበትና የብአዴን plan A ካልተሳካ plan B መፈጸም ስላለበት ነው!!!
የብአዴን plan B ደግሞ ፕላን ኤው ማለትም ቅጥረኞቹን ከእነ እስክንድር ጋር በማቀናጀት በሕዝብ ዘንድ ከፍተኛ ድጋፍ ይኖራቸዋል ተብሎ የሚገመተውን የእነእስክንድርን ድምፅ ማግኘት ካልተቻለ ፕላን ቢው ደግሞ እነ እስክንድርን፣ አብንን፣ የእነ ልደቱን ጥምረት እንዳይቀናጁ በማድረግ የሕዝብን ድምፅ በመከፋፈል ብልግና የተሻለ ድምፅ እንዲያገኝ ማስቻል ነው!!! ግልጽ ነው ገብቷቹሃል???
ለምሳሌ በአንድ የምርጫ ጣቢያ ከተሰጡ ድምፆች እነ ባልደራስና መኢአድ 30% ቢያገኙ፣ አብን 20% ቢያገኝ፣ እነልደቱ 10% ቢያገኙ፣ ሌሎች 9% ቢያገኙና፣ ብልግና 31% ቢያገኝ ተቃዋሚዎች በድምሩ ያገኙት 69% ሆኖ እያለ 31% ያገኘው ብልግና አሸናፊ ይሆናል ማለት ነው!!!
እጅግ የሚያሳዝነው ደግሞ የፖለቲካ መሃይሙ አቶ ማሙሸት አማረ በዚሁ ኢንተርቪው ላይ እንደገለጸው ከአብን ጋር ባይቀናጁም አብን ተመራጭ በሚያቀርብበት የምርጫ ጣቢያ ላይ እነሱ ተመራጭ ላለማቅረብ እነሱ ተመራጭ በሚያቀርቡበት የምርጫ ጣቢያ ደግሞ አብን ተመራጭ እንዳያቀርብ ወይም መደራረብ ላለመፍጠር ለመስማማት እንዳሰቡ መግለጹ ነው፡፡ ይሄ ለአገዛዙ ድርብ ድል ወይም ጥቅም እንደሆነ ልብ እያላቹህ ነው??? ምክንያቱም በአብን ተመራጭ ስም የሚቀርቡት የአገዛዙ ተመራጮች ናቸውና ነው!!! የአቶ ማሙሸት አማረን ቅጥረኝነት ልብ እያላቹህ ነው አይደል???
ምን እነ አቶ ማሙሸት ብቻ አሁንማ እራሱ እስክንድርስ ቅጥረኝነቱ ተጋለጠ እኮ!!! ምክንያቱም በርካታ ሰው አብን ለብአዴን የሚሠራ የብአዴን ካድሬዎች ፓርቲ በመሆኑ በማስረጃዎች እያስደገፉ ነግሮትና አስገንዝቦት እያለ ይሄንን ወደጎን በማለት ከቅጥረኛው አብን ጋር መቀናጀት ፈልጎ ከላይ በገለጽኩላቹህ የብአዴን ፕላኖች ምክንያቶች ሳይሳካ ቀርቷልና ነው!!!
በመሆኑም ከዚህ ቀደም የነገርኳቹህ መረጃ ትክክል ነው ማለት ነው፡፡ ይሄ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ይገባቹሃል አይደል??? ከዚህ ቀደም ስለ እነ እስክንድር ምን ነበረ ያልኳቹህ???
“””””…….ነገሩ እንዴት መሰላቹህ ወያኔ/ኢሕአዴግ የፖለቲካ እስረኞችን ለመፍታት እንደወሰነ ከዋና ዋናዎቹ የፖለቲካ እስረኞች ጋር በለውጡ ኃይል ስም ተደራድሮ ነበር፡፡ “የለውጥ ኃይል!” በሚል የገጸባሕርይ ስም የሚተውነው የወያኔ ቅጥረኛ ቡድን ከእነኝህ ዋና ዋና የፖለቲካ እስረኞች ጋር ሲደራደር ወያኔ እንደወደቀና ሥልጣኑን የለውጥ ኃይል እንደተረከበ፡፡ ይሄ የለውጥ ኃይልም ከእነሱ ጋር መሥራት እንደሚፈልግና እንደሚፈታቸው በመንገር ነበር አታሎ የተደራደራቸው!!!
