ከኦነጋዊነት ባሻገር !!
ሀብታሙ አያሌው
የብሔርተኝነት ጠርዝ ላይ የቆሙ የኦሮሞ ብሔርተኞች ፖለቲካቸውን የሚጀምሩት ኢዮጵያን በመስራት ጉልህ ታሪክ ያላቸውን ከኦሮሞ ብሔረሰብ የተወለዱ ጀግኖች በመካድና በማዋረድ ነው። ብሔር የሚል መደበቂያ ጫካ ተጠቅመው ስልጣን በኮታ ካልተቀበሉ በቀር እንደ እንደ ጀግኖቹ የኦሮሞ ልጆች ስማቸውን በጉልህ ማድመቅ እንደማይቻላቸው ያውቃሉ።
ህወሓት መጣች የትግራይ ህዝብ በአገር ግንባታ ሂደት የነበረውን ደማቅ ታሪክ ሁሉ ክዳ “አዲስ ኢትዮጵያ እንገነባለን አለች” እንደ ብርሃነ መስቀል ያሉ ዋልታረገጥ ብሔርተኞችም “አዲስ ኢትዮጵያ እንገነባለን” ባዮች ናቸው።
ነገ ደግሞ ሌላው ጠርዘኛ ሲመጣ “ሌላ አዲስ ኢትዮጵያ እገነባለሁ” ይልሃል።
ኢትዮጵያ የመጣ ተረኛ ሁሉ እያፈረሰ የሚሰራት በድቡሽት ላይ የተገነባች ጎጆ አይደለችም። ታሪክ በደረስክበት ዘመን የድርሻህን እንድትሰራ እንጂ ወደኋላ ተጣመህ ያልነበርክበትን ዘመን እንድታጠፋው አይፈቅድልህም። ታሪክ ብትወድደውም ብትጠላውም ያው ታሪክ ነው።
የብርሃነ መስቀል ከንቱ ሃሳብ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ገበያ ዋጋ አጥቶ የሚያስለቅሰው ” እኔ ኦሮሞ ነኝ ስለዚህ ያለፈውን ሁሉ አጥፍቼ አዲስ ታሪክ ልፃፍ” የኦሮሞ ልጆች የፃፉትን ታሪክ ልደምስሰው እያለ መሆኑን አለመገንዘቡ ነው ። የአበበ ሰኚ ልጅ ብርሃነ መስቀል ፤ የጥንቶቹ የኦሮሞ እናቶች ያፈሯቸው ዕልፍ የኢትዮጵያ ምልክቶችን ሁሉ መካድና የሰሯትን አገር ማፍረስ እንዲሁ በቀላሉ የሚሳካ እንዳልሆነ ዛሬም አልተረዳም።
ብርሃነ መስቀል የበታችተት ከወለደው ኦነጋዊ ፖለቲካ መላቀቅ ተስኖት ዛሬም እዛው እየዳከረ ነው። ኢትዮጵያን ለመገንባትና ጠብቆ ለማቆየት የተከሰከሰ አጥንት የፈሰሰን ደም እረግጦና አራክሶ ፖለቲካ ለመስራት “ኦሮሞትን በኦነጋዊ አስተሳሰብ የመስፈር ፖለቲካ ጀግና ወልደው ለአገር ከገበሩ የኦሮሞ እናቶች የሚያላትም የትም የማያደርስ ከንቱ የከንቱ ከንቱ ፖለቲካ ነው…የኦሮሞ ልጆችን አኩሪ ታሪክና ተጋድሎ ክዶ እና አራክሶ ለኦሮሞ መብት እታገላለሁ የሚል የፌዝና የስላቅ ፖለቲካ የትም ሊያደርስ አይችልም።
ብርሃነ መስቀል አበበ ሰኚ ተስፋህን ቁረጥ በጀግኖች ደም የቆየች አገር በዋልታ ረገጥ ብሔርተኞች አትፈርስም። ኦሮሞነትን በኦነጋዊነት መስፈሪያ መለካት ካልተውክ ከኢትዮጵያዊነት ጋር ስትላተም አንተው እራስህ ትፈርሳለህ እንጂ የምታፈርሰው በአሸዋ ላይ የተሰራ ቤት የለም።
⇐ ከታሪክ ማህደር
*************
ብ/ጀ አሰፋ ሞሲሳ በስተግራ
_
ብ/ጀ ተመሥገን ገመቹ በስተቀኝ /ሐረር በ 1968 ዓ/ም