>

"የአፍሪካውያን ምድር መላው ዓለምን ባንድነት ይመግባል፤ ነገር ግን ችግራቸው አንድና አንድ ነው፤ እርሱም "….. " የሩሲያውያኑ ፕሬዚደንት ቭላድሜር ፑቲን (በሰሎሞን ዳውድ አራጌ፤ጎንደር ዩኒቨርሲቲ)

የአፍሪካውያን ምድር መላ አውሮፓውያንን፣ አሜሪካውያንንና ኤዥያውያንን ባንድነት ይመግባል፤ ነገርግን ችግራቸው አንድና አንድ ነው፤ እርሱም “….. “፡፡

 የሩሲያውያኑ ፕሬዚደንት ቭላድሜር ፑቲን አፍሪካ በምዕራባውያኑ ላይ ያላትን ጥገኝት / ዕምነት መጣል አስመልክቶ የሰነዘሩት ድንቅ መልዕክት

ሰሎሞን ዳውድ አራጌ
ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ፤ እንግሊዝኛ ቋንቋና
ስነፅሁፍ ትም/ት ክፍል መምህር

 

ሪፖርተርስ ፕረስ ኤን. ጅ በተባለ ድረገፅ የወጣውን ይህን ወቅታዊና ለመላው ዓለም በተለይም ለዕኛ በዚህ እነርሱው አምጠው በወለዱት ጭንቅና መከራ መልሰን እነርሱኑ የሙጥኝ ብለን ያድኑን ዘንድ ከእነርሱ ውጭ ላሳር በምንልበት ወቅት ጆሮ ገብ መልዕክት ነው፤

♦ ♦ ♦ ♦

አፍሪካ ራስ-መር ልትሆን ፈፅማ አትችልም፤ አፍሪካዉያኑ ዕምነታቸውን ከራሳቸው ይልቅ በአውሮፓውያኑ፣ አሜሪካውያኑና ቻይናውያን ላይ የተንጠለጠለ ነው፡፡

 ራሳቸው ፍፁም ዕምነት የላቸውም፣ አፍሪካውያን የቴክኖሎጅ ጠበብት /መሃንዲሶች በሰለጠኑባቸው ሙያዎች ላይ ልምድን ያካብቱ ዘንድ መድረኮች አይመቻቹላቸውም፤ በአንፃሩ ቻይናውያኑን መንገዶቻቸውን ይገነቡላቸው ዘንድ ይቀጥሯቸዋል፡፡ 

አፍሪካ ውስጥ አንድ ነጭ ግለሰብ ወንጀል ሊፈፅም ይችላል፤ ይፈፅማልም፤ ነገርግን ምንም ዕርምጃ ሲወሰድበት አይታይም ምክኒያቱም አፍሪካውያን ባለስልጣናት /ሊቀመናብርት/ የወንበር ላይ ሊቆች እኛን (ነጮችን) ከዕውነታው ባፈነገጠ መልኩ የሚስሉን አንደ ከፊል ፈጣሪዎቻቸው አድረገው ነው፡፡ አውሮፓ ውስጥ ጥቁር ሰው ታፍኖ ሊወሰድ እንዲሁም ትንኮሳ ሊደርስበት ይችላል፤ ይባስ ብሎም ይገደላል፤ አንድም አፍሪካዊ መሪ ግን ግድ ሰጥቶት ጠይቆ አያውቅም፡፡ አፍካውያን ለራሳቸው የሚሰጡት ምስል በተለይም ከአውሮፓውያንና አሜሪካውያን ዘንድ አንዳች የውል ስምምነትን በሚያደርጉበት ግዜ እንደ አንድ ተስፋ ቢስና ደካማ ፍጡር ነው፡፡ 

ራሳቸው የራሳቸው ባላንጣዎች ናቸው፡፡ ዕርስ በርስ አይዋደዱም፤ ይህም ለቅኝ ገዥ ጌቶቻቸው የሃብት ብዝባና ምዝበራ መቀጠል በር ከፋች ነው፡፡ 

እኔ እስካማውቀው ድረስ አፍሪካ በፈጣሪ ዘንድ የተመረጠች ብሎም የተባረከች አሕጉር ነች፤ እናም ለአፍሪካውያን መላው አውሮፓውያን፣ አሜሪካውያንና ቻይናውያን የሚቋምጡባት፣ እነርሱን በሆን ሲሉ የሚጎመዡባት ሁናቴ ላይ መሆናቸው የሚገነዘቡበት ግዜው አሁን ነው፡፡ የአፍሪካውያንን የአየር ፀባይ ከሌላው ዘንድ አታወዳድረውም፤ የአፍሪካውያ ምድር መላ አውሮፓውያንን፣ አሜሪካውያንንና ኤዥያውያንን ባንድነት ይመግባል፤ ነገርግን ችግራቸው አንድና አንድ ነው፤ እርሱም “መሪዎቻቸው“፡፡ ጉዳዩ እንደሚያስጨንቀው አንድ ሰው የምንግዜም ምርጡ መሪያቸው ጋዳፊ ነበር፡፡  

♦ ♦ ♦ ♦

 እንደ አንድ ዕጣ ፋንታዋ አንደሚያሳስበው፤ ለውጧን በእጅጉ እንደሚናፍቅ አፍቃሬ አፍሪካ ወይም አፍሪቃዊ ይሕ ጦማር ቧልት፣ ፌዝ ወይም መናኛ ወሬ አይደለም ነገርግን የማህበረሰባችን ከነጭ ውጭ ወደ ውጭ የሚል ያልተገባ ዕሳቤ የሚገራ ምክር ነው፤ (በቅርቡ አንኳን በባሕል ሕክምናችን ላይ የተሰነዘረው መዘባበት ገና ከአዕምሮአችን ስላልጠፋ እርሱን በሕሊናችን ሰንቀን እነርሱ አንዲት ብልቃጥ ወርውረው ለወረርሽኙ ክትባቱ ተገኘ ብለው ቢሰጡን ዕለቱን የምንሽር የሚመስለንን ቤቱ ይቁጠረን) እና ፈጣሪ ባስቀመጠን ሁኔታ /እንደፈጠረን/ እንዳንጠብቀው እንለወጥ ዘንድ፤ ሰልጥነንም የተሰጠንን ምልዑ አሕጉር ሃብቷን እንጠቀም ዘንድ ለእኛ የተላለፈ ብርቱ መልዕክት ነው፡፡

♦ ♦ ♦ ♦

ምንጭ፡ Reporters press NG at http://reporterspressng.com

Filed in: Amharic