>

"የገበያ ግርግር ለሌባ በጀው!!!"(ቀሲስ ደጀኔ ሽፈራው)

“የገበያ ግርግር ለሌባ በጀው!!!”

  ቀሲስ ደጀኔ ሽፈራው
 በእውነቱ ልበ ብርሃኖቹ አበው እንደተናገሩት በደራ ገበያ መካከል የሚ ነሣ ግርግር የሚበጀው ለሌባ ብቻ ነው።ባለፈው እንደምታስታውሱት አገሪቱ በአራቱም ማዕዝን በአክራሪ “ብሔረተኞች” በተያዘችበት፥አብ ያተ ክርስቲያናት እንደ ዋዛ በሚቃጠሉበት፥ካህናት እና ምእመናን በሚ ታረዱበት ሰዓት፦እነ እገሌ ጥቂት ጳጳሳትን ጨምረው፦”የኦሮምያን ቤተ ክህነት እናቋቁማለን፥ይህንንም ዓላማችንን ትግርኛ ተናጋሪ የሆኑጳጳሳት ደግፈውልናል፤”በማለት ያዙን ልቀቁን ብለው ነበር።
በወቅቱም ፕሮቴስ ታንቱና እስላሞቹ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭው ዓለም አብረዋቸው ተሰልፈው እንደነበረ፥ ፀሐይ የሞቀው እና አገር ያወቀው እውነት ነው። እንደ አገር ወገኖቻችን፥ በሃይማኖት ግን ባዕዳን የሆኑ እነዚህ ሰዎች ያልገባቸው ነገር ቢኖር ነገ ተነገ ወድያ የነርሱ ተራ መሆኑን ነው። እኛም ከምናውቀው ተነሥተን የሚቀጥለው ደግሞ፦”የትግራይ ቤተ ክህነት ነው፤”ብለን ነበር። እነሆ የተናገርነው አልቀረም። ይኸው በአቶ ስብሐት ነጋ መሪነት፦ የውስጥ ለውስጥ ሴራው አልቆ በአደባባይ ተገልጠዋል። ዓላማቸውን ለማሳካትም፦ ሠላሳ ዓመት ታግለው ያልጣሉትን ማኅበረ ቅዱሳንን፦ አስቀድመው ለመምታት እንደ አዲስ እቅድ አውጥተዋል። የመረጡትም ጊዜ፦እንኳን ኢትዮጵያ መላው ዓለም በኮሮና ምክንያት የታወከበትን ጊዜ ነው። ለዚህ ነው፦”የገበያ ግርግር ለሌባ በጀው፤” ያልኳችሁ። ይገርማል፥የዓለም መሪዎች ንስሐ እየገቡ ባለበት በዚህ ሰዓት የኛዎቹ ጉዶች ግን በኃጢአትና በበደል እንደጃጁ ወደ መቃብር ሊወርዱ ነው።ኮረናን የፈሩ ሰዎች እግዚአብሔርን አልፈራ አሉ። ወገ ኖቼ፦ መቃብሩ የተማሰ፥ ልጡ የራስ ሰው እንዴት ወደ ልቡናው ተመልሶ ንስሐ አይገባም።
እንዲህም እየሆነ ቤተ ክርስቲያን ለሁሉም ኢትዮጵያ ውያን ለእነርሱም ጭምር ከታዘዘው መቅሠፍት እንዲሰወሩ በዕንባ እየጸለየች ነው። እነርሱ አስቀድመው በውጭ አገር ያደራጇቸው አብያተ ክርስቲያናትም ቢሆኑ ስማቸው ብቻ ነው የኢትዮጵያ። ምክንያቱም፦ ሲመሠረቱም ሆን ተብሎ ለዚሁ ዓላማ የተዘጋጁ በመሆናቸው የሚጠ ብቁት የነ “አቡነ” ስብሐትን ዐዋጅ ብቻ ነው።ይሁን እንጂ አይሳካላቸ ውም። ወገኖቼ፦ለማገናዘብ እንዲመቻችሁ፥ይኸንን በተመለከተ የዛሬ ሰባት ወር ለጥፌው የነበረውን ጽሑፍ እንደገና ለጥፌላችኋለሁ።ይህ ዘመን ከሃይማኖታችን እና ከሌላው የቱን እንደምንመርጥ የምንመዘን በት ዘመን ነው።እግዚአብሔር ይሁነን።
ባለሥልጣኖች ለምን ወደ ሮቴስታንትነት ፈለሱ?
