>

ቤት ለቤት የሚባል የኮሮና ምርመራ የለም!! (ቅዱስ ማህሉ)

ት ለቤት የሚባል የኮሮና ምርመራ የለም!!

 

ቅዱስ ማህሉ
 
ታኬ ሲቦተረፍ “ቤት ለቤት እየዞርን የኮሮና በሽታን የደም ምርመራ እናደርጋለን” ብሎልሀል። ስማ ! ሰዉዬ እነ አሜሪካም በቂ ባለሙያና በቂ መመርመሪያ ስለሌላቸው ቤት ለቤት እየሄዱ አልመረመሩም  እስካሁን በአለም ላይ አንድም ሃገር (እደግመዋለሁ አንድም ሃገር) ቤት ለቤት እየዞረ የኮሮና በሽታ የደም ምርመራ ያደረገ የለም!! ሙቀት መለካት በየትኛውም መመዘኛ ምርመራ ሊባል አይችልም  !!
***
የሳንባ ቆልፍ(ኮሮና ቫይረስ)ን ቤት ለቤት ለማዳረስ ካልሆነ በቀር ቤት ለቤት የሚባል ህክምና እስካሁን የትም ሃገር አልተጀመረም። ግምባር ላይ ሙቀት መለኪያ ደግኖ የሙቀት መጠን መለካት እና የሳንባ ቆልፍ(የኮሮና ቫይረስ) ምርመራ ምንም ግንኙነት የላቸውም። #በድሬዳዋ እና #በአዲስ አበባ የታሰበው የቤት ለቤት ምርመራ ሰዎችን በብዛት ለቫይረሱ ተጋላጭ ያደርግ እንደሆን እንጅ ከምርመራ ጋር ምንም አይቆራኝም።  ግምባራቸው ላይ እኮ ሙቀት እየለኩ የለባችሁም ያሏቸው ተጓዦች ናቸው አሁን ከማህበረሰቡ ውስጥ ኮሮና ተያዙ እያሉ መልሰው የሚያወጧቸው። የሰውነት ሙቀቱ ከፍተኛ የሆነን ሰው ሁሉ ወደ ማግለያ ጣቢያ መውሰድም ቫይረሱን ያስፋፋል እንጅ አይቀንሰውም። የሰውነት ሙቀት የሚጨምረው በኮሮና ቫይረስ ብቻ አይደለም። ቤት ለቤት የሚባለው አሰራር የሳንባ ቆልፍን ቤት ለቤት የሚያሰራጭ አደገኛ አሰራር ነው። የቤት ለቤት የሚባል ህክምና እንሰጣለን የሚሉት ሰዎች ስራ ካጡ አርፈው በቤታቸው እንደሌላው ሰው ቢቀመጡ የተሻለ ነው። ለሳንባ ቆልፍ የቤት ለቤት የሚባል ህክምና የለም! በቤቱ አርፎ የተቀመጠን ሰው ለመበከል በየቤቱ አትሂዱ!!!
በእርዳታ ያገኘችው መቶ ሽ የማይሞላ የሳንባ ቆልፍ መመርመሪያ ያላት ሃገር ድሬዳዋን እንኳ ብንተወው ከ3ሚሊዮን ህዝብ በላይ በሚኖርበት የአዲስ አበባ ከተማ ቤት ለቤት ምርመራ ላድርግ ስትል ውጤቱ ሳይሆን አጀማመሩ ራሱ ትክክለኛ አለመሆኑን መረዳት ይቻላል። የዚህ አሰራር ክሽፈት የሚንጸባረቀው ትክክለኛ መሰረት ላይ የተጣለ ጅማሮ ስለሌለው ብቻ ሳይሆን ይህንኑ ፉርሽ አካሄድም ቢሆን ከግብ የሚያደርስ በቂ መመርመሪያ ኪት፣በቂ የሰው ሃይል እና ላብራቶሪዎች አለመኖሩ ነው። ይህ ሁሉ ደግሞ አሁን ባለው አቅም ለኢትዮጵያ ተምኔታዊ ነው።እንደዚያ ለማድረግ ላደጉት ሃገራት ራስ ምታት ሆኗል።  የኢትዮጵያን አቅም እና ነባራዊ ሁኔታ ከግምት ውስጥ ስናስገባው ብቻ ሳይሆን አቅም ቢኖራትም እንኳ የቤት ለቤት የሚባለው ህክምና ምንም ትርጉም አይሰጥም።  እስኪ ይህን ቀልድ ተውትና በሆስፒታል የሚመጡትን ሰዎች በአግባቡ ህክምና ስጧቸው። ይህ ማለት የሚመጣውን ሁሉ ትኩሳት አለብህ እያሉ መያዝ አይደለም። ይህ ህክምና አይደለም። ኮሮና ቫይረስ እንዳለበት በምርመራ ሳታረጋግጡ ሰዎችን ሁሉ በማግለያ ጣቢያ ማስቀመጥ በሽታውን ካለበት ወደሌለበት ሰው ያስፋፋል። ትኩሳት የኮሮና ቫይረስ አንድ ምልክት ቢሆንም በሁሉም ታማሚዎች ላይታይ እንደሚችልም መረዳት ያስፈልጋል። ስለዚህ የቤት ለቤት ህክምና የሚባለውን ነገር በመተው እና ይህን ከሚያደርጉ ጋር ባለመተባበር ራሳችንን እና የምንወዳቸውን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ፤ ስርጭቱንም እንግታ!!!
Filed in: Amharic