ክፍል ሶስት
(ሙክታሮቪች)
ጋዜጠኛ:
ክቡር ፕሬዝዳንት በክልሉ በቅርቡ የተፈጠሩ አለመረጋጋቶችን ተከትሎ እስር ተካሂዷል። በክልሉ ስለተፈጠረው ጉዳይ ሊነግሩን ይችላሉ? በተለይ የእርስዎ የፕሮቶኮል ሀላፊ የነበሩት አቶ አብዱል ቃድርን አስረውታል? ምክንያቱ ምንድነው?
ሙስጠፋ:
እኔ በግል ፀብ አላስርኩትም። የታሰረው በህግ ጥሰት ምክንያት ነው። ሀገር ነው የምንመራው። ሀገር በህግ እያስተዳደርን ነው። ህግ ሲጣስ ህጉ እኛንም እንድናስር ያስገድደናል። ሆኖም …..
ጋዜጠኛ: (ንግግራቸው አቋርጦ)
ምን ጥፋት አገኛችሁበት? የትኛውን ህግ እንደጣሰ ይህን ፕሮግራም በቀጥታ እየተከታተሉ ላሉት የተከበሩ ተመልካቾቻችን ሊነግሩ ይችላሉ?
ሙስጠፋ:
አይ አልናገርም
ጋዜጠኛ:
ክቡር ፕሬዝዳንት ለምን አይነግሩንም?
ሙስጠፋ:
የማልናገረው ለተከሳሹ መብት ስል ነው። የተከሳሹን የህግ ጥሰት በአደባባይ እኔ መሪ ሆኜ ከተናገርኩ የፍትህ ስርዓቱ ላይ አላስፈላጊ ጫና እናም አድሎ እንዳያመጣ ስጋት አለኝ። ማንም ሰው በህግ ፊት ንፁህ እንደሆነ የህግ ግምት አለ። በህገመንግስት የተቀመጠ ነው። እዚህ ያጠፋውን ብዘረዝር እራሱን ለመከላከል ከፍተኛ ጫና ሊኖርበት ነው። ህግ እየጣስኩ ህግ አስከብራለሁ የማለት ሞራል አጣለሁ።
ስለዚህ የማልናገረው ለተከሳሹ መብት፣ ፍትህ እና ደህንነት ስል ነው።
ጋዜጠኛ:
ምንም ጥፋት ሳይኖርበት አስረውት ቢሆንስ
ሙስጠፋ:
በፍርድቤት ስራ ጣልቃ መግባት ስለሌለብኝ ነው የህግ ጥሰቱን የማልነግርህ። ጠቅለል አድርጌ የምነግርህ እኛ ህግ ጥሷል ብለን በህግ ጥሰት ጠይቀነዋል። ህግ መጣስ አለመጣሱን ማጣራት ያለበት ፍርድቤት ነው። ያሻውን ያህል ምርጥ ምርጥ ጠበቆችን አሰልፎ መሟገት መብት አለው። እኛም አቃቤ ህግ መድበን እንሟገታለን። አስፈላጊ መስሎ ከታየን የችሎቱን ሂደት ለህዝብ በቀጥታ ልናስተላልፍም እንችላለን። ጋዜጠኛም ፍርድቤት ገብቶ ሊመለከት፣ በነፃነት ሊዘግብ ይችላል።
ጋዜጠኛ:
ህግ ያልጣሰ ከሆነስ
ሙስጠፋ:
ህግማ ጥሷል አልኩህ እኮ
ጋዜጠኛ:
የቱን ህግ
ሙስጠፋ:
በቅርቡ የተከሰተው ፖለቲካዊ አለመረጋጋትን ተያይዞ አሁን እዚህ በገለፅኩልህ ምክንያት የማልዘረዝረውን የህግ ጥሰት ፈፅሟል ብለን እናምናለን። ፍርድቤት ደግሞ የራሱን ፍርድ ይሰጣል። የችሎቱን ሂደት ቤተሰቡም ሆነ ፍላጎት ያለው ሰው መታደም ይችላል። በእስርቤት በህግ ለተጠየቁ ሰዎች በህገመንግስቱ የተረጋገጡለት መብቶች እንዳይነኩበት እኔው እራሴ ነኝ ትዕዛዝ ያስተላለፍኩት። ትዕዛዜ ተግባራዊ ስለመሆኑም ተከታትዬ እያጣራሁ ነው። እንደ መሪ ማድረግ ያለብኝ ይህን ነው።
ጋዜጠኛ:
የተፈጠረው እና እሱ በግል ተሳትፎበታል ያሉት ጉዳይ ምንድነው?
