>

"በኮሮናቫይረሱ ከተያዙት ሦስቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ሠራተኞች ናቸው!" (የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ተወልደ ገብረ ማሪያም)

“በኮሮናቫይረሱ ከተያዙት ሦስቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ሠራተኞች ናቸው!”

-የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ተወልደ ገብረ ማሪያም
 
በኢትዮጵያ ውስጥ በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ከተረጋገጡት ሰዎች መካከል ሦስቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ሠራተኞች መሆናቸው ተገለጸ።
የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ተወልደ ገብረ ማሪያም ዛሬ በሰጡት መግለጫ ላይ እንዳሉት ከሠራተኞቻቸው መካከል ሦስቱ የኮቪድ-19 ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።
 የታመሙት ሠራተኞች በአሁኑ ወቅት ጤንነት በደህና ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ሥራ አስፈጻሚው አመልክተዋል።
ሮይተርስ የዜና ወኪል እንደዘገበው ደግሞ ከፈረንጆቹ ጥር እስከ ሚያዚያ ድረስ አየር መንገዱ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከሰት ሳቢያ ካለው አቅም 10 በመቶውን ብቻ እየሰራ 550 ሚሊዮን ዶላር ገቢ አጥቷል።
ወረርሽኙ ቻይና ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ በተስፋፋበት ጊዜ በርካታ አየር መንገዶች ወደ ቻይና የሚያደርጉትን በረራ ባቋረጡበት ወቅት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጉዞውን ሲያደርግ መቆየቱ ይታወሳል።
ድርጅቱ አሁን በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን ይፋ ያደረጋቸው ሠራተኞቹ በበሽታው በምን ሁኔታ ሊያዙ እንደቻሉ የተባለ ነገር የለም።
Filed in: Amharic