ያለኝ መረጃ የሚያሳየው ሁሉም የተደራደራቸው እስረኞች እንደተስማሙ ነው፡፡ ይሄ መረጃ “ትክክለኛ ነው!” ብየ መቶ በመቶ እንዳልቀበለው ያደረገኝ ብቸኛው ሰው እስክንድር ነጋ ነው፡፡ እስክንድር መጀመሪያ ላይ ለውጥ የሚባለውን ድራማ ያደንቅና ይቀበል ስለነበረ ጠርጥሬው ነበር፡፡ በኋላ ግን እነ ስንታየሁ ቸኮል ባልደራስን ጠነሰሱና ወደ ባልደራስ ከተውት ለውጥ ከሚባለው ድራማ ጋር ሲጣላ “ቆይ እስኪ!” አልኩኝ፡፡ ይሄው እስከአሁንም “ቆይ እስኪ!” እንዳልኩ ነው!!!
መሀል ላይ ግን ባልደራስ ባለፈው መስከረም ላይ ሰላማዊ ሰልፍ የጠራ ጊዜ የአዲስ አበባ ሕዝብ ከትንሽ እስከ ትልቁ በዚሁ ሰልፍ ላይ ለመሳተፍ አሰፍስፎ እየጠበቀና ወጣቱ ቀኑ አልደርስ ብሎት በየመንደሩ እየጨፈረ እየተነቃቃ ውስጥ ውስጡን ተጋግሞ ሰልፉ ሳይታሰብ ከ1997ቱ ሰልፍ የላቀ ቀውጢ ሰልፍ ሊሆን እንደሚችል ተገምቶ ሰዓቱ እየተጠበቀ እያለ ከፍተኛ ሥጋት ላይ የወደቀው አገዛዙ በመጨረሻ ሰዓት ላይ “ሰልፉ ፈቃድ አልተሰጠውም!” ብሎ ኢሕገመንግሥታዊ በሆነ ምክንያት ሰልፉን ሲከለክል እስክንድር ይሄንን ኢሕገመንግሥታዊ ምክንያት በመቀበልና ለኢሕገመንግሥታዊው አሠራር ዕውቅናና አክብሮት ሰጥቶ “ፈቃድ አልተሰጠውም ከተባለ ሕጉን አክብረን ሰልፉን እንሰርዘዋለን!” ብሎ ሰልፉን ሰርዞ አገዛዙን ከጉድ ሲያወጣው “I got you bitch!” ብየው ነበር፡፡ ለማንኛውም የእስክንድርን ጉዳይ በቅርቡ የምናረጋግጥ ይመስለኛል፡፡ የመሠረተውን ፓርቲ ከነ አብንና ከነ ልደቱ ጋር ካጣመረው ላያችን ላይ ሲተውንብን እንደቆየ ያረጋግጥልናልና ያ መረጃ መቶ በመቶ ትክክል እንደሆነ አረጋግጣለሁ!!!
ሌሎቹ የተቀሩት ሁሉ ግን በየጊዜው ከፈጸሟቸው የአገዛዙን ጥቅም የሚያስጠብቁ ሸፍጦችና ክህደቶች መረጃው ትክክለኛ መሆኑን አረጋግጫለሁ፡፡ ለምሳሌም እነ ጄኔራል አሳምነው በተገደሉ ጊዜ እነ አሳምነውን በአገዛዙ ሚዲያ ቀርቦ “ከሀዲዎችንና ፀረ ሕዝብ ናቸው!” ያለው ከሀዲው ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱንና ማሙሸት አማረን መጥቀስ ይቻላል፡፡ አገዛዙ እነ ጄኔራል አሳምነውን በእነ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱና መሰሎቹ ሲሰልል ነው የቆየው፡፡ አገዛዙ እነ አሳምነውን መግደል እንዳለበት የወሰነው ከነ ኮሎኔል ደመቀ በሚያገኘው መረጃ ላይ ተመሥርቶ ነው፡፡ እነ ጄኔራል አሳምነው ኮሎኔል ደመቀን ፈጽሞ ስለማይጠረጥረው የልቡን ማለትም ዓላማውንና እቅዱን ሁሉ ለደመቀ ይነግረው፣ ያማክረውና ያዋየው ነበር!!! ሌሎቹን ከሀዲዎችን ግን ብዙዎቻቹህ ስለማታውቋቸው እተዋቸዋለሁ!!!””””” ነበር ያልኳቹህ፡፡
“የፈሩት ይደርሳል የጠሉት ይወርሳል!” እንደሚባለው ይሄው እንደምታዩት ሆኗል!!! እጅግ ያሳዝናል!!! እንዲያው ግን ለመሆኑ ይሄ ወያኔ የሚባል የጥፋት ኃይል ከሰው የተወለዱ የሰው ፍጥረቶች ናቸው??? እኔ ፈጽሞ አላምንም!!! የአጋንንት ሽንቶች መሆናቸውን ነው የማምነው!!! አጋንንት ከሰው እንደሚወልድ ታውቃላቹህ??? አዎ ከሰው ይወልዳሉ፡፡ ወያኔ/ኢሕአዴግ ውስጥ ያሉ ሁሉ የአጋንንት ልጆች ናቸው!!! እንደ ጦጣ ተጫወቱብን እኮ!!! እንደምንም ብለው የኢትዮጵያ ሕዝብ አማራጭ እንዳይኖረው አደረጉት!!!
