>

ሐሳብ በእንተ ኮረና...!!! (ዶክተር ዘሪሁን ሙላት)

ሐሳብ በእንተ ኮረና…!!!

 

ዶክተር ዘሪሁን ሙላት
•የኮረና ቫይረስ የማይዘው ማንን ነው? +++
• የሚይዘውስ እነማንን ነው ??++
•ስለ ኮረና ቫይረስ መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?+
•የአሁኑ የኮረና በሽታ የጉግማንጉግ ወረርሽኝ
መባሉን ያውቃሉ ??+
• የጉግማንጉግ ዝርያዎችስ እነማን ናቸው ?+
 
• አሜሪካ ጉንፋን ሲይዛትና ሲያስላት እኛ እያስነጠስን ፤ እንግሊዝ ሲያተኩሳት የእኛ ሙቀት እየተለካ፤ ቻይና በበላችው እኛ እየታጠብን እንደኾነ ያለፍንበት ሳምንታት ይነግሩናል !!!
 
የኮረና ወረርሽኝ እንደየሀገሩ የፖለቲካ ሴራ ስያሜው ልዩ ልዩ ነው ። ኮረና ማለት ስርወ ቃሉ ላቲንኛ ሲኾን ትርጉሙም የፀሐይ ጨረር መሰል ዘውድ ማለት ነው፤ የጣዖት አምልኮና የሰይጣን አገዛዝ መገለጫ ነው ።
ሰይጣን ማለትና ኮረና ማለት መልእክቱ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ አይነት ነው ። የአሁኑ የሰይጣን መልእክተኛ ኮረና ተላላፊ ሊኾን የሚችል ሰው ሰራሽና አንድ ወገን ላይ ያነጣጠረ በሽታ መኾኑን መጽሐፍ ቅዱስም ኾነ ሳይንሳዊ ጥናቶች አስቀድመው ተናግረዋል ።
የዛሬን አያድርገውና አሜሪካም በቫይረሱ ሳትያዝ የቫይረሱን ስም “ቻይኒስ ቫይረስ” ብላ መናገር የጀመረችው ከክስተቱ በፊት የበሽታው መረጃ በእጇ ሰለነበር ነው ፤ አሜሪካ በሽታውን በመነሻው ኮረና ያላለችው በአሜሪካ የካሊፎርንያ ደቡባዊ አቅጣጫና ለሎሳንጀለስ ምሥራቃዊ አቅጣጫ ላይ 152,374 ሕዝብ ብዛት ያላት ኮረና የምትባል ከተማ ስላላት ከዚያ ጋር እንዳይጣረስባት ነበር ፤ ከዚህ በላይ የነበረው ምክንያቷ ደግሞ በበሽታው ፈብራኪነት እንዳትጠረጠር ስለፈለገችና ቻይና ላይ ለመሳለቅ ስላሰበች ነበር ።።
አሁን ግን አሜሪካም ብትኾን የበሽታውን ስያሜ COVID-19 ብላ መጥራት ጀምራለች ፤ COVID-19 ማለትም corona virus identified in Wuhan, China in December 2019 ማለት ነው ፤ ይኹንና አሜሪካ በዚህም ስያሜ ቻይናን መጥራቷ ስላልቀረ አልሸሹም ዞር አሉ ኾኖባታል ።።
ቻይናዎች በበኩላቸው በሽታው እንደተከሰተ በሽታውን “አሜሪካን ሶልጀርስ ቫይረስ” ብለውት መጥራት ጀምረው ነበር ፤ አሁን ቻይናና የእስያ አህጉር ሕዝቦችም ለሰላም ሲባል በሽታውን ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ ብለውታል ።
እንግሊዞችም በመነሻው በሽታውን ኮረና ብለው የጠሩት ኮረና ማጎግ ከተባለ የአፈ ታሪክ ጀግናና የነገድ ዝርያ መነሻቸው ጋር አያይዘውት ነበር፤ እንዲህም ያሉት እስያውያንን የሚያጠፋ እንጂ እነሱን የማይነካቸው ስለመሰላቸው ነበር ፤ ይሁንና ከጓዳቸው ገብቶ ልዑሉን ሲይዝ ጠቅላይ ሚንስትራቸውን ሲነድፍ የተውሳኩ መጠርያ ከኮረና ወደ ኮቪድ 19 ዕለቱኑ ተቀየረ ።
