>

አለማችንን የኮረና ቫይረስ እንዴት እያደረጋት ነው ?አጫጭር መረጃዎች፦ (ሳምሶም ጌታቸው)

አለማችንን የኮረና ቫይረስ እንዴት እያደረጋት ነው ?አጫጭር መረጃዎች፦

ሳምሶም ጌታቸው
ኢትዮጵያ በ24 _ሰአት ውስጥ  በተወሰዱ 965 ናሙናዎች በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች አለመኖራቸው ተረጋግጧል ። አዲስ የሟች ቅጥር ያልተመዘገበ ሲሆን 116  ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
በጁቡቲ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 974 ሲደርስ አጠቃላይ በቫይረሱ የሞቱ ሰዎች 2 ሲሆኑ ከ183 በላይ ደግሞ ከቫይረሱ ማገገምቸው ተገልጿል።
 
በኬንያም በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 18 ሲደርስ አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙት ደግሞ 303 ደርሰዋል። 83 ደግሞ ከበሽታው ማገገም ችለዋል።
 
– በሳውዲ አረቢያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 12,772 ደርሷል። ባለፉት 24 ሰዓት ብቻ 1,141 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። በሌላ በኩል ተጨማሪ 5 ሰዎች መሞታቸውን ተከትሎ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 114 ደርሷል።
በጀርመን 800 ካሬ ሜትር ስፋት ያላቸው የንግድ ተቋማት ፣ የመኪና እና ብስክሌት ሱቆችና የመጻሕፍት መደብሮች እንደገና መክፈት ጀምረዋል። ምግብ ቤቶችና የመዝናኛ ስፍራዎች አሁንም ላልተወሰነ ጊዜ ዝግ እንደሆኑ ይቆያሉ።
በፈረንሳይ ተጨማሪ 544 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል። አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርም 21,340 ደርሷል።
በፓኪስታን በረመዳን የፆም ወቅት መስጂዶች ተከፍተው ይቆያሉ። ነገር ግን በመስጂዶች ውስጥ የሚከናወኑ ሃይማኖታዊ ስርዓቶች አካላዊ ርቀትን (2 ሜትር ርቀት) በጠበቀ መልኩ እንዲከናወን ማሳሳቢያ ተሰጥቷል።
– የፓኪስታኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ከሃን በተደረገላቸው ምርመራ ከኮሮና ቫይረስ ነፃ መሆናቸው ተረጋግጧል።
በጣልያን ባለፉት 24 ሰዓት 437 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል። ተጨማሪ 3,370 ሰዎች በቫይረሱ ተይዟል።
በአሜሪካ በ24 _ሰአት ውስጥ 1700 ሰዎች መሞታቸው ታውቋል። ጠቅላላ የሟቾች ቁጥር ከ46,000 በልጧል። በሀገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ831,000 በልጧል።
በሩዋንዳ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች 154 ደርሰዋል። ባለፉት 24 ሰዓት 1,038 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 3 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
 
ቻይና በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ተጨማሪ 10 ሰዎችን ማግኘቷን አስታወቀች። የሀገሪቱ የጤና ሚኒስትር እንዳስታወቀው ከአስሩ ስድስቱ ከውጪ ሀገር የገቡ ናቸው ብሏል። ሆኖም በቫይረሱ የሞቱ ሰዎች ግን  አለመመዝገቡ ተገልጿል።
 
በኢንግላንድ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ተዘግተው የነበሩ ትምህርት ቤቶች በመጪው ሰኔ ወር  መልሰው ይከፈታሉ ተባለ።
በሀገሪቱ አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ133 ሺ ያለፈ ሲሆን ከ18 ሺ የሚበልጡ ሰዎች ደግሞ ህይወታቸው አልፏል።
በመላው ዓለም በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች 2,614,803 ደርሷል። 182,467 ሰዎች ሞተዋል። 714,319 ሰዎች አገግመው ከሆስፒታል ወጥተዋል።
Filed in: Amharic