>

"ለምን ጎንደር ብቻ?" (ሀብታሙ አያሌው)

“ለምን ጎንደር ብቻ?”

ሀብታሙ አያሌው
“አቶ ተመስገን ጥሩነህ አማራን ለማዋረድ የተላከ ነው። ይሄ ምስለኔ ከሃላፊነቱ ካልተነሳ፣ በቅርቡ ሌላ መገዳደል እናያለን” 
ህገ ወጥነት በመላው ሀገሪቱ አለ። አማራ ክልልም እንዲሁ። ይሄም መስተካከል አለበት። ጥያቄው ለምን ጎንደር ላይ ብቻ ትኩረት ተደረገ? የሚለው ነው። መልሱን የኦነግ አመራሮች ይነግሩሃል። ወያኔን አንቀጥቅጦ ያስፈረጠጠው አብዮት ጎንደር ላይ ነው የተለኮሰው። ኦነግም የወያኔ የሽንፈት ታሪክ በእሱ ላይ እንዳይደርስ ይሰጋል። በዚህም ጎንደርን ቀጥቅጡልኝ የሚል ትዕዛዝ ለእነ አቶ ተመስገን ጥሩነህ አስተላለፈ። ምስለኔዎቹም ወደ ትግበራ ገቡ።
በቅርቡ 86 ሰዎች ያረደውን ቄሮ የኦሮሞ ባለስልጣናት ስሙን በመጥፎ ያነሱታል ወይ? ሌላው ቀርቶ ተማሪዎችን ያገተውን ኦነግ ሸኔን ስሙን በክፉ የሚያነሳ አንድ የኦሮሞ ባለ ስልጣን አለ ወይ? መልሱ የለም ነው።
ታዲያ የአዴፓ ባለስልጣናት ፋኖን ወንበዴ ለማለት ለምን በቁ? ወንበዴና ህገ ወጥ ቡድን ሌሎች የክልሉ አካባቢዎች ላይ የለም ወይ? እርግጠኛ ነኝ በአማራ ክልል ሌላ መገዳደል ይኖራል። አቶ ተመስገን ጥሩነህ አማራን ለማዋረድ የተላከ ምስለኔ ነው።
አቶ ተመስገን ወደ ክልሉ ከተላከ ወዲህ የሰራውን በሙሉ ተመልከቱ። ውርደት ብቻ ነው ያከናወነው።
Filed in: Amharic