ይህ ተውሳክ በኢትዮጵያ የተለየ ስም ባይሰጠውም እነርሱ ያሉትን በመድገም “እግዚአብሕርን ብቻ አትመኑ ተጠንቀቁም” የሚለው ማስጠንቀቂያ የበሽታው መገለጫ አዋጅ ኾኗል ። ይህ ደግሞ የአሕዛብነት መታወቅያ አዋጅ ኾነብን እንጂ ከኦርቶዶክሳዊነት ጋር የሚጣጣም ኾኖ አላገኘነውም ፤ መልእክተኞቹ በእግዚአብሔር ከመታመን በላይ ጥንቃቄውን ብቻ እየለፈፉ ብዙዎችን ጭንቀት ውስጥ ከትተዋቸዋል ፤ ይህ ዓይነቱ ልፋፍ የፖለቲካ ማኒፌስቶ ዓላማና ለዛ የተለወሰበት ለመኾኑ ከማንም የተሰወረ አይደለም ።
ከዚህም የተነሣ አሜሪካ ጉንፋን ሲይዛትና ሲያስላት እኛ እያስነጠስን ፤ እንግሊዝ ሲያተኩሳት የእኛ ሙቀት እየተለካ፤ ቻይና በበላችው እኛ እየታጠብን እንደኾነ ያለፍንበት ሳምንታት ይነግሩናል ።
ይኹንና በሀገራችን የትንቢቱ ቃል ይፈጸም ዘንድ የምእመናን እምነት ተፈትኖ አሕዛብ ከክርስቲያኖች የሚለዩበት ኾነ እንጂ የካድሬዎች ልፈፋ ተቀባይነት አግኝቶ እንዳልኾነ ግልጽ ነው ። ይህም ” ሰይጣን በአራቱም በምድር ማዕዘን ያሉትን አሕዛብ፥ ጎግንና ማጎግን፥ እንዲያስታቸው ለሰልፍም እንዲያስከትታቸው ይወጣል፤ ” የሚለው የዮሐንስ ራእይ ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ኾነ ። ( ራእይ 20)
ጉግማንጉጎች የሚባሉት ያፌታውያን በተለይ እንግሊዞች ቀድመው ግብረ ሰዶምን ፈቅደው ፤ ሰይጣንን አምልከው ቤተ እምነታቸውን ዘግተው አሕዛብ ተብለዋል ፤
ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ከ1-30 ቅዱሳን ስለሚታሰቡ ቃልኪዳኔቸው ስለሚዘከር ኢትዮጵያ የቅዱሳን ሰፈር ትባላለች ፣ የድንግል ማርያም የአስራት ሀገር ኢትዮጵያ በአምልኮተ እግዚአብሔር ጸንታ እስከአሁን እግዚአብሔር እየተመለከባት አብያተ ክርስቲያኖቿ ኹሉ ክፍት ናቸው ።
እንግሊዞች ቤተ መቅደሳቸውን እየዘጉ ለዘር መነሻቸው ለማጉግ ስያሜውን ኮረኒዎስ ኮረና እያሉ ሐውልት የሰሩለት የአፈ ታሪክ ጀግናቸው መገለጫ በማድረግና እግዚአብሔርን በመካዳቸው ዛሬ ለሰይጣን መልእክተኛ ኮረና ለተባለው ተላልፈው ተሰጥተዋል ።ለበለጠ ማብራርያ ኹለቱን ማስፈንጠርያዎች ይጫኑና ይመልከቱ ።
ኮረና የሚለውን ስም ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ባናገኘውም ማጎግ የሚለው ተለዋጭ ስሙ በመጽሐፍ ቅዱስ ይታወቃል ፤ ሙሴ በጻፈው የዘፍጥረት መጽሐፍ ምእራፍ 10 ላይ የዘር ሐረጉን መነሻን እናገኛለን ፤ ኖህ ያፌትን ይወልዳል፤ ያፌት ማጎግን ይወልዳል ይላል፨ ማጎግ የያፌት ልጅ ሲኾን ያፌታውያን ጎግማንጉጋውያን ይባላሉ ። ጉጎማንጉጋውያን በአሁኑ ዘመን አውሮፖውያን ፤ በተለይ እንግሊዞች ዋነኞቹ ሲኾኑ እስያውያን እንዲሁም ባቢሎናውያን በዚህ የዘር መነሻ ውስጥ የሚካተቱ ናቸው ።።።
