>

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ማስፈጸሚያ  ደንብ ይፋ ሆነ!!! (ኢዜአ)

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ማስፈጸሚያ ደንብ ይፋ ሆነ!!!

ኢዜአ
ክልከላን በሚመለከት ማንኛውም ሃይማኖታዊ ይሁን ፖለቲካዊ ስብሰባዎች፣ እድር፣ ደቦ፣ እቁብና ሌሎችም ከ4 ሰው በላይ ስብሰባዎች ክልክል ናቸው።
ከአራት ሰዎችም ቢሆኑ ሁለት የአዋቂ ሰው እርምጃ የጠበቀ መሆን እንዳለበት አቃቤ ህጓ አብራርተዋል።
ቀብርና ሌሎች አስፈላጊ ጉዳዮች ሲኖሩ ግን እየታዩ  ሊፈቀዱ የሚችሉበት አሰራር መኖሩን ጠቁመዋል።
ታራሚዎች ከጠበቆቻቸው ጋር አስፈላጊው ጥንቃቄ ተደርጎ እንዲገናኙ የሚፈቀድ ቢሆንም ጥየቃ ለሚሄዱ ሰዎች የማይፈቀድ መሆኑ ተገልጿል።
በፖሊስ የተያዙ እስረኞችንም ስንቅ ከማቀበል በስተቀር መገናኘት የተከለከለ መሆኑን አስረድትዋል።
በድንበር አካባቢ ከካርጎ፣ የደረቅና ፈሳሽ ጭነት አገልግሎቶች በስተቀር ሌሎች እንቅስቃሴዎች ዝግ ተደርገዋል።
የቤት ተከራዮች በራሳቸው ፍላጎት ካልወጡ በስተቀር ማስውጣትና ኪራይም መጨመር በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተከልክሏል።
ሰራተኞችን መቀነስና የስራ ቅጥር ውል ማቋረጥም ተከልክለዋል
በዚህ ደንብ መሰረት ተማሪዎችና መምህራን  በኦን ላይን ካልሆነ በአካል እንዲገናኙ አይፈቀድም።
ስፖርታዊ ጨዋታዎች፣ የህፃናትም ይሁን የሌሎች መጫወቻ ስፍራዎች እንዲሁም የእጅ መጨባበጥ ሰላምታ የተከለከለ ነው።
በትራንስፖርት ዘርፍም አገር አቋራጭ ካለው ወንበር ከ50 በመቶ በላይ ተሳፋሪ መጫን የተከለከለ ነው፡፡
Filed in: Amharic