ሞት ኢትዮጵያን እንዲያልፍ አሁንም ወደ እግዚአብሔር እንመለስ!!!”
ዘመድኩን በቀለ
* የኢትዮጵያ ን ሰማይ ሞልቶ የዋለው የምህረት ቃል ኪዳን ምልክት (ቀስተ ዳመና) ፈጣሪያችን አምላካችን ጾማችንን፣ ጸሎታችንን፣ ሱባኤያችንን፣ ምህላችንን፣ ስግደታችንን ለመቀበሉ ማሳያ ነው!!!“
• ኮሮና በአባቶች ጸሎት ተጠርንፎ ታስሯል። ዓለም እንደጠበቀን አልሆነም። ሞት ሆይ ኢትዮጵያን እለፍ።
* ~ ስለ ሌሎች ሃይማኖት አያገባኝም። እኔ ስለራሴ ሃይማኖት ነው የምጽፈው። መልእክቱም ለእናንተ ለተዋሕዶ ልጆች ነው። አንብቡት ተጠቀሙበት።
•••
የተወሰነ ጊዜ አለንና በቀረችን ጥቂት ደቂቃም ቢሆን ንስሐ መግባትን አንተው። በቤታችን የጀመርነውን የማኅበር ጸሎት አናቋርጥ። የቀማን እንመልስ፣ የበደልን እንካስ፣ ይቅር እንባባል። ማዕተባችንን አጥብቀን በወፍራሙ እንሰር። ቁንጣን አስኪይዘን አንመገብ። ቁርስ መብላት እንተው። ድሆችን እንጎብኝ። ተካፍለን እንብላ። ኅብረት ይኑረን። ወደ ሃይማኖት እንመለስ።
እሺ ብትሉ ለእኔም ብትታዘዙ፥ የምድርን በረከት ትበላላችሁ፤ እንቢ ብትሉ ግን ብታምፁም፥ ሰይፍ ይበላችኋል፤ የእግዚአብሔር አፍ ይህን ተናግሮአልና። ፍርድ ሞልቶባት የነበረው የታመነችይቱ ከተማ እንዴት ጋለሞታ ሆነች! ጽድቅ አድሮባት ነበር፥ አሁን ግን ገዳዮች አሉባት።
ብርሽ ወደ ዝገት ተለወጠ፤ የወይን ጠጅሽ ከውኃ ጋር ተደባለቀ። አለቆችሽ ዓመፀኞችና የሌቦች ባልንጀሮች ሆኑ፤ ሁሉ ጉቦ ይወድዳሉ፥ ዋጋም ለማግኘት ይሮጣሉ፤ ለድሀ አደጉ አይፈርዱም፥ የመበለቲቱም ሙግት ወደ እነርሱ አይደርስም።… ጽዮን በፍርድ ከእርስዋም የሚመለሱ በጽድቅ ይድናሉ።
በደለኞችና ኃጢአተኞች ግን በአንድነት ይሰበራሉ፥ እግዚአብሔርንም የሚተዉ ይጠፋሉ። ኢሳ 1፥ 18-28
• ይሄ ዛሬ በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ የታየው የምህረት ምልክት ነው። አዎ ኢትዮጵያ የድንግል ማርያም የአስራት ሀገሩ ናት። በዓለም አዘንድ የተናቀች በእግዚአብሔር ዘንድ የከበረች ናት። 24/7 በአምላኳ ፊት የምትንበረከክ ናት። ይሄ ዛሬ በኢትዮጵያ ሰማይ የታየው ምልክት አግዚአብሔር ለኖኅ አባታችን ቃል በገባ ጊዜ የሰጠው የቃል ኪዳን ምልክት ነው። ግብረ ሰዶማውያን የትናንት ወዲያ አርማችን ሳይሉ በፊት ጥንት እግዚአብሔር ለኖኅ ቃልኪዳን የገባበት የቃል ኪዳኑ ሰነድ የታሰረበት ማኅተም ነው።
♥
እግዚአብሔርም ለኖኅና ለልጆቹ እንዲህ ብሎ ተናገረ። ዘፍ 9፥8
✝እግዚአብሔርም አለ። በእኔና በእናንተ መካከል፥ ከእናንተም ጋር ባለው በሕያው ነፍስ ሁሉ መካከል፥ ለዘላለም የማደርገው የቃል ኪዳን ምልክት ይህ ነው፤ ዘፍ 9፥12
✝ ቀስቴን በደመና አድርጌአለሁ፥ የቃል ኪዳኑም ምልክት በእኔና በምድር መካከል ይሆናል። ዘፍ 9፥ 13
✝ በምድር ላይ ደመናን በጋረድሁ ጊዜ ቀስቲቱ በደመናው ትታያለች፤ ዘፍ 9፥14
✝ ቀስቲቱም በደመና ትሆናለች፤ በእኔና በምድር ላይ በሚኖር ሥጋ ባለው በሕያው ነፍስ ሁሉ መካከል ያለውን የዘላለም ቃል ኪዳን ለማሰብ አያታለሁ። ዘፍ 9፥16
••• “ ሞት ሆይ ኢትዮጵያን እለፍ ”
እኛን ከእግዚአብሔር በቀር የሚደርስልን፣ የሚረዳንም የለም እና ወደ ጥንቱ ማንነታችን እንመለስ።
•••
ሻሎም ! ሰላም !
ሚያዝያ 8/2012 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።