>
5:16 pm - Tuesday May 24, 9431

አዲስ_አበባ ~ የተፈተነች ውብ ሐምራዊ ምድር!!! (ኤልያስ የኔሁን ገዳሙ)

አዲስ አበባ  የተፈተነች ውብ ሐምራዊ ምድር!!!

ከኤልያስ የኔሁን ገዳሙ
* ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ የመላው ኢትዮጵያዊ ሰብሳቢ ነገር ግን በተረኛ ነን ባዮች የተፈተነችው ሐምራዊዋ ምድር አዲስ አበባ (ሸገር) መዳኛ ፓርቲ ነው!!!
-~•<<•>>•~-
የአሁኑ ባልደራስ ፓርቲ ከጅምሩ የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክር ቤት ሆኖ በአዲስ አበቤው ዘንድ  እንዲቋቋም ተደርጎ የአዲስ አበቤውን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማሕበራዊ እናም ዘርፈ ብዙ ተያያዥ የሆኑ አዲስ አበቤያዊ ልዩ ውቅር/ጠንካራና ውብ ሐምራዊ ሕብር መሠረት ያለው ሁለንተናዊ ሕዝባዊ የማንነት ህልውናውን ይመክትና ያስጠብቅ ዘንድ የተሰጠውን ሕዝባዊ የሆነ ታሪካዊ ኃላፊነትን ከመወጣት አንፃር ከእኩይ የተረኝነት የመነጨውን እናም አዲስ አበባ ላይ እየተካሄደ የቆየውንና የሚገኘውን የኦነጋውዊያን የልዩ ጥቅም ጋር የተያያዘ አጉል የመብት ጥያቄ ሕገ ወጥ ወረራ ባልደራስ ድምፁን ሲያሰማ ሲቃወም ቆይቷል።
በተመሳሳይ ሁኔታ ባልደራስ በአዲስ አበቤውና መሠል ኢትዮጵያዊያን በሚቀርብለት ጥያቄ መሠረት ብሎም ዘርፈ ብዙ ሕዝባዊ የውጭና የሀገር ውስጥ ነዋሪ ኢትዮጵያዊያ የድምፅና የገንዘብ ወዘተ. ድጋፍ ታጅቦ ከባላደራ ምክር ቤትነት ወደ ፖለቲካዊ ፓርቲነት እራሱን ማሸጋገሩ ችሏል። አዎ! የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክር ቤት ወደ ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ (Balderas for True Democracy (BTD) Party) በሚል ስያሜ ተቋቁሟል። ባልደራስ ለአዲስ አበቤው የለውጥ ተስፋ በአንፃሩም በፅንፈኛ ብሔር ተኮር እኩይ የተረኝነት ባዶ ስሜት ውስጥ የልዩ ጥቅምና መብት በሚባለውን ፀረ-አዲስ አበቤ የጥፋት ተልዕኳቸውን እናት አዲስ አበባ ላይ ተፈፃሚ ለማድረግ ላለመው ፅንፈኛ አክራሪ የኦነጋዊያንን ቡድንን ኢ-አመክንዮዊ አካሄድን የሚያመክን ሠላማዊ ታጋይ የፖለቲካዊ የለውጥ ኃይል ሆኖ መምጣቱ ለኦነጋዊያኑ እራስምታት ሆኗል። ባልደራስ ከጅምሩ ጀምሮ በነበረው እንቅስቃሴ አግላዩን የተረኝነት ስሜት እራቁቱን አስቀርቶታል። የተረኛ ነን ባዮች የለየላቸው አግላይ ዘረኛ ኦነጋዊያን አሽከር የሆኑ እንደኢዜማ አይነቶቹን ከሀዲ አስመሳይ (ወይም ሀሰተኛ) የአንድነት ኃይል ነን ባይ ራዕይ የለሽ የገዢው መንግስት አፓርታይድ ስርዓት ተለጣፊና አለቅላቂ ማንነትንም እንዲሁ እራቁቱን አስቀርቶ ገሃድ እንዲዎጣ አድርጎታል። ባልደራስ የተረኛ ነን ባዮች ብሎም የተለጣፊዎቻቸው ገመናን ያጋለጠ የእውነት ራስ ነው።
ስለሆነም ባልደራስ በለየላቸውና አስመሳይ ፅንፈኛ ኦነጋዊያን ፖለቲከኞች የበላይነት እየተመራ የሚገኘው የሀገራችን ማዕከላዊ/የፌዴራል መንግስት እና ኢዜማ ፓርቲና መሠል ኩሊ አጋሮቹ ዘንድ ቀላል የማይባል ድርጅታዊ ሥም የማጥፋት ዘመቻን እየተመለከትንና እየሠማን እንገኛለን። በተያያዘ አነጋገር ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመወዳደር የሚያስችለውን ድርጅታዊ ቅንጅት ከመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ጋር መፍጠሩን ተከትሎ የተለያዩ ተራ የማደናገሪያ ውጅንብር እየፈጠሩ ይገኛሉ። አዲስ አበባን ለመታደግ ባለው ሕዝባዊ በአደራ የታጀበ ተልዕኮውን ባልደራስ በአዲስ አበባ 23 ወረዳዎች በምርጫ ቢያሸንፍ በሌሎች ክልሎች በተጨማሪ የሚያገኘው ድምፅ በመንግስት የሕዝብ ተወካዮች ውስጥ የተሻለ አቅም ይፈጥርለታል። በተመሳሳይ ሁኔታ አዲስ አበባ ላይ የሚያገኘውን የምርጫ ድምፅ በዐማራ ክልል፣ በደቡብ፣ ድሬዳዋ፣ ሐረር ወዘተ. ከሚያገኘው ድምፅ ጋር ተደምሮ ሲመጣ ባልደራስ የፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማሕበራዊ ብሎም የተለያዩ ተያያዥ የሆኑ የድርጅታዊ የለውጥ ፖሊሲ አጀንዳዋቹን ማስፈፀም ይችላል። እናም የበልደራስ ሀገር አቀፍ የመሆኑ ውሳኔና እርምጃው ስህተቱ የት ላይ ነው?
ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ የመላው ኢትዮጵያዊያን የአዲስ አበባ ባለቤትነትን፣ የውዷ አቃፊ ውብ ሐምራዊ ምድር እናት ዋና መዲናችን አዲስ አበባ ከአካባቢዎቿ ከሚገኙ ገጠርና የገጠር ከተሞች ጋር በማስተር ፕላን ተሳስራ የእምዬ እናት ሀገራችን አንዷ የሆነች ክልል ክፍለ ሀገርነት የመሆን እናም የአዲስ አበባ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት (አአብክመ) መሆንን እውን በማድረግ የአዲስ አበቤውን (ማለትም የአዲስ አበባ ክልል ነዋሪ የሆኑ የመላው ኢትዮጵያዊያንን ውቅር) ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማሕበራዊ ዘላቂ ህልውናን ለማስጠበቅ የሚያስችል ዘርፈ ብዙ አጀንዳን እውን ያደርጋል።
እኔ አዲስ አበቤነትን ባሰብኩ ጊዜ ሁልግዜ ወደ አዕምሮየ የሚመጣው ቀለም ሐምራዊ ቀለም ነው። አዲስ አበቤነትን ሐምራዊ ሕብር ነው። አዲስ አበቤነት እጅግ ውብ ኢትዮጵያዊ ቀለም ነው። አዲስ አበባ ትንሿ ውብ የኢትዮጵያ መገለጫ ናት። የድርጅቴ ባልደራስ ራዕይ የኔው ራዕይ ነው።  ይኸውም የትንሿ ኢትዮጵያ ውብ ሐምራዊ ሕብር ቀለም የሚታይባት እንቁና አቃፊ የሆነች ክልል ሁና ማየት ነው።  ከታላላቅ ቀደምት የግሪክ ፈላስፋዎች መካከል አንዱ የሆነው አርስቶትል (Aristotle) ሐምራዊ (purple) ቀለምን  የቀለሞች ሁሉ ቀለም (the color of colors) ሲል ይጠራዋል። ሐምራዊ ቀለምን በማስተዋል ለሚያየው ሁሉ በአንድ ሐምራዊ ቀለም ውስጥ ሰማያዊን፣ ቀይን፣ ፒንክን ወዘተ. ቀለሞችን በውስጡ ይመለከታል። ሐምራዊ ውብ ቀለም። አዲስ አበባ (ሸገር/አዱ ገነት) ሐምራዊ ምድር። አዲስ አበባ ውብ ምድር። በሀቀኛ የነፃነት ታጋይ የሠፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ ልጆች የሚመራው ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ  አዲስ አበባን ብሎም ኢትዮጵያን ይታደጋል።
በተያያዘም የጥንቱ ታላቅ ፈላስፋ አርስቶትል የሠው ልጅ  ከሕግ በላይ እራሱን ካየ ከተናካሽ አውሬ የላቀ ከህግና ፍትሕ የተለየ የዱር አውሬ እንደሆነ (…at his best, man is the noblest of all animals; separated from law and justice he is the worest…) ከሁለት ሺ አምስት መቶ ዓመታት በፊት አስረግጦ ተናግሮ አልፏል። በአንፃሩም ዛሬ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ላይ የዘመናችን ስርዓት አልበኛው የኦነጋዊያን (የኦህዴድ-ኦነግ) ቡድን በአጠቃላይ የዘመናችን የሠው ልጆችን ንቃተ-ህሊና የማይመጥን አውሬያዊ ሠው በላ ባህሪውን በተግባር አሳይቶናል። ጋጠወጥ ትውልድ ቀርፆና አንፆ የከፋ እኩይ ኢ-ሰብዓዊ የጥፋት ተልዕኮውን ተፈፃሚ አድርጓል። እየፈፀመም ይገኛል። ብዙሃኑ የዱር አውሬዎች ቢያንስ የራሳቸውን ዘር እየተናከሱ አያጠፉም። በአንፃሩ በጥላቻ ናላቸው የዞረው ፅንፈኞቹ ዘረኛ የኦነጋዊያን ሴረኛ ሠዎች በቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ ውስጥ ቄሮ የኦሮሞ ወጣትን በመስበክ ንፁሃን የሠው ልጆች (ኢትዮጵያዊያን) ላይ ብሔር ተኮር ዘርፈ ብዙ ወንጀል የሀሰት የጥላቻ ትርክት ባነፁት የቄሮ ኃይል ተፈፃሚ እንዲሆን አድርገዋል። ይሁንና የንፁሃን ዜጎቻችን ደም በከንቱ ፈሶ አይቀርም። የንፁሃን ኢትዮጵያዊያን እንባ በከንቱ ፈሶ አይቀርም። የፍርድ ቀን እጅግ ቅርብ ነው። ለአሁኑ እዚህ ላይ ላብቃ።
ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ  የኢትዮጵያዊያን መሰብሰቢያ የሆነችው ሐምራዊዋ ምድር (የነገዋ ክልል) አዲስ አበባ ብሎም የታላቋ ኢትዮጵያ መዳኛ ነው።
Filed in: Amharic