ሙስጠፋ:
የፖለቲካ አለመረጋጋት አልያም የፖለቲካ ክራይስስ ልንለው እንችላለን
ጋዜጠኛ:
እንዴት ያለ የፖለቲካ ክራይስስ?
ሙስጠፋ: (ፈገግ እያለ)
የፖለቲካ ክራይሲስ ብዬ ብጠቅሰው ነው እኔ የምመርጠው
ጋዜጠኛ:
የፖለቲካ ክራይሲስ ሲባል እንግዲህ መንግስት ለመገልበጥ ማሴር ሊሆን ይችላል። የፓርላማውን ስራ በህገወጥ መልኩ ማደናቀፍ እና ለህገወጥ ተግባር መመሳጠር ሊሆን ይችላል፣ አማፂ ማደራጀት ሊሆን ይችላል፣ እነዚህን የመሳሰሉት ሊሆኑ ይችላል። ከጠቀስኩት አንዱን መቼም ፈፅሞ ሊሆን ይችላል ብላችሁ ነው የምታምኑት። አይደለም እንዴ ክቡር ፕሬዝዳንት? እስቲ አሁን ከጠቀስኳቸው የትኛው ሊሆን ይችላል?
ሙስጠፋ:
አንተ የመገመት መብት አለህ። እኔ ግን የፖለቲካ አለመረጋጋት ወይም ፖለቲካል ክራይሲስ በሚለው አገላለፅ እፀናለሁ
ጋዜጠኛ:
በክልሉ የተሞከረው መፈንቅለ መንግስት ማለትዎ ነው?
ሙስጠፋ:
የፖለቲካ ክራይሲስ ለመፍጠር የታሰበ ሴራ ነው ብዬ የማስቀምጠው
ጋዜጠኛ:
የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ አልነበረም እያሉኝ ነው?
ሙስጠፋ:
የፖለቲካ አለመረጋጋት እና ነውጥ ለመፍጠር አይነት ተደርጎ የሚወሰድ ነው
ጋዜጠኛ:
ምንም ጥፋት ሳይኖርበት አስረውት ቢሆንስ
ሙስጠፋ:
በፍርድቤት ስራ ጣልቃ መግባት ስለሌለብኝ ነው የህግ ጥሰቱን የማልነግርህ። ጠቅለል አድርጌ የምነግርህ እኛ ህግ ጥሷል ብለን በህግ ጥሰት ጠይቀነዋል። ቀሪው የፍትህ ስርአታችን ስራ ነው። ፍትሀዊ እንዲሆን የሚቻለውን ብቻ ሰይሆን በህግ የተቀመጠውን መብቱን ሁሉ እናስጠብቀለን።
ጋዜጠኛ:
መልካም። ሌሎች የታሰሩም አሉ። እነ ማህዲ ሀሰን ገፍዲድ የሚባል ሰው። ከደር ኦላድ የሚባል ሰው። እነዚህስ ምን አድርገው ነው?
ኸረ ብዙ ነገር የማነሳልዎት አለ።
ለምሳሌ እርስዎ ያቀረቡትን የደም ባንክ ተጠናቅቋል እወጃ፣ የጤና ሚኒስትሩ አለመጠናቀቁን አስተውቀዋል፣ ተናብባችሁ አትሰሩ ማለት ነው? የጂግጂጋ ከተማ ለህይወት መሰረታዊ የሆነውን ውሃ የተነፈገች ከተማ ናት። ውሃ የለም።
የፀጥታ ዘርፍ ሀለፊውን ለምን በሌላ ተኩ? ብዙ ጥያቄ ማንሳት ይቸላል።
እንደውም እርስዎ አክቲቪስት እንጂ ሀገር መምራት አይችሉም ይበለሉ።
ክቡር ፕሬዝደንት እውነቱን ለሶማሌ ህዝብ እንዲያሰውቁ እጠይቆታለሁ። ይመልሱልኝ!
ሙስጠፋ: (አየር ስቦ አስወጣ። ፈገግ አለ። በማዘን ጭንቅለቱን ከወዘወዘ በኋላ)
ስማ ማነህ አብዲልአፊዝ፣ እንዲህ ተብሎ አይጠየቅም
(ሙስጠፌ፣ የተቆጣ ይመስላል ……)
ክፍል አንድና ሁለት⇓