>

በ24 ሰአት ምርመራ ከተደረገላቸው 345 ግለሰቦች  አራቱ የኮሮና ቫይረስ  ተገኘባቸው! (ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር)

በ24 ሰአት ምርመራ ከተደረገላቸው 345 ግለሰቦች  አራቱ የኮሮና ቫይረስ  ተገኘባቸው!!!
ቫይረሱ ተገኝቶባቸው ክትትል እያደረጉ ከሚገኙት መካከል 10 ግለሰቦች አገግመዋል!!!
ባለፉት ቀናቶች በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ለ3,500 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተከናውኗል።
ዛሬ ቫይረሱ የተገኘባቸው አራቱም ግለሰቦች ኢትዮጵያዊያን ናቸው።
ሁለቱ ወንድ ሁለቱ ደግሞ ሴቶች ሲሆኑ ሶስቱ የጉዞ ታሪክ ያላቸው ናቸው።
ከእነዚህም መካከል አንድ የ30 ዓመት ሴትና አንድ የ29 ዓመት ወንድ ኢትዮጵያዊያን ከዱባይ መጥተው በለይቶ ማቆያ ክትትል ሲያደርጉ የነበሩ ናቸው፡፡
አንድ የ33 ዓመት ሴት ኢትዮጵያዊት ደግሞ የአሜሪካ አገር የጉዞ ታሪክ ያላት ናት።
ሌላኛው ግለሰብ የ42 ዓመት እድሜ ያለው ኢትዮጵያዊ ነው።
ግለሰቡ የውጭ አገር የጉዞ ታሪክ የሌለው ሲሆን፤ በህመሙ ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ እንዳለውና እንደሌለው እየተጣራ ነው።
በሌላ ዜና ቫይረሱ እንዳለባቸው ተረጋግጦ ክትትል እያደረጉ ከሚገኙ ግለሰቦች መካከል ተጨማሪ ስድስት ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
ይህን ተከትሎም በአጠቃላይ ከህመሙ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ወደ 10 ከፍ ብሏል።
በጽኑ ህሙማን ክፍል ክትትል ሲያደርጉ የነበሩት የ65 ዓመት ኢትዮጵያዊት ትናንት ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል፤ አሁን ላይ በጽኑ ህሙማን ክፍል ክትትል የሚደረግላቸው ህሙማን የሉም።
Filed in: Amharic