>
5:13 pm - Saturday April 18, 2668

ኮረናና ፖለቲካ - አብይና መደመር ጋብቻ ፈፅመዋል?! (ካሳሁን ለማ)

ኮረናና ፖለቲካ – አብይና መደመር ጋብቻ ፈፅመዋል?!

 

ካሳሁን ለማ
የኮረና ቫይረስ የቻይናን “ዊሃን” ትንሽዬ ከተማ መነሻውን አድርጎ መላው ዓለምን እያዳረሰው ወይም እየጎበኘው ይገኛል::ጉብኝቱ በጥሪ ሳይሆን በኮረና በራሱ ተነሳሽነትና ገፋፊነት ነው::ስለዚህ ሁሉም ሰው ሳይወድ በግድ ሊጨብጠው የግድ ነው::
ጀርሙ በአይን የማይታይ በመሆኑ በማንኛውም ሰዓት ፊታችን ላይና እጃችን ላይ አጋጣሚው በተመቻቸለት  ቅፅበት ይጎበኘናል::
ዛሬ ቫይረሱ የሁሉንም ቤት እንኳኩቷል::
የጀርሙን መከሰት ተከትሎ የጤና ባለሞያዎችና ፖለቲከኞች ብዙ ብለዋል::የጤና ባለሞያዎች ሳይንሳዊ ምክር ሲሰጡን መሪዎች የበሽታውን ስርጭት ለፖለቲካ ሥራ አለመጠቀምና ደዌው በጋራ መመከት እንዳለብን ሲሰብኩን ሰምተናል::
ዛሬ ጥዋት ከመኝታዬ እንደተነሳሁ የሞባይሌ ሶሻል ሚዲያ ጉብኝት ስላላረካኝ የቲቪዬን ስክሪን ስነካካ ከETV ስክሪን ላይ የሆነ እገላለፅ ወደ ጆሮዬ ተወርውሮ ላይወጣ ገባ ::ይህ ቃል ቀኑን ሙሉ በአዕምሮዬ ውስጥ በመመላለስ ጤና ሲነሳኝ ውሏል::ቃሉ የተለመደ ቢሆንም ያለ ቦታው መግባቱ ነው ለካ እንዲህ ሲያስጨንቀኝ የቆየው !
ጠቅላይ ሚንስትሩ ስለኮረና ወቅታዊ መረጃ ሲሰጡ በንግግራቸው መሃል ላይ ” መደመር ነው የሚያዋጣው ” ማለታቸው የንግግራቸው አንግል ውስጤን ሳያምሰው እልቀረም::ጠቅላዩ ከሳምንት በፊት ኮረናን ማንም ፖለቲከኛ ” ለፖለቲካ ፍጆታ” ማዋል የለበትም ማለታቸው ልብ ይሏል !
 1 , ታድያ ለምን ጠቅላዩ ራሳቸውን ተቃረኑ?!
 እሺ እሳቸው እንዳሉት ይሁን ” በዚህ ስዓት የሚያዋጣው መደመር ብቻ ነው ” ሲሉ ምን ማለት ነው ?
በኮረና ሳብያ ያልተደመረ ( እኔ እንደሚገባኝ ያልተባበረ ወይም በአንድ ላይ ያልቆመ ) አለ እንዴ ?! ጃዌ ( ከበቡሽ) እንኳን በአቅሟ ሳይንስንና ሎጂክን ደፍጥጣ ለመሸወድ ብትሞክርም የጠቅላያችንና መንግስታቸውን ቀልብ ወደ ራሷ ለማስደመም ስትወድቅና ስትነሳ ታይታለች ! … ሰሚ እላገኘችም እንጂ ::
ወደ ጠቅላያችን ስመለስ እባክዎን ለጤና ጥበቃ ሚንስትሯ የኮረናን ነገር ለቀቅ አድርጉላቸው::እስቲ የሚሱማቸውንና የተረዱትን ያህል “አፕዴት” ያድርጉ::እርስዎም ከጤና ሚንስትር  ሁለት ወይም ሶስት “Updates”በሃሏ አጠቃለው ሳይንሳዊ ትንታኔና ዝርዝር ማብራሪያ ለመስጠት ክግራና ቀኝ የጤና ሳይንቲስቶችን ; ከፊት ለፊት የጤና ሚንስትሯን ዕውቅ ኢትዮጵያውያንና Physicians and ከጉዳዩ ጋር ግኑኝነት ያላቸው ሙሑራን ጋር  ታጅበው ቢሆን እንዴት መልዕክትዎ በአማረ !
ያለበለዚያ ስልጣንዎን ያለአግባብ እየተጠቀሙ ነው::
ስለሆነም ኮረናን ለፖለቲካ ፍጆታ እየዋሉት ስለመሆኑ ማስረጃው እርስዎ ኖት::እስካአሁን ድረስ ” ኮረና” ን ፖለቲካ ያደረገ መሪም ሆነ ፖለቲከኛ የለም::
በእርግጥ እንናገር ከተባለ ግን በቪዲዮና በቴክስት የተመከረ /የተነገረ ማስረጃ አለ::የእርስዎን ማህበራዊ ሚዲያ ገጽ መመልከትና ETV እንደማስረጃ እሁኑኑ ማየት በቂ ነው ::
እንደኔ ኮረናና ፖለቲካ አብይና መደመር ጋብቻ ፈፅመዋል::ብግልጽ አነጋገር ከተባሉ ኮረና ፖለታከኛ እንዲሆን ጠቅላዩ አስተዋፅኦ አላቸው ::
Filed in: Amharic