>
7:17 pm - Tuesday June 6, 2023

ከኮሮና ጋር የነበረን የ2 ሳምንት የዘለቀ አስጨናቂ ቆይታ!!! (ዘውዱ መልካሙ)

ከኮሮና ጋር የነበረን የ2 ሳምንት የዘለቀ አስጨናቂ ቆይታ!!!

 

ዘውዱ መልካሙ
ማስታወሻ፤ ይህንን ልምድ ለማካፈል የወሰንኩት ማንንም ለማስፈራራት ሳይሆን ምናልባት የኔ ተሞክሮ ለሌሎች ወገኖችም ይጠቅማል በሚል ነው።
በፈረንጆች አቆጣጠር መጋቢት 20 ነበር ጎሮሮየን የመጠዝጠዝና አልፎ አልፎ የማስነጠስ ስሜት የተሰማኝ። ይህ ስሜት እየተሰማኝ ከ7 ቀን በኋላ በመጋቢት 27 አርብ ቀን ተሰምቶኝ የማያውቅ ከፍተኛ የሆነ የሚያቃጥል ትኩሳትና የድካም ስሜት ይሰማኝ ጀመር። ቅዳሜና እሁድ ይተወኛል ብየ ብጠብቅም ሊሻለኝ አልቻለም። በዚሁ ቀጥሎ ማክሰኞ የሆድ ህመምና ማስቀመጥ ጀምሮኝ ለተከታታይ 3 ቀናት ሰነበተብኝና አርብ አቆመ። 2 ሌሊት ሀይቅ ውስጥ የገባሁ ያክል ከፍተኛ የሆነ ላብ ነበረብኝ። አብዛኛውን ጊዜ ራስ ምታት ነበረብኝ። ደረቴ ላይ መግለጽ የማልችለው ከባድ ሸክም ነበረብኝ፤ አሁንም በተወሰነ መልኩ ይሰማኛል። እነዚህ ምልክቶች ሌላ 3 ጓደኞቼ ጋር በተመሳሳይ ሰዓት ነበሩ።
ምልክቶቹ እየጠነከሩብኝ ሲመጡ ዶክተሬ ጋር ደወልኩ። ጉሮሮዬን የመጠዝጠዝ፣ የትኩሳት ስሜት፣ የሆድ ህመምና ተቅማጥ፣ ራስ ህመም፣ ከፍተኛ የሆነ የድካም ስሜትና አልፎ አልፎ የማስታወክ ስሜት እንዳለብኝ ነገርኩት። አስከትዬም መመርመር እፈልጋለሁ አልኩት። ዶክተሩም እነዚህ ስሜቶች የኮሮና በሽታ ቀላል ምልክቶች ( mild symptoms) ስለሆኑ ምርምራ አያስፈልግም። 80% የሚሆኑ ታማሚዎች ቤት ሆነው ካለምንም የህክምና ርዳታ ነው የሚዲኑት ብሎ ለማረጋጋት ሞከረ። ነገር ግን የመተንፈስ ችግር ካጋጠመህ ብቻ የአስቸኳይ ጊዜ ስልክ ደውል። ከቤት የትም ሳትወጣ ራስህን ተንከባከብ። Stay at home and treat yourself. የቫይታሚን ሲና ዲ ምግቦችን አዘውትረህ ተመገብ ብሎኝ ተሰነባበትን።
ከዛ አንድ የቅርብ ወዳጅ ከሆነ የሚዴዲካል ዶክተር ጋር ደውዬ ነገርኩት። እሱም ራሱ ነው አለኝ። ድጋሚ እንዳይዝህ ቤት ውስጥ የምትጠቀማቸውን እቃዎች በደምብ አጽዳቸው አለኝ።
ይህ ሁሉ ሲሆን ለተወሰኑ ቀናት ጉሮሮየን የማፈን ስሜት እየተሰማኝ ስለነበር እንቅልፍ በአይኔ ሳይዞር ሰነበተ። ከቤት ሳልወጣ ለ14 ቀናት ቆይቻለሁ።
እንዴት እንደያዘኝ እስካሁን የማውቀው ነገር የለም። ምናልባት ሱፐርማርኬት ውስጥ ሊሆን ይችላል ብየ ገምቻለሁ።
ካለምንም ህክምና ርዳታ ያደረኳቸው ነገሮች፤
ዋናውና የመጀመሪያው ጸሎት ነበር።
ከፍተኛ የሆነ ውኃ እጠጣ ነበር። በተለይ ትኩሳቱንና የራስ ህመሙን የሚያስታግስልኝ ውኃው ነበር።
ነጭ ሽንኩርት፣ ዝንጅብል፣ ማርና ሎሚ እየቀላቀልኩ አፍልቸ እጠጣ ነበር።
ፍራፍሬ ማለትም ብርቱካን፣ ሙዝና የመሳሰሉትን አብዝቸ ተጠቅሚያለሁ።
የቫይታሚን ሲና ሌሎች ይህን በሽታ ይከላከላሉ የተባሉትን ወስጃለሁ።
ሀኪም ቤት ሳልሄድ አሁን ደረቴ ላይ ከሚሰማኝ ቀለል ያለ ሽከም መሰል ነገር ውጭ ወደ ድሮው ጤንነቴ እንደምታዩኝ መመለስ ችያለሁ።
የመጨረሻ መልዕክት፤
ይህ የኮሮና በሽታ ሌላ ተደራራቢ በሽታ ልክ እንደ ልብ ድካም፣ ደም ግፊት፣ ኤድስና የመሳሰሉት የሌለበት ሙሉ ጤነኛ የሆነን ሰው አጥቅቶ የመግደል ዕድሉ ዝቅተኛ ነው። ስለሆነም በተለይም ወጣቶችና ሙሉ ጤነኛ የሆናችሁ ይህ በሽታ እናንተን የማጥቃት እድሉ ዝቅተኛ ቢሆንም ቤት ውስጥ ሽማግሌና ተደራቢ በሽታ ያለበት ሰው ካለ ከእናንተ ወደዛ ሰው እንዳይዛመት ጥንቃቄ ብታደርጉ መልካም ነው እላለሁ።
Filed in: Amharic