>

ሙስጠፌና አብዲልሀፊዝ Hardtalk ክፍል አምስት (ሙክታሮቪች)

ሙስጠፌና አብዲልሀፊዝ Hardtalk

ክፍል አምስት
(ሙክታሮቪች)
ከዩኒቨርሳል ቲቪ ጋዜጠኛ አብዱልሀፊዝ ጋር ፕሬዝዳንት ሙስጠፌ ያደረጉትን ቃለምልልስ ከአንድ እስከ አራት ክፍል አቅርቤላችሁ ነበረ። ክፍል አምስት እነሆ!
ጋዜጠኛ:
ክቡር ፕሬዝዳንት በክልሉ ከፍተኛ የሆነ ሙስና እንደሚታይ ይነገራል። የስልጣን ክፍፍል ላይም የአንድ ቦታ ሰዎች ብቻ እንደተሰባሰባችሁ መረጃው ደርሶኛል። በኃላ በሰፊው ዘርዝሬ እጠይቆታለሁ። አሁን ግን አንድ ሳልዘነጋው መጠየቅ የምፈልገው የተፈናቃዮች ጉዳይን ነው።
ተፈናቃዮች ያሉበት ሁኔታ አስከፊ ነው። ምነው በልማት እቅዳችሁ ዘነጋችሁአቸው? አቅም አጥሯችሁ ነው ወይስ አንዳንዶች እንደሚወቅሷችሁ ስላልፈለጋችሁ?
ሙስጠፋ:
ተፈናቃዮችን በተመለከተ የሰራነው እና እየተሰራ ያለ ስራ አለ። በተለይም ቀጥታ ከኑሮአቸው ጋር የተያያዘ ስራዎች እየተሰሩ ነው። የትምህርት፣ የጤና እና የመሳሰሉ አስፈላጊና አንገብጋቢ ጉዳዮችን እየሰራን ነው።
አንዳንድ ጉዳዮች ከሩቅ መተቸት እና በርግጥም ስራውን ቀረብ ብሎ ውስብስብነቱን ተረድቶ ፌር የሆነ ምልከታ ሊኖረን ይገባል።
እኛ ስልጣን ከያዝን በኋላ በሰላም ላይ በሰራነው እልህ አስጨራሽ ስራ በኢትዮጵያ መፈናቀል ያልታየበት ክልል እኔ የማስተዳድረው ክልል አንዱና ምሳሌም ሊሆን የበቃም ነው። በዚህም የተፈናቀሉ የነበሩ እና አሁን የተረጋጋ ሰላማዊ ኑሮ የጀመሩ በርካቶች ናቸው። ይህም በተግባር በሚሰራ ስራ የሚገኝ ውጤት ነው።
እኔ እንግዲህ በአለማቀፍ ድርጅቶች ከተፈናቃይና የስደት ጉዳዮች ጋር የመስራት ልምድ አለኝ። በበርካታ ሀገራት የስራ ልምዴ በአመት ከስድስት ወር የተፈናቃይ ጉዳዮች ሁሉ ተፈትቶ ምቹ የሚሆንበት አለም የለም። ጊዜ ይፈልጋል። ፖለቲካውን ማረጋጋት ያስፈልጋል።
እንደውም እኛ ጋ ባሉት ተፈናቃዮች በአለማቀፍ ኢንዲኬተር ልኬት መሰረት ስናየው የተሻለ የሚባል ነው።
ወደ ቀኤአቸው መመለስ፣ ግጭት መፍታት፣ ባሉበት ቦታ የሚያስፈልጋቸው ነገሮች እንዲሟሉላቸው ማድረግ ያስፈልጋል።
ይህ ደግሞ ክልሉ ብቻውን ለመስራት የአቅም ችግር አለብን። የፌደራል መንግስት፣ የአለማቀፍ ድርጅቶች እርዳታ ያስፈልጋል። ተባብረን የሰራናቸው ስራዎች አሉ። መስራት ሲገባን ያልሰራናቸውም አሉ።
ጋዜጠኛ;
መልካም። አንዳንዶች በክልሉ የስልጣን ክፍፍል የርስዎ አስተዳደር የሚቀርቦትን ሰዎች ብቻ፣ ከአንድ አካባቢ፣ ማለትም እርስዎ ከተወለዱበት አካባቢ ብቻ ስልጣን ላይ እንደተቀመጡ ያማርራሉ። ስለዚህ ጉዳይ ምን ይላሉ?
ሙስጠፋ: (ሳቅ ብሎ)
ይህ አስተያየት አዲስ ነው ለእኔ። ካልክ አይቀር እኔ እንደውም የምከሰሰው ለተወለድክበት አካባቢ ሰው፣ ለሚቀርብህ ሰው ስልጣን አትሰጥም በሚል ነው። እኔ እስከማውቀው በስልጣን ክፍፍል ከሁሉ አከባቢ የተወጣጣ ፍትሃዊ እና ሚዛናዊ የስልጣን ክፍፍል ነው ያለው። ይህም ሊሆን የቻለው እኔ ጎጥና ቀበሌ ባለመመልከት በችሎታ ስለማምን ነው። ችሎታ ደግሞ አላህ የሰጠው ለሁሉ አካባቢ ላሉ ሰዎች ስለሆነ ሚዛኑን መጠበቁ ተፈጥሮአዊ ነው። ሆኖም ሚዛኑን እንዳይስት ከሁሉ አካባቢ ሰዎች እንዲኖሩ ጥረት እናደርጋለን።
ለምሳሌ ዋና ዋና የስልጣን ቦታ ከሚባሉት አምስቱን ብዘረዝርልህ፣ ምክትል ፕሬዝዳንታችን ከሲቲ ዞን ነው (ከድሬደዋ ዙሪያ እስከ አፋር አከባቢ ያለ ዞን ነው)
የፓርቲያችን ዋና ፀሀፊ አፍዴር ዞን ነው (ክልሉ ወደ ደቡብ ምስራቅ)
የክልሉ ሀፈጉባዔ ከሞያሌ አካባቢ ነው።
የክልሉ ከፍተኛ ፍርድቤት ዳዋ ዞን አከባቢ ነው።
የክልሉ ጄኔራል ኦዶተር ቶጎ ጫሌ አካባቢ ነው።
እንዲህ እየዘረዘርኩ ላስረዳ እችላለሁ። ለህዝቡ ምን ሰራችሁ በሚለው ብንመዘን ይሻላል። ማን ስልጣን ያዘ። ከየት አካባቢ። ከየትኛው ጎሳ፣ ከየትኛው ጎሳ ንዑስ ጎሳ እያልን ነው የማናድገው። በዚህ በኩል ