>
5:16 pm - Saturday May 24, 7028

ነጭ ነጯን ልናገር ነኝና  ጫ ብላችሁ ስሙኝማ (ዘመድኩን በቀለ)

ነጭ ነጯን ልናገር ነኝና  ጫ ብላችሁ ስሙኝማ

 

 

  ዘመድኩን በቀለ
• ጫጫጫ ስትል ዋል እንግዲህ አዳሜ። እንደፈረደብኝ መቼም ዛሬ በትግርኛና በአማርኛ “ ቆንቃ“ ስወገር መዋሌ ነው እንግዲህ። ጫጫቴያሞች ግን ወደ ፔጄ ስትገቡ እጃችሁን መታጠባችሁን፣ አፋችሁን መሸፈናችሁን፣ ርቀታችሁን መጠበቃችሁን እንዳትረሱ። በንዴትም ከቤት እንዳትወጡ። “Stay at home”
 የግድ ሃሳብ ስጥ ባይ ሲበዛ፥ ጉዳዩ ባይመለከተኝም የግድ እንደዚህ አቋሜንም አሳውቃለሁ። ቃሌንም እሰጣለሁ።
•••
ሰሞኑን አንዳንድ የማይባሉ ብዙ ሰዎች ስለ ሦስቱ ሰዎች ሰዎች የሆነ ነገር በል እንጂ። አቋምህ ምንድነው? ዶር ቴዎድሮስ በኢትዮጵያዊነቱ ከአሜሪካ ጋር ተጣላ። ( በሳቅ) ታሪኩ አበራ እንዲያና እነደዲህ ሆነ( በሳቅ) እህተ ማርያም በጾሙ ሥጋ አበላች( በሳቅ ) እናም ተናገር እንጂ እያሉ መቆሚያ መቀመጫ የሚያሳጡኝ በዙ። ስለ እውነት ለመናገር በዚህ ሰዓት ከኮሮና ጭንቀት ተርፈው ስለግለሰብ ጉዳይ ጭንቅ የያዛቸው ሰዎች ሳይ እገረማለሁ። ወይ ሥራ መፍታት። የሆነው ሆኖ ግን አሁን ሁሉም መሄጃ ስለሌለው ተከዝኖ በተቀመጠበት ቤቱ አቋሜን እንደሚከተለው አቀርባለሁ። ያቀነአለይ  !!
የምንነጋገረውም ፦
፩ኛ፥ በዶር ቴዎድሮስ አድኃኖም
፪ኛ፥ በ“ግርታዴ” ታሪኩ አበራ እና
፫ኛ፥ በወሮ ስንዱ ( እህተ ማርያም ) ጉዳይ በተመለከተ ነው።
፩ኛ፥ ዶር ቴዎድሮስ አድሃኖም።
•••
ዶሩ ኤርትራ የተወለዱ፣ እትብታቸውም በዚያ የተቀበሩ በትውልድ ኤርትራዊ በዜግነት ኢትዮጵያዊ የሆኑ ሶዬ ናቸው። እንደብዙዎቹ የኤርትራ ዲቃሎች ኢትዮጵያን ለ26 ዓመት ረግጠው ሲገዙ እሳቸውም እንደ ሌሎቹ ዓድዋውያን በለስ ቀንቷቸው ኢትዮጵያዊ ነኝ ብለው በምርጫ ኢትዮጵያዊ ሆነው በኢትዮጵያ ላይ የተሾሙ ወያኔ ናቸው።ይሄንን አሁን አማሪካም በሰፊው እየጻፈችበት ስለሆነ ሊንኩን ከፍታችሁ አንብቡ። https://trib.al/2ShcXIj ። ዶሩ በዘመናቸውም ትግሬነታቸው ብቻ ሳይሆን ወያኔነታቸው በሰጣቸው ልዩ ፀጋና መብት አንዴ ጤና ጥበቃ ሚንስትር፣ አንዴ ደግሞ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር በመሆን ሥልጣን በማማራጥ እንዳሻቸው ሲሆኑ የኖሩ ወያኔ ናቸው። እናም እኔ ዘመዴ ስለ ወያኔ ምን አገባኝ። ስለ ወያኔም አያገባኝም።
•••
ዶክተሩን በሰውነታቸው ይልቁንም በትግሬነታቸውም እንደ ማንኛቸውም ትግሬ ወንድሞቼ አከብራቸወላሁ። በወያኔነታቸው ግን እጅግ አድርጌ እጸየፋቸዋለሁ። እንደ መርገም ጨርቅ ነው የምፀየፋቸው። ወያኔ ማለት የኢትዮጵያ ካንሰር ናት። ወያኔ ማለት ኢትዮጵያን በዘር የከፋፈለች። ሃይማኖቴን ያዋረደች መርዝ የመርዝም ብልቃጥ ናት። ወያኔ ማለት ዘራፊ ናት። ኢትዮጵያን በቁሟ ግጣ የጨረሰች ነቀርሳ ናት። እናም እኔ በምድር ላይ ዲያብሎስ ሰይጣንና ሥጋ የለበሰችው ወያኔን ሁለቱን ለይቼ አላያቸውም። ለእኔ ወያኔና ሰይጣን በዕድሜ ቢበላለጡ እንጂ በተንኮል አንድ የሆኑ ናቸው። እንዲያውም ሳይጣን ራሱ በወያኔ ግፍና ጭካኔ የሚቀና ሁሉ ነው የሚመስለኝ።
•••
ዶክተር ተዎድሮስ አድሃኖም ማለት በገዛ አፋቸው፣ አንደበታቸው እኔ ወያኔ ነኝ ያሉ ሰው ናቸው። ወለጋ ላይ ልጃቸውን ገድሎ የልጃቸው አስከሬን ላይ ያስቀመጠው አረመኔ ወያኔ ነኝ እኮ ነው ያሉት። ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስን ቋንጣ፣አድርጎ የበላ፣ የዋልድባን መሬት ያረሰ፣ መነኮሳቱን አርዶ የበላ ወያኔ ነኝ እኮ ነው የሚሉት። በ1983 የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን፣ በ1997 ከትግራይ በቀር መላውን የኢትዮጵያ ህዝብ አርዶ የበላው ወያኔ ነኝ እኮ ነው የሚሉት። እና በምን ሂሳብ ነው ወያኔ ነኝ የምለው። አይመለከተኝም።
•••
በነገራችን ላይ ዶሩ ክብሮም የሚባል ታናሽ ወንድም አላቸው። በአካል አላውቀውም በፌስቡክ ነው የማውቀው። በክርስትናው የማደንቀውም ልጅ ነው። ለእኔም በዚሁ በፌስቡክ ወዳጄ ነው። በተለይ በተሃድሶ ጉዳይ ግምባር ቀደም ተሳታፊም ነው። ከእኔም ጋር የመረጃ ልውውውጥ እናደርግም ነበር። ዶር ቴዎድሮስ የዚህ ጓደኛዬ ወንድም በመሆናቸው ደስ ይለኝና የካንሰሯ የህወሓት፣ የገዳይዋ የህወሓት አጋርና አመራር የነበሩ ሰው በመሆናቸው ግን ከልቤ፣ ከአንጀቴም እጠየፋቸዋለሁ። የማውቀው ወያኔ የገባበት ሀገርም፣ ዕድርም፣ ማኅበርም ይፈርሳል። አሲዳም ናት ወያኔ። ብልጥ መሳይ ፋራ ናት ወያኔ። እሷም ደጋፊዎቿም ይፈርሳሉ።
•••
እኔ ዘመዴ ዶሩ ሲሾሙም አልተቃወምኩም።  አልደገፍኩምም። ቢዝነሴም አልነበረም። ጉዳዬም አልነበሩም። ኬሬዳሽ። አሁንም ሊሻሩ አንድ ሐሙስ ሲቀራቸው አልቃወማቸውም። አልደግፋቸውምም። አሁንም አጀንዳዬ አይደሉማ። ምንአገባኝ። ወያኔና የወያኔ ቡችሎች ይደግፏቸው እንጂ እኔ ዘመዴ ምን አገባኝ። ሶዬው ሲሾሙ ዛሬ እሳትና ጭድ የሆኑት ቻይናና አማሪካ ናቸው ደግፈዋቸው የተሾሙት። እኔ አልደገፍኩም። አልተቃወምኩምም። ደግሞም ብደግፋቸውም ብቃወማቸውም ምንም አባቴ አላመጣም ነበር። አሁንም ምንም አላመጣም። ዛሬ አማሪካና ቻይና ከኢትዮጵያ ጋር ለዋንጫ ጨዋታ ጥሎ ማለፍ ለመግጠም በሚጣለዙበት በዚህ ጊዜ ለጥቅማቸው ሲሉ በገንዘባቸው በቀጠሩት የመሃል ዳኛ ጉዳይ እርስ በእርስ  ሲጣለዙ እኔን ምን አገባኝና ነው በማያገባኝ ጉዳይ የምጣደው? ለምን እንጦሮጦስ አይወርዱም። [ ኢትዮጵያዬ ብቻ ደህና።]
•••
ዶሮ ቴዎድሮስ ሲሾሙ የህወሓት ደጋፊ የነበሩት በሙሉ ኢትዮጵያዊ የተሾመ እስከማይመስል ድረስ አበጠሩ። እንዴትና ለምን እንደተሾሙ ልባቸው እያወቀ “ ወዲ ተጋሩ፣ አምበሳ ትግራይ፣ ወያኔ እዩ። ቅብጥርሶ ምንጥስዮ ሲሉ ፎለሉ፣ ፍገሉ።” ብዙ ኢትዮጵያውያን የዓለም አቀፍ ድርጅቶችን ለመምራት የኢትዮጵያን ድጋፍ ሲፈልጉ የወያኔ ደጋፊ ባለመሆናቸው ብቻ የድጋፍ ፊርማ ተነፍገው ከጨዋታው ውጪ መሆናቸው ሲናገሩ ሰምተናል። እናም ወያኔ ከቻይና ጋር ገጥሞ ተባጥሶ እንዲሾሙ አድርጎ ሲያበቃ እንዲያ ደርሰው ሚሪንዳ ካልተቀቀለልን ሲሉ የከረሙና የተሾመው ትግሬ፣ ዜግነቱም ትግራዋይ ነው ሲሉን ኖረው ዛሬ ዶክተሩ ከቀጣሪያቸው ችግር ሲገጥማቸው “ቴዲ በአሜሪካ ጥርስ የተነከሰበት ኢትዮጵያዊ ስለሆኑ ነው፣ አፍሪካዊ ስለሆኑ ነው ” ብለህ እዬዬ ብትል ሥራህ ያውጣህ። እዚህ ዐማራና ትግሬን፣ ኦሮሞና አማራን፣ ኦሮሞና ሱማሌን ሲያናክስ የከረመው ሰውዬ አሁን አፍሪካዊ ነኝ፣ ዝንጀሮ ነኝ ቢል ጥቂት አፍሪካዊ ያስከትል ይሆናል እንጂ እኔ በበኩሌ አልሰማውም። ይሄ ታክቲክ የሚሠራው ኢትዮጵያ ብቻ ነበር። ፈረንጅ ወዳጄ አይሸወድልህም። ሥራህ ያውጣህ። እኔ የማውቀው ዶሩም እንዳሉት ወያኔ መሆናቸውን ብቻ ነው። ስለወያኔ ደግሞ አያገባኝም። እንጦሮጦስ  !!
