>

ባድመ ለሻእብያ የሸጠው ስዩም መስፍን ዶ/ር አብይን በአገር ሉአላዊነት ይከሰዋል!!! (ናትናኤል አስመላሽ)

ባድመ ለሻእብያ የሸጠው ስዩም መስፍን ዶ/ር አብይን በአገር ሉአላዊነት ይከሰዋል!!!

 

 

ናትናኤል አስመላሽ
ስዩም መስፍን አገር በመሸጡ አፍሮ ከሚዲያ መደበቅ ሲገባው፣ መቀሌ ተደብቆ በራሱ ሚዲያ ዶ/ር አብይን ይከሰዋል፣ ሲጀመር ጋዜጠኛውም ካድሬ ስለሆነ፣ ስዩም መስፍንን በባድመ ሉአላዊነት ሊጠይቀው አልቻለም ;አይችልምም፣ የዛሬ ሃያ አመት ለዘጠና ሚልዮን ህዝብ ዋሽቶ፣ ህዝብ ያስጨፈረ ስዩም መስፍን፣ ኢትዮጲያውያንን ይቅርታ ሳይጠይቅ ዶ/ር አብይን መክሰሱ፣ የኢትዮጲያን ህዝብ ምን ያህል እንደሚንቀው በድጋሚ አሳይቶናል።
የአልጀርስ ስምምነቱን ሚስጥር የሆነው የኢትዮጲያ ህዝብ፣ ዛሬ ስዩም መስፍን የኢትዮጲያ ህዝብ ስለ አባይ ሊጠይቅ ይገባል ይለናል፣ ዶ/ር አብይ ከግብፆች ጋር ያደረገውን ስምምነት ለህዝብ ይፋ ማድረግ አለበት ይላል፣ ከዛም አልፎ የኢትዮጲያ ህዝብ መጠየቅ አለበት ይላል፣ ትናንት ስልጣን ላይ ቁጭ ብለው፣ የህዝብ የልብ ትርታ ያላዳመጡ የከሰሩ የህወሓት ባለስልጣናት ዛሬ የኢትዮጲያ ህዝብ በአባይ ጉዳይ ላይ፣ጠ/ሚ ዶ/ር አብይን ጠይቆ መልስ እንዲያገኝ እና ካልሆነ ግን ፀረ ዶ/ር አብይ ተሰልፎ ሉአላዊነቱን እንዲያስከብር ጥሪ ያቀርባል፣ ሚስጥሩ ግን የኢትዮጲያ ህዝብ በአባይ ግድብ ሰበብ በዶ/ር አብይ ላይ ተቃውሞውን አስነስቶ ህወሓትን ድጋሚ እንዲያነግስ ነው።
ስዩም መስፍን ሆይ! ህወሓት ወደ ስልጣን ከምትመጣ ይልቅ፣ የኢትዮጲያ ህዝብ፣ አርባ ሚልዮን የኢትዮጲያ ህዝብ በዶ/ር አብይ ቢጨፈጭፍ ይመርጣል። ለኢትዮጲያ ህዝብ አዛኝ መስለህ፣ ኢንጅነር ስመኘው ሓወልት ይሰራለት አልክ፣ የኢትዮጲያን ሉአላዊነት ያስከበሩ በኢትዮጲያ ህዝብ እንደ ጀግና የሚታዩ፣ ለኢትዮጲያ ሉአላዊነት አንገታቸውን የሰጡ የንጉሶች  ንጉስ አፄ የውሃንስ ሃወልት እስካሁን ድረስ ትግራይ ውስጥ ያልተሰራበት ምክን ያት ምን ይሆን? በትግራይ ይቅር እና ሃያ ሰባት አመታት ሙሉ ስልጣን ላይ ተቀምጣቹ በአፍሪቃ መዲና በሆነችው አዲስ አበባ ውስጥ ;  የአፍሪካ ጀነራል ራስ አሉላ አባነጋ ሃወልት ለምን አላሰራቹም? አየህ ባንዳ እና የባንዳ ልጅ ስለሆንክ ኢትዮጲያዊነታቸውን አስቀድመው ለኢትዮጲያ መስዋእት የከፈሉትን ጀግኖቻችን ሃወልት ሳታቆም፣ የኢትዮጲያን ህዝብ አንጀት ለመብላት የኢንጅነር ስመኘው ሃወልት ይሰራ ትላለህ።
ደስ የሚለው ነገር ግን በቁሙ ደንግጦ እንደሞተው አምባገነን አለቃህ፣ ሳትሞት ይህንን ለውጥ ማየትህ ነው።በስልክ በቀጭን ትእዛዝ ቡጁምቡራ አትሄድም ያለህ ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ፣ ለኢትዮጲያ ህዝብ እና ለኢትዮጲያ እናቶች ሲል፣ ባድሜ ውስጥ ደማቸው እና አጥንታቸው ለገበሩ ኢትዮጲያውያን ሲል አንድ ቀን ፍርድቤት ያቀርብህ ይሆናል!!! ጊዜ ደጉ ለታሪክ ዶ/ር አብይ በስልክ እና በሰዎስት መስመር ደብዳቤ እንዳባረራቹ ስለመሰከራቹ ልትመሰገኑ ይገባል። ባንዳ እና የባንዳ ልጅ ግን ሁሌ ያው ነው፣ አይኑን በጨው አጥቦ ዶ/ር አብይን ይከሳል። ባድመ ውስጥ እግራቸው በቦምብ የተቆረጡ፣ በመድፍ አይናቸውን እና እጃቸውን ያጡ፣ በሂወቱ ያሉ የቁርጥ ቀን ልጆች ግን ሲሰሙህ ምን ይሉ ይሆን? እርግጠኛ ነኝ ቢያገኙህ ስጋህን ቆርጥው ለአሞራ ይሰጡት ነበር። ባድመን ሸጠህ ዶ/ር አብይ በሉአላዊነት መክሰስ አይቻልም!!!
Filed in: Amharic