ቆይ ግን እኛስ ለምን በወያኔ/ኢሕአዴግ ላይ አሲረን አናበሽቀውም??? ምን እናድርግ መሰላቹህ ይሄ የመኢአድና የባልደራስ ቅንጅት አመራሮች ከዚህም በኋላ እንደ አቶ ማሙሸት ሁሉ ቅጥረኝነታቸውን የሚያሳይና ለጆሮ የማይጥሙ ነገሮችን በተለያዩ መድረኮችና በምርጫ ክርክር ላይም ጭምር ሲናገሩ ልትሰሙ ትችላላቹህ፡፡ ይሄንን በሚያደርጉበት ጊዜ ታገሱ አትበሳጩ፡፡ ምርጫው ሲደርስም ይሄንን የባልደራስንና የመኢአድን ቅንጅት ምረጡ!!!
ለምን መሰላቹህ “ልንመርጠው የምንችለው ፓርቲ የለም!” ብለን ተስፋ ቆርጠን እራሳችንን ከምርጫው ብናቅብ ተጠቃሚ የሚሆነው አገዛዙ ስለሚሆን ነው፡፡ ምክንያቱም እኛ ሳንመርጥ ስንቀር የአገዛዙ ደጋፊዎች ብቻ ስለሚመርጡ አገዛዙ አንዳችም ማጭበርበር ሳያስፈልገው መቶ በመቶ ድምፅ እያገኘ እንዲያልፍ ያስችለዋልና ነው!!! ይሄ ደግሞ ለሸፍጠኛው አገዛዝ ታላቅ ድል ነው፡፡
ይሄ ከሚሆን የመኢአድንና የባልደራስን ቅንጅት በመምረጥና በከፍተኛ ድምፅ እንዲያሸንፉ በማስቻል አጥንቱን በእነ እስክንድርና በአገዛዙ መሀል ጥለን እንዲባሉ በማድረግ ወያኔ/ኢሕዴግን መበቀል፣ ማብሸቅ፣ ማብገን፣ እንዲከዱትም ማማለል እንችላለን!!! ይሄ ሴራችን ሊሠራ የሚችለው ግን ቅጥረኛው አቶ ማሙሸት “በምርጫ ጣቢያዎች ከአብን ጋር ላለመደራረብ እንነጋገራለን!” ያለውን ነገር ማስቀረት ከተቻለ ብቻነው!!! “የአገዛዙ ቅጥረኞች ካልሆናቹህ ይሄንን ባለማድረግ አረጋግጡ!” እያላቹህ አግባቧቸው ወይም አስገድዷቸው!!!
ምርጫው ነጻ ፍትሐዊና ተአማኒ እንደማይሆን በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል፡፡ እንዲህም ሆኖ ማድረግ ያለብን ይሄንን ነው፡፡ ለምን መሰላቹህ አገዛዙ ምርጫውን እንዲያጭበረብር በማስገደድ ለማስፎረሽ ነው!!! አገዛዙ ቅጥረኞቹ ከሚያልፉለት ይልቅ ቀጥተኛ የሱ ተመራጮች ቢያልፉለት ይመርጣልና!!! እነኝህ በተቃዋሚ ስም የሚቀርቡት ሙሉ ለሙሉ ለአገዛዙ ጭልጥ ብለው ያደሩ ከሆኑ ግን አገዛዙ ቢያጭበረብርም “አላጭበረበረም!” ብለው ስለሚመሰክሩና የእነሱ ሚና ተቃዋሚ መስለው መተወን ብቻ ስለሚሆን ሴራችን አይሳካልንም!!!
ለማንኛውም መልካም ዕድል እንግዲህ ዕድለ ቢሱ የኢትዮጵያ ሕዝብ!!! በምርጫ ይሄንን አገዛዝ ፈጽሞ ማስወገድ ወይም መለወጥ እንደማትችል ከዓመታት በፊት ጀምሬ ደጋግሜ ብነግርህም ልትሰማ አልቻልክም!!! ለውጥ እያልክ ስትጃጃል ከረምክ ለውጡ ውሸትና ማዘናጊያ መሆኑን አየህ፡፡ የቀረህ ነገር ካለ ከመጭው ምርጫ መጭበርበር ሙሉ ለሙሉ ታረጋግጣለህ፡፡ ያኔ ይሄንን አገዛዝ ፈጽሞ በምርጫ መጣል መለወጥ ወይም ማስወገድ እንደማይቻል ለመጨረሻ ጊዜ ታረጋግጣለህ!!! ከዚያ የግድህን ዓምፀህ አገዛዙን በዓመፅ ለማስወገድ ትነሣለህ!!!