•••
ለሾም ሲል ትግራዋይ ሊሻር ሲል ኢትዮጵያዊ ? ሞኝህን ብላ። ቴዎድሮስ ማለት በአዲስ አበባ ጁፒተር ሆቴል ከሃይማኖት አባቶች እጅ ሰዶማውያንን የሚያወግዝ መግለጫ ሊሰጡ ሲል ለጋዜጠኞች ጭምር የተበተነ መግለጫ በፌደራል አስቀምቶ ያባረረ። እነ ፓትርያርክ አባ ጳውሎስን፣ ካርዲናሉን፣ ሼኩንና ፓስተሩን ያዋረደ፣ ለተቃውሞ የወጡትን 200 ያህል የካዛንችስ ልጆች አሳፍሶ ወፌ ላላ ያስገረፈ እኮ ነው። እኔ ምን አገባኝ። አይመለከተኝም። ሥራው ያውጣው።
•••
እንዲያው ኧረ ለመሆኑ በኢትዮጵያ ግን ያለ ትግሬ የጤና ጥበቃ ሚንስትርነት ሥፍራ ሌላ ዜጋ የማይዘው ለምንድነው ግን? በክፉ ሳታዩ መልሱልኝ።
• ቴዲ ( ኤርትራ ተወላጅ ትግሬ )
• አማን ( ባህርዳር ተወላጅ ትግሬ)
• ሊያ ( የት እንደተወለዱ አላውቅም ግን ትግሬ) ናቸው ይላሉ። በዚህ ላይ እዚህ መርዛማ ስፍራ ላይ ትግሬ ሲቀመጥ ዐማራ የወሊድ ቁጥሬ እያሽቆለቆለ ነው የሚሄደው። አሁን እንኳ በኮሮና ጉዳይ ትግራይና ኢትዮጵያ በዝግጅት ራሱ ሰማይና ምድር ናቸው። ቻይናና ትግራይ የሆነ መረጃማ ቀድመው ሳያገኙ አልቀሩም የሚሉ አሉ። ተሿሚው ደግሞ ወያኔ መሆኑን አንርሳ።
•••
ዐማራ ደግሞ ልክ አሁን አሜረካ በዶር ቴዎድሮስ ላይ እንደምትነጫነጨው በዶሩ ላይ ይነጫነጫል። ዘሬን አጥፍቷል። በኪኒን ትውልዴን፣ ነገዴን ገድሏል ነው የሚለው። በወባና በኮሌራ፣ በኤድስም ፈጅቶናል ነው የሚሉት። አሁን ዶሩን በምድራዊ ፍርድቤት ከሶ ለመሟገት የሚቻል ባይመስልም አሜሪካ ሆዬ በቤቷ የሬሳ ክምር ሲበዛባት ዶሩ ድሮም በኢትዮጵያ የዘር ማጥፋት የፈጸመ ነው ብላ የከረመ ፋይል ይዛ ከች ብላለች። ዶሩ ከቻይና ጋር ተመሳጥሮ ልክ እንደ ዐማራ አሜሪካዊ ዘሬ ፈጅቷል። የቻይናን ሞይ ቀሽቧል እያለች ነጠላ ዘቅዝቋ እያስነካችው ነው። ይቧቀሱ ለምን አፈር ከድሜ አይጋጋጡም። እኔ አያገባኝም
•••
የገረመኝ ነገር ግን ህወሓት ሽንቷን እያጠጣች ያሳደገቻቸው የበድኗ የብአዴን ግልገሎች አቶ መላኩ አለበል፣ ጠገዴን ፈርሞ ለህወሓት ያስረከበው አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ሳይቀሩ ለእንጀራ አባታቸው ወያኔ እየዬ ሲሉ ባይ በሳቅ ፍርስ ማለቴን ግን አልደብቃችሁም። ሆኖም ግን ከምር አያገባኝም። አንተ ኢትዮጵያዊ አይደለህም እንዴ? ዘመዴ የሆነ ነገር በል እንጂ እያላችሁ ለምትወተውቱኝ መልሴም ይኸው ነው። እኔ ለወያኔ አያገባኝም። አስተያየትም አልሰጥም።
•••
ደክተሩን ግን ዕድለ ቢስ ናቸው። በኢትዮጵያ ሳሉ ኮሌራ፣ በWHO ሳሉ ደግሞ ኮሮና አልተፏቷቸውም። ለኮሬላ አተት የሚል የዳቦ ስም ሰጥተው ነው የፈጁት ይሏቸዋል ከሳሾቻቸው። ለኮሮና ግን የዳቦ ስም ለመስጠት ብዙም አልቻሉም። አሁን አማሪካ የጦስ ዶሮ አድርጋ ኦሳማ ቢን ላዲን በገባበት ገመድ ልታስገባቸው ያሰበችም ይመስላል። ሸንኮራዬ። እኝክ፣ ምጥጥ፣ ትፍት። ሥራዎት ያውጣዎት። ኢትዮጵያን የነካ የሆነ ቀን ጊዜ ጠብቆ ይነካል። ኢትዮጵያን ያዋረደ ጊዜው ይርዘም እንጂ የሆነ ቀን ተዋርዶ መሞቱ የታወቀ ነው። አሸባቴ የኢትዮጵያ አምላክ ፍርዱን ይስጥዎት።

