>

‹ለውጥ ለእኛ የ"ሕገ-መንግሥቱ" መለወጥ ፤ ለውጥ ለእነርሱ የሕገ-መንግሥቱ መተግበር!" እንዴት እንግባባ??? (ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ)

‹ለውጥ ለእኛ የ”ሕገ-መንግሥቱ” መለወጥ ፤

ለውጥ ለእነርሱ የሕገ-መንግሥቱ መተግበር!” እንዴት እንግባባ???

ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ
ለውጥ ሥርዓትን በመቀየር ወይም በአዲስ በመተካት እንጅ ሰዎችን በሌሎች ሰዎች ወይም ደግሞ አንድን የፖለቲካ ማኅበር በሌላ በመተካት አይመጣም፤ አንዲህ ሆነ ማለት ደግሞ ያው የተለመደው “ጉልቻ ቢለዋወጥ ወጥ አያጣፍጥም” ከሚለው ዛሬም አለመውጣታችን ያሳያል።
የሥርዓት ለውጥ የሚጀምረው የሥርዓቱ ቁንጮ የሆነውን ሕገመንግሥት ከመቀየር እንደሆነም ጠቁመዋል።
ሕገ-መንግሥታዊ ሽፋን የተሰጠው የህውሐት የከፋፍለህ ግዛው ትርክትም ፍሬያማነቱን አጠናክሮ ቀጥሏል ፡፡
ሚሊዮኖች በአገራቸው ላይ ባይተዋር ሆነው እንዲፈናቀሉ በማድረግም ኦነጋውያኑ ሕገ-መንግሥቱን በሚገባ ሥራ ላይ ማዋል ጀምረዋል ። ዛሬ ላይ ይህ ወንጀል ህገ መንግስታዊ ከለላ ቢያገኝም በታሪክ ማስጠየቁ አይቀርም።
 ምን አልባትም ኢትዮጵያን እንደ ሶሪያ የሚያደርገውንና የኦነጋውያኑም ፍፃሜ የሚሆነውን፣ በታሪካዊ ዳራውም በነባራዊ ሁኔታውም ፍፁም ተቀባይነት የሌለው ሲሉ የገለፁትን አዲስ አበባን የኦሮሚያ የማድረግ ቅዠትንም ኦነጋውያኑ የሚመሩት ኦዴፓ በመግለጫም ጭምር በማስደገፍ ታሪክ የማይረሳው ጠባሳውን እያስቀመጠ ይገኛል፡፡
ስርዓቱ አድሎአዊ፣ ነገን የረሳና ከስሌት ይልቅ በስሜት የሚጋልብ  መሆኑን ነው ለመታዘብ የቻልኩት።
Filed in: Amharic