በታሪክ መዛግብት እንደሚታወቀው በእንግሊዞች ሸር አማካኝነት ያላደጉ ሀገሮች በተለይም ካማውያን በብሔርና በቋንቋ እየተከፋፈሉ ሲገዳደሉና በድንበር የጎሳ ግጭት ሲጠፋፉ መኖራቸው ሐቅ ነው ። በአንጻሩ ያደጉት የጉግማንጉግ ሀገሮች እነ እንግሊዝ ራሳቸው ደግሞ እግዚአብሔርን በመካድ ሊጠፉ ሲፈልጉ በሥነ ሕይወት የዘረ መል ምድብ እየተቧደኑ እርስ በርሳቸው እንደሚጠፋፉ በቅዱሳት መጻሕፍት ተከትቧል ።
ከዚህም የተነሣ የጉግማንጉግ ሕዝቦች እነ አሜሪካም ኾኑ እንግሊዞች ከእስያ አህጉር ሕዝቦች ጋር በነገድ ከአንድ ከያፌት ወገን ጎግና ማጎግ ኾነው ቢገናኙም በሥነ ሕይወት ሳይንስ የዘረ መል ምድብ ግን ተለያይተዋል።
ከወቅታዊው የኮረና ቫይረስ እንበለውና ተውሳክ አንጻር የዘረ መል ምድባቸውን ስንለየው በሥነ ሕይወት የዘረመል ምደባ ከአሜሪካኖችና ከእንግሊዞች በተለየ ኹኔታ የእስያ አህጉር ሕዝቦች እነ ሩስያ ፣ኮርያ ፣ቻይናና ባጠቃላይ እስያውያን ሞንጎሎይድ (Mongoloid race ) የተባለ የዘረ መል ምድብ ያላቸው መኾናቸውን ጥናቶች አረጋግጠዋል ።
አሜሪካ ከእንጎሊዝ ጋር በመኾን የኢኮኖሚ የበላይነትን ለማግኘት እነዚህን በሥነ ሕይወት ምድብ ሞንጎሎይድ (Mongoloid race ) ዘረ መል ዝርያ ያላቸውን በተናጠል ነጥላ የደዌ ተውሳክ ፈጥራባቸው በሕመምና በሞት እያሰቃየች የኢኮኖሚ ብሎም የፖለቲካ የበላይነቷን ለማስቀጠል ብትሞክርም ለጣይም ፈንጋይ ያዝበታል እንዲሉ የተውሳኩ ዓይነት መልኩንናኃይሉን ቀይሮ ወደ እረሷና መሰሎቿ እንዲመለስ ስለተደረገ አሜሪካ እራሷ በሞት ጥላ ስር ኾና እርዳታ መጠየቅ ጀምራለች ።። እንግሊዝም ከፈጣሪ በስተቀር ሊታደጋት ማንም እንደማይችል አውቃ ይቅር በሉኝ አይነት ሲቃ ውስጥ ገብታለች !!!
ወዮልሽ እንግሊዝ !
ወዮልሽ አሜሪካ !
ንስሐ ግቢ ማለት ይህን ግዜ ነው !!!
የዚህን ሴራ ክርክርና ሙግት ለመገንዘብ ያህል ማስፈንጠርያውን ተጭነህ ተመልከት https://euvsdisinfo.eu/…/coronavirus-a-wuhan-laboratory-sp…/ https://euvsdisinfo.eu/…/coronavirus-a-racial-bomb-that-af…/ ስለዚህ በሽታው ጎግማንጉጎንና አሕዛብን እነ አሜሪካንና እንግሊዝን እስያውያን አውሮፓውያንን እንደሚመለከት ስለተረዳን የሴም ማደርያ ፤ የካም መታሰብያ ኢትዮጵያን በተለይ ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖችን የሚያስፈራን አይደለም ።
ነገር ግን ለኃጥአን የመጣ ለጻድቃን እንዳይዃንብን ፤ የትንቢት ቃል እንደማይሻር የተረዳን እኛም እምነታችን ፈተና ላይ ወድቆ ከአሕዛብ ጋር እንዳንቆጠር እግዚአብሔርን ይዘን የድንግል ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስን በማምለክ ድንግል እናቱን በመማጸን የቅዱሳንን ተራዳኢነት በቃል ኪዳናቸው መሠረት ዕለት ዕለት በመጠየቅ በገዳማውያን ጸሎት በመተማመን፣ በሱባኤ ፣ በቅዳሴ ፣ በጸሎት፣ በኪዳንና በማዕጠንት ተውሳኩን ከነሰይጣኑ በርትዕት እምነታችን እየተዋጋን እንቀጥላለን ።።።
ይቆየን !!!
Filed in: Amharic