>

ጉድ በል ጎንደር ማለት ይሄኔ ነው! (ቅዱስ ማህሉ)

ጉድ በል ጎንደር ማለት ይሄኔ ነው!

ቅዱስ ማህሉ
የዓለም ጤና ድርጅት፣ የቻይናው ውሃን የስነ ቫይረስ ተቋም፣የቢል ጌት ፋውንዴሽን ሃክ ተደርገው በርካታ ሚስጥራዊ ዶክመንቶች፣ ኢሜል እና ፓስወር ሳይቀር ተሰርቀዋል እየተባለ ነው። ተሰረቁ ከተባሉት ሚስጥራዊ ዶክመንቶች ውስጥ በትዊተር ላይ የተለጠፉት ጥቂቶቾ ከኢንተርኔት ላይ የተነሱ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ የኮሮና ቫይረስ(ሳንባ ቆልፍ) ቀደም ሲል ተከስቶ የነበረው ሳርስ እና የኤችአይቪ ቫይረስን በመቀላቀል በውሃን ኢንስቲቱት ኦፍ ቫይሮሎጂ ተቀምሮ እንደተሰራ እና እንዴት የመጀመሪያውን ቫይረስ ወደ ህዝብ የማዛመት ኦፕሬሽን እንደተከናወነ የሚያሳይ ነው።
የሳርስ በሽታ አማጭ ቫይረስ ኮሮና ቫይረስ ሲሆን የጄነቲክ መዋቅሩ ካሁኑ የኮሮና ቫይረስ ልዩነት ያለው ሲሆን በስርጭት ፍጥነት ዘገምተኛ በገዳይነት ግን ካሁኑ ኮቪድ 19 የሚበልጥ እንደነበር ተገልጿል።ሃክ የተደረጉት ዶክመንቶችን በባለሙያ እየተመረመሩ እውነቱን ለማግኘት እና ለዓለም ለማሳወቅ ጥቅም ላይ እንደሚውሉ ትዊተር ላይ ከተደረጉ ምልልሶች ለመረዳት ይቻላል።
 የሆኖ ሆኖ እስካሁን በጉዳዩ ላይ ከሶስቱ ድርጅቶች በይፋ የተሰጠ ምንም ዓይነት መግለጫ ወይም ማስተባበያ ባይኖርም ዋሽንግተን ፖስትግን ከ25ሽ በላይ ኢሜሎች እና ፓስወርዶች በአካውንት ጠላፊዎች ከድርጅቶቹ ተሰረቁ ስለተባሉት ኢሜሎች እና ፓስወርዶች (አብዛኞቹ አሁን ትዊተር አጥፍቷቸዋል) ዘግቧል። በሌላ በኩል ስም ጥር ኢንተርፕርነሮች፣ ኢንቨስተሮች እና የቴክኖሎጅ ሰዎች ደግሞ ድርጅቶቹ ሃክ መደረጋቸው በትዊተራቸው ላይ እንደምታዩት ሸር አድርገውታል።
የዋሽንግተን ፖስት ዘገባ ይሄው https://wapo.st/2xCXyul
Filed in: Amharic