>

ከሞዛምቢክ ወደ ደቡብ አፍሪካ በኮንቴነት ተጭነው የሚጓዙ 64 ኢትዮጵያውያን ህይወታቸው አለፈ!!! (ክርስቲያን ቲዩብ)

ከሞዛምቢክ ወደ ደቡብ አፍሪካ በኮንቴነት ተጭነው የሚጓዙ 64 ኢትዮጵያውያን ህይወታቸው አለፈ!!!

 
ክርስቲያን ቲዩብ
64 ኢትዮጵያዊያን ከማላዊ ወደ ሞዛቢክ በከባድ ተሽከርካሪ ኮንቴይነር ውስጥ በመጓዝ ላይ ሳሉ ታፍነው መሞታቸው ተገለጸ።
ኢትዮጵያዊያኑ ህይወታቸው ያለፈው ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመግባት በማሰብ ከማላዊ ወደ ሞዛምቢክ በአንድ የእቃ መጫኛ ተሽከርካሪ ውስጥ ተደብቀው ሲጓዙ በተፈጠረ መታፈን መሆኑ ተገልጿል።
በአጠቃላይ 78 ኢትዮጵያያን በተሽከርካሪው ወስጥ ሲጓዙ የነበረ ሲሆን 64ቱ ሲሞቱ 14ቱ በህይወት የተረፉ ሰዎች ከጭነት መኪና ውስጥ ዛሬ ጠዋት ተገኝተዋል፡፡
ኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች መነሻቸውን ያረጉት ከምዕራባዊ ግዛት አከባቢ ነበር ተብሏል፡፡
የኢሚግሬሽን አገልግሎት እንዳለው ስደተኞቹ በጭነት መኪናው ሟቲዝ ከምትባል ከተማ መነሳታቸውን ተናግሯል፡፡
የብሔራዊ ፍልሰት አገልግሎት ቃል አቀባይ ለቢቢሲ አፍሪቃ እንዳሉት እስካሁን ኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች የሞታቸው ምክንያት በትክክል ባይረጋገጥም የአየር እጥረት ሳይሆን እንዳልቀረ ተናግረዋል፡፡
አክለው ሲያስረዱም ሾፌሩ ተሽከርካሪውን እንዲያቁም ቢጠየቅም ለማቆም ፍቃደኛ አለመሆኑን አስረድተዋል ፡፡አንድ የስራ ባልደረባቸው ከመኪናው ጩኸት እንደሰሙ እና ስደተኞች ውስጥ ሊሆኑ ይችላሉ የሚል ስጋት እንዳላቸው ገልጸችላቸው እንደነበር አስታውሰዋል ፡፡ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመጓዝና በዚያ ስራ ለመስራትና ህይወትን ለመለወጥ የሚሹ ሰዎች አከባቢው የታወቀ መተላለፊያ ነው ፡፡
Filed in: Amharic