••• ሥራቸው ያውጣቸው።

• በቀጣይ ደግሞ “የተዋረዱት ከፉ የግርታዴ ታሪኩ አበራና” በእህተ ማርያም ጉዳይ ላይ ሳልፈልግ አስተያየቴን እንድሰጥ በመገደዴ እኔም በሁለቱም ላይ አስተያየቴን መስጠት ፈቃዴ ያልነበረ በመሆኑ ያለኝ የግል ዕይታዬ እንዲሁ ተራ በተራ በአጭሩ ለማስቀመጥ እወዳለሁ። በነገራችን ላይ ታሪኩም ከመሬት ተነስቶ ወደ እንግሊዝ የተወሰደ ሰው ነው። እህተ ማርያምም ከእንግሊዝ ጠቅልላ ወደ ኢትዮጵያ የገባች ናት። እንግሊዝ ደግሞ በኮሮና ቫይረስ እየተቀጣች ነው።
• ነገ አርብ የግሪሳ ታሪኩን አበራን
• ከነገ ወዲያ በእኛ በኢትዮጵያውያን አቆጣጠር ቅዳሜ በእንግሊዛዊቷ በእህተ ማርያም አቆጣጠር ደግሞ ማክሰኞ ወይ ረቡዕ በሁለቱ የእንግሊዝ ልዑካን ላይ ቃሌን እሰጣለሁ። ሁለቱም የመርካቶ የ7 ተኛ ሰፈር ልጆች ናቸው የሚሉም አሉ።[ ደመቀ መኮንንና እህተ ማርያምን ደግሞ ምን ያገናኛቸዋል? ደመቀ መኮንን ከምክትል ጠቅላይነት የማይወርደው እንግሊዝ …  ለማንኛውም …
ማስታወሻ | ~ በሁለቱ ላይ መረጃ አለን የምትሉ በውስጥ መስመር ላኩልኝ።
•••
ሻሎም !  ሰላም !  
ዘመድኩን በቀለ ነኝ። 
ሚያዝያ 1/2012 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
Filed in: Amharic