>

የቀድሞው የቅንጅት አመራር ፣ የህዝብ ተወካዮች አባል እና የአንድነት ፓርቲ አመራር የነበሩት አቶ ተመስገን ዘውዴ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ (ህብር ራድዮ)

የቀድሞው የቅንጅት አመራር ፣ የህዝብ ተወካዮች አባል እና የአንድነት ፓርቲ አመራር የነበሩት አቶ ተመስገን ዘውዴ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

ህብር ራድዮ
አቶ ተመስገን ዘውዴ በጤና እክል በህመም ላይ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ከቤተሰቦቻቸው የተገኘ መረጃ ያመለክታል።
አቶ ተመስገን ዘውዴ የተቃዋሚው ሀይል ተጠናክሮ እንዲወጣ ትልቅ ፍላጎት የነበራቸው ሲሆን ምክር ቤት ሳሉም በህዝብ ጥቅም ላይ ጉዳት ያመጣሉ ባሉዋቸው አዋጆች እና ፖሊሲዎች ላይ በግልጽ በመቃወም ይታወቃሉ።
አቶ ተመስገን በኢኮኖሚያዊ ጉዳይ አቶ መለስ ለምክር ቤቱ ሪፖርት  በሚያቀርቡበት ወቅት ያቀረቡትን የማምታታት ገለጻ በግልጽ በመቃወማቸው የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሊያሽሟጥጧቸው ሲሞክሩ ፊት ለፊት በመጋፈጣቸው ብዙዎች ያስታውሷቸዋል።
አቶ ተመስገን ዘውዴ የእንድነት ፓርቲን በውጭ አገር ድጋፍ እንዲያደርግ በአንድ ወቅት በተለያዩ ስቴቶች በመጉዋዝ እንቅስቃሴ ያደርጉ ነበር። ለዚሁ ዓላማ ከስድስት ዓመት በፊት ቬጋስ በመጡበት ወቅት ከሕብር ሬዲዮ ዝግጅት ክፍል ጋር ቆይታ አድርገው ነበር።
በአቶ ተመስገን ዘውዴ ሞት የተሰማንን ሐዘን እየገለጽን ለቤተሰቦቻቸው፣ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ፍትህና ነጻነት እንዲሳካ በበኩላቸው ትግል ላደረጉለት ወገናቸው መጽናናትን እንመኛለን።
Filed in: Amharic