     ማንኛውም ሰው የፈለገውን እምነት የመከተል መብት እንዳለው ከማንም በላይ እውቀቱ አለን።ከእኛ የሚጠበቀው በእኛ ድካም የምእ መናን ፍልሰት  እንዳይመጣ እንደተሰጠን ጸጋ መጠን ተግቶ ማገልገል ብቻ ነው።በተለያየ ምክንያት የፈለሱትንም በጎች ወደ በረታቸው የመ መለስ ሃላፊነትም አለብን።
  የምእመናን ፍልሰት ለምን እንዳጋጠመ የትለያየዩ ምክንያቶችን መደርደር ቢቻልም የባለሥልጣኖቹ ትንሽ ለየት ይላል:-
የፖለቲካ ሥልጣ ኑን ሙሉ በሙሉ የተቆጣጠሩት የኢትዮጵያ ባለሥልጣኖች ወደ ፕሮቴ ስታንትነት መፍለስ ከጀመሩ እጅግ ሰነባብተዋል።ነጭ የፕሮቴስታንት ፓስተሮች በኢትዮጵያ ፓርላማ ውስጥ በነ አባ ዱላ ላይ እጃቸውን ጭነው ሲጸልዩ በገሀድ አይተናል።በኃይለ ማርያም ደሳለኝ ጊዜ ከአንድ አፍሪካ ሀገር ሐሰተኛ ነቢይ አስመጥተው በቤተ መንግሥቱ ማጸለያቸ ውን ሰምተን እንደ ዋዛ እልፈናል።በዩኒቨርስቲዎቻችን ኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎች በጾም ወራት ሥጋ ካልበላችሁ ተብለው ሲገደዱ ሰምተን አይተን ለአንድ ሳምንት ተንጫጭተን ዝም ብለናል።ለሃያ ስምንት ዓመ ታት በዓለ መስቀል እና በዓለ ጥምቀት እናከብርባቸው የነበሩ ቦታዎቻ ችን በጉልበት ሲነጠቁ ሰሚ የሌለው ጩኽት ጮኽናል።አብያተ ክርስቲ ያናት ሲቃጠሉ፥ካህናት እና ምእመናን ሲታረዱ እያየን እርር ድብን ብለን ቀርተናል።ያለንበት ዘመን፦ዘመነ ዮዲት ጉዲት፣ዘመነ ግራኝ መሐመድ፣ ዘመነ ፋሽስት ኢጣልያ፣ዘመነ ሱስንዮስ ሆኖብናል።
  ይህ ሁሉ ለምን ሆነ? ጩኽታችንስ ለምን የቁራ ጩኽት ሆነ?
ደማችንስ ለምን ደመ ከልብ ሆነ? እዚህ የምኖርበት ሀገር ውሻ እንኳ ትልቅ ክብር አለው።ክብርት፥ልዕልት፥ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በባለ ሥልጣኖች ዘንድ ለምን ክብር አጣች? እስኪ የሰማሁትን አንድ ታሪክ ልንገራችሁ።ታሪኩን የነገረኝ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል አድዋ ተወልዶ ያደገ፥አምስት ኪሎ ዩኒቨርስቲ የተማረ ባልንጀራዬ ነው።ፍጹም ኢትዮጵ ያዊ፣ፍጹም ኦርቶዶክሳዊ ነው።ከተማሪነት ጊዜ ጀምሮ የማኅበረ ቅዱሳ ንም አባል ነው።የሥጋ ዘመዶቹ ታላላቅ ባለሥልጣኖች ነበሩ።
             ነፍሳቸውን ይማረውና ሟቹ ጠቅላይ ሚንስትር  መለስ ዜናዊ በአንድ ወቅት ማኅበረ ቅዱሳንን ከእስልምና አክራሪዎች ጋር  በማነጻ ጸር በፓርላማ ላይ ይከሱታል።በዚህን ጊዜ እስከ ዛሬም ድረስ ባልንጀ ራዬ የሆነውን ገብረ መድኅንን፦”ለምንድነው እነዚህ ዘመዶችህ ማኅበረ ቅዱሳንን እንዲህ ንክስ አርገው የያዙት? ማኅበሩ ፖለቲካ ውስጥ እንደ ማይገባ አንተ ራስህ ምስክር ነህ፤”ብዬ በቀልድ አዋዝቼ ጠየኩት።እር ሱም፦”ይህንንማ በደንብ አሳምረው ያውቁታል፥የተማረውን ትውልድ በኦርቶዶክሳዊነት ያጸና ፣ቤተ ክርስቲያኒቱን ከውስጥ እና ከውጭ ጠላት የጠበቀ ማኅበር እንደሆነ ማንም እንዲነግራቸው አይፈልጉም። ራሳቸው በደንብ አጥንተው ደርሰውበታል።”ሲል መለሰልኝ።እኔም ገር ሞኝ፦”ታድያ ችግሩ ምንድነው?” ስል ዳግመኛ ጠየኩት።
