>

የጠቅላዩ ሀሳብ (ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም)

የጠቅላዩ ሀሳብ

 

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም

 

ዛሬ ማታ (መጋቢት 26፣ 2012) ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንድ ጥሩና በጣም አስቸኳይ ነገር ተናገረ፤ የምግብ እጥረት መከሰቱ ስለማይቀር አንድ ቤተሰብ የሚችል ቤተሰብ ለሌላ ችግረኛ ቤተሰብ ምግብ ቢሰጥ የአደጋውን ጊዜ ተባብረን እናልፈዋለን የሚል ሀሳብ ነበር፤ ግሩም ሀሳብ ነው፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተፈላለጉ ብሎ ነገሩን ለሕዝብ ከሚጥለው ሥርዓቱን አብሮ ቢያሳውቀን ጥሩ ነበር፤ እኔ እንደሚመስለኝ፡–

• ቀበሌዎች እንደገና የሕዝብ ለሕዝብ ሆነው ቢዋቀሩ፤ ከፖሊቲካ ሎሌዎች ጸድተው
• ቀበሌዎቹ ችግረኞቹን እያጣሩ ቢመዘግቡ፤ ከሙስና የጸዳ ሆኖ
• ምግብም ሆነ ገንዘብ ለመስጠት ፈቃደኞች የሆኑትን መመዝገብ፣
• በጉልበት ሊረዱ የሚችሉትን መመዝገብ፤
• በቀበሌው አንድ ምግብ የማደራጃ አዳራሽ መሥራት

እንደዚህ ቢሆን ችግሩን ቀጥ አርገን ልንይዘው የምንችል ይመስለኛል፡ በጎደለ ሙሉበት፡፡

Filed in: Amharic