ፖሊስ የአዲስ አበባ ኗሪዎችን ቤቶች እያፈረሰ ነው !!!
በዛሬው እለት ከ58 በላይ ቤቶችን በእሳት አቃጥሏል!!!
ኢትዮጲስ
በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ወረገኑ የሚገኙ መኖሪያ ቤቶችን መንግሥት ከማለዳው ሁለት ሰዓት ጀምሮ በሃይል እያፈረሰ ነው።
“በላያችን ላይ ቤታችንን በእሳት እያቃጠሉ ኦሮሚኛ ተናጋሪ ፖሊሶች እያፈረሱብን ነው። ሶፋና ቁም ሳጥኖቻችንን ጨምሮ የቤት ዕቃዎቻችን ተቃጥለዋል። አሁንም እሳቱ እየነደደ ነው። እያሳደዱ በጅምላ እያሰሩን ነው። ሰፈር ውስጥ ወ ንድ ልጅ እንዳናይ ብለዋል። እኔንም እያደኑኝ ነው። አሁን አምልጨ ተደብቄ ነው የማዋራህ።” ብለዋል ቤታቸው የፈረሰባቸው የአካባቢው ነዋሪ።
ቤቶቹ ከመፍረሳቸውም በላይ የእሳት ቃጠሎው የሚያደርሰው አደጋ እንዳሳሰባቸውም ገልፀዋል።
ፖሊስ ቤቶቹን ለማፍረስ በሁለት አይሱዙ ተሽከርካሪ ህጻናትን ጭምሮ ኗሪዎችን ወደ ቦሌ እስር ቤት እንደወሰዳቸውም ያነጋገርናቸው ኗሪዎች ገልፀዋል።
በኮሮና ተህዋሲ ምክንያት መንግሥት ዜጎች ቤት ውስጥ እንዲውሉ እየመከረ ቤቶችን ማፍረሱ እዳሳዘናቸው ገልፀዋል።