>

ብአዴን እስካለ ድረስ የአማራ ባለጉዳይ የሆነ ሁሉ አይበረክትም!!! (አቻምየለህ ታምሩ)

ብአዴን እስካለ ድረስ የአማራ ባለጉዳይ የሆነ ሁሉ አይበረክትም!!!

አቻምየለህ ታምሩ

እነ ኦሕዴድ/ኦነግ ለተስፋይቱ ምድራቸው ደጀን የሚሆን በአስር ሺዎች የሚቆጠር መከላከያ ሠራዊት  በየዙሩ ሲያሰለጥኑ ሲውሉ፤ መቀመጫውን አዲስ አበባ ያደረገውን የኦነግን የፖለቲካ አመራር እንቅፋት እንዳይመታው  በሪፑብሊካን ጋርድ እያስጠበቁ ጫካ ያለውንና ከሀያ በላይ ባንክ የዘረፈውን፣  ከሀያ በላይ  የኦሕዴድ ባለሥልጣናትን የገደለውን ወታደራዊው አመራር ደግሞ ለማቀፍ ከሀያ ጊዜ በላይ በሬ እያረዱ፣ ግንባራቸውን ደም እየተቀቡና ሽማግሌ እየላኩ  ሲታረቁ ሲውሉ፤ የአማራው ርግማን፣ በሎሌነት መስተፋቅር  የወደቀው  የሕወሓት  የነፍስ ልጅና  የ«አማራ»ው ጉድ ብአዴን ግን በራሳቸው ጥረት የአማራ አለኝታ ለመሆን የበቁትን  የጎበዝ አለቆች [ፋኖዎች] አጥፍቶ  ምስለኔ ላደረጉት አለቆቹ  ያለ ተቀናቃኝ  የጌታ ለማደር  ደፋ ቀና ሲል ይውላል።  ብአዴን እስካለ ድረስ የአማራ ባለጉዳይ የሆነ ሁሉ አይበረክትም።

እውነተኛ የአማራ ድምጽ ብአዴንን ይረብሸዋል። እውነተኛ የአማራ ድምጽ  እስካለ ድረስ ብአዴን አገልጋይነቱን  እስከ ጥግ ድረስ በሰላም ለመከወን አይቻለውም። ስለሆነም  ነባር ይዞታው የሆነውን  ሎሌነት  ለማጽናትና  ታዛዥነቱን  ሙሉ በሙሉ ለማረጋገጥ የሚረብሹትንና የሚያውኩትን  የአማራ ድምጾች ሁሉ ማጥፋት አለበት።  ከሰሞኑ የምናየው  ብአዴንና የእንጀራ ልጆቹ  የሆኑት ኮልኮሌዎች በጎበዝ አለቆች [ፋኖዎች] ላይ የሚያደርጉት ዘመቻም የዚህ አካል ነው።
ብአዴን የሚባለው የአማራ ጠላቶች እንደራሴ እስካለ ድረስ እውነተኛ የአማራ ድምጾችና የአማራ ባለጉዳይ የሆኑ የሕዝብ ልጆች አይበረክቱም። ያለን ምርጫ አንድ ብቻ ነው። የአማራ ጠላቶች እንደራሴና  የሕወሓት ነውረኛ ድርጅት የሆነው ብአዴን ይጥፋ ወይስ እውነተኛ የአማራ ድምጾችና የአማራ ባለጉዳይ የሆኑ የሕዝብ ልጆች ይጥፉ  የሚለው ነው። ምርጫው ያለው በእጃችን ነው!
Filed in: Amharic