          ባልንጀራዬም እስከ ዛሬም ድረስ የሚገርመኝን አንድ ታሪክ እንደሚከተለው ተረከልኝ።”ከኢትዮ ኤርትራ ጦርነት በፊት መለስ ዜናዊ ሃይማኖትን በተመለከተ አንድ ጽሑፍ ያዘጋጅና በጣም ታማኝ የሚባሉ ባለሥልጣኖች ብቻ ማታ ማታ ቤተ መንግሥት ተሰብስበው እንዲወያ ዩበት ያደርጋል። ለተወሰኑ ወራት እስከ እኵለ ሌሊት እየቆዩ ተጨቃጭቀ ውበታል።የጽሑፉ መንፈስ፦ኢትዮጵያን እኛ እንደምንፈልጋት  አይነት ለማድረግ የግድ እምነት አልባ ትውልድ ማፍራት አለብን፥ የሚል ነበር። ምክንያቱም እምነት አልባ ትውልድ ሀገሬን ታሪኬን አይልም። በማጠቃ ለያም የተስማሙበት አሳብ፦እምነቶችን ሁሉ ማጥፋት ቢያቅተን መቼም ቢሆን ከኦርቶዶክስ ፕሮቴስታንት ይሻለናል።ስለዚህ ትውልዱን በፕሮቴስታንቲዝም ማደንዘዝ አለብን፤የሚል ነበር፤ስለዚህ ኦርቶዶክስን ለማዳከም ማኅበረ ቅዱሳንን አስቀድሞ መምታት የሚለው የመጀመ ሪያ ስልታቸው ነው።ይኽንን ወስነው ወደ ተግባር ሊገቡ ሲሉ የባድመ ጦርነት ፈነዳ።ከጦርነቱ በኋላ ደግሞ ሕወሓት ለሁለት ተሰነጠቀ።እስ ኪረጋጉም ትንሽ ጊዜ ወሰ ደባቸው” አለኝ።
    እንግዲህ ለዚህ ነው ፥ኦርቶዶክስ እንዲጠፋ ፕሮቴስታንቲ ዝም እንዲስፋፋ በገሃድ ሳይሆን በስውር የታወጀብን።ለዚህ ነው አብዛ ኛው ባለ ሥልጣን ወደ ፕሮቴስታንት የፈለሰው።ለዚህ ነው ተሀድሶ መናፍቃንን ፈትተው የለቀቁብን።ለዚህ ነው ሐሰተኞች ነቢያትን እንደ አሸን ያፈሉብን።ለዚህ ነው አብያተ ክርስቲያናት እየተቃጠሉብን፥ ካህና ትና ምእመናን እየታረዱብን ዝም በሉ የሚሉን።በአብዛኛው ክልል ባለ ሥልጣን የሚሆነው ፕሮቴስታንት ነው።ኦርቶዶክሱ ሠርቶ የሚበላው የሚያመልከውም በሰቀቀን ነው።በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች የተፈና ቀለው ኦርቶዶክሱ ነው።ሀብቷ እና ንብረቷም በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ በሰገሰጓቸው ካድሬዎች እንዲመዘበር አድርገዋል።የመጨረ ሻው ሙከራቸው ደግሞ፦የትግራይ፣የኦሮሞ ቤተ ክህነት ብሎ ከፋፍሎ ማዳከም ነው።
        ሃይማኖታችንን የምትወዱ፥ሴራው ያልገባችሁ የተለያየ ቋንቋ የምትናገሩ ኦርቶዶክሳውያን ወገኖቼ! እባካችሁን ከዘር ከረጢት ውስጥ ውጡና በቅድሚያ ቤተ ክርስቲያናችሁን አድኑ።ጌታ በወንጌል፦ “አስቀ ድማችሁ መንግሥቱን እና ጽድቁን ፈልጉ፤”ያለውን ሕያው ቃል አትርሱ። መንግሥቱን የተባለ ሃይማኖት ነው፥ጽድቁን የተባለ ደግሞ ምግባር ነው።እግዚአብሔር ሀገራችንን፣ቤተ ክርስቲያናችንን ይጠብቅልን፥ አሜን።
Filed in: Amharic