>

ሞኝ በሆነች ሀገር ደጃፍ ላይ የበቀለች ሞፈር ! (ጴጥሮስ አሸናፊ ከበደ)

ሞኝ በሆነች ሀገር ደጃፍ ላይ የበቀለች ሞፈር !

 

ጴጥሮስ አሸናፊ ከበደ
ኮሮና ቫይረስ ….
♦  ለታላቁ እውቀታቸው ምዕራባውያን ሽልማታ የሰጧቸው ፤ ልምድና እውቀታቸውን በሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ….ሄደው ልምዳቸው አካፍለው የተወደሱ ነገር ግን  በሀገር ውስጥ እንደሚነሳ ነቢይ ያልተከበሩ የስነፈለክ ባለሞያ ናቸው። 
   ይቺ እናት ወ/ሮ አበበች ሽፈራው ይባላሉ። ጤና ሚኒስቴር ለኮሮና ቫይረስ ፈዋሽነት የሚሆን መድኃኒት ግኝት ላይ ታላቅ ድርሻን የያዙ ታላቅ እናት ናቸው። ብዙዎች ዓለም የምትመካባቸው የህክምና ተመራማሪዎች እውቀት ሊኖራቸው ይችላል። ይህኝ እናት ግን ከእውቀትም በላይ ከፍ ያለ ጥበብ እንደያዙ ሙሉ እምነት አለኝ። በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ተሰናስኖ በሊቃውንት አባቶች የተሰናዳውን የህክምና ውቅር ገልጣ ያወቀች በሞኝ ዓለም ላይ የተከሰተች ብልህ ሴት ናት።
   እርግጥ ነው ከስማቸው ትይዩ ዶክተር ወይም ፕሮፌሰር የሚል ምድራዊ የሽልማት ወይም የማዕረግ ስሞች ባይኖራቸውም ከዕምነት ጎን ቆመው በእግዚአብሔር የተማመኑ የጥበባቸው መጀመሪያ እግዚአብሔርን በመፍራት የጀመሩ ልዩ እናት ናቸው። የእግር መዳፍ በማዬት፣ የእጅ አሻራ በመመልከት ብቻ በሽታን የሚያውቁ ለታላላቅ ደዌዎች ፍቱን መድኃኒት ይሆን ዘንድ ቅጠል በጥሰው፣ ስራስር ጨቅጭቀው የሚሰጡ ልዩ ሴት ናቸው።
   እኛ ልናመልካቸው የምንሯሯጥላቸው ምዕራባውያን መጥተው የሚያማክሯቸው ሞኝ በሆነች ሐገር የበቀሉ የጥበብ ሞፈር ናቸው ። የህይወት ታሪካቸው እንደሚያመለክተው በዓለም ባንክ ጋባዥነት አሜሪካን ሀገር በሚገኙ ታላላቅ የትምህርት ተቋም በሆኑት በሜሪላንድ እና ሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ሄደው ልምዳቸው አካፍለው የተወደሱ ነገር ግን  በሀገር ውስጥ እንደሚነሳ ነቢይ ያልተከበሩ የስነፈለክ ባለሞያ ናቸው።
   ለታላቁ እውቀታቸው ምዕራባውያን የወርቅ ኒሻን እና  200 ሺህ ዶላር ሽልማት ያቀበሏቸው የእውቀት ግምጃ ቤት ናቸው። ታድያ ዛሬ ላይ የኮሮና ቫይረስ መድኃኒት ለማግኘት በሂደት ላይ ናቸው ሲባል ምን ነው እኛኑ ኮሰኮሰን ? በዳማካሴና በፌጦ ዕድሜ ዘመናችንን ደዌን እየሻርን ኖረን ከጎረመስን በኃላ ዛሬ ላይ የባህል መድኃኒት መድኅን ሊሆነን ነው ሲባል ቁርጥማት ለምን ይሰድብናል?
በታላቁ የኢትኤል ምድር ላይ ተፈጥረን የጉንዳን ታክል ክብር ለእራሳችን ያልሰጠን ሞኝነት የወረሰን ደካማ ትውልድ መሆናችንን አስመስክረናል።
Filed in: Amharic