>

የነጻው ፕሬስ ፋኖ!!! (አርአያ ተስፋማርያም)

የነጻው ፕሬስ ፋኖ!!!

 

አርአያ ተስፋማርያም
በአሜሪካ ይኖራል። በኢትዮጵያ የነፃው ፕሬስ ፋና ወጊ በመሆን ትልቅ ሚና ከተጫወቱት በቀዳሚነት ስሙ ይነሳል!የነፃው ፕሬስ ጋዜጠኞች “ኢነጋማ” እንዲመሰረት በረከት ስሞኦን ከሚመሩት አፋኝ መዋቅር ጋር እልህ አስጨራሽ ትግል አካሂዶ ማህበሩ እንዲቆም ያደረገና በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅና እንዲያገኝ ያስቻለ ነው! ከአዲስ ዘመን ጀምሮ በተለያዩ የነፃው ፕሬስ ጋዜጦች ላይ በሳል ጦማሮችን ሲከትብ የኖረ ነው! ማህበሩን በታማኝነት፣ በቅንነት ያገለገለና ለጋዜጠኞች መብት መከበር ትልቅ አስተዎፅኦ ያበረከተ ነው!
በጣም የማዝነው የእሱና እሱን መሰሎች ለለውጥ ያደረጉት ታሪክ የሚዘክረው ተግባራቸው አስታዋሽ ያለማግኝቱ ነው! ይህ የፕሬስ ፋና ወጊ ጋሽ ክፍሌ ሙላት ሲሆን ላደረገው ትልቅ ተግባር በአሜሪካ የተለያየ ዝግጅቶች የሚያስናዱና የረባ ነገር ላልሰሩ ስማቸውን እያገነኑ ሽልማት ሲሰጡ እሱና እነበፍቃዱ ሞረዳ፣ ደረጄ ደስታና ሌሎች ለአንድም ቀን ለዚህ ያለመታጨታቸው በጣም ያሳዝናል!! ሌላው ቢቀር ምስጋና ተብሎ እንኳ ለከፈሉት መስዋዕትነት በአደባባይ ሊመሰገኑ አለመሞከሩ አንገት ያስደፋል! ለአንድ አዝማሪ የሚደረገው ሸብረብ ለነጋሽ ክፍሌ ያለመታሰቡ ያሳዝናል! ጋሽ ክፍሌ ሙላት ከፍ ያለ ምስጋናና አክብሮት ይገባዋል!
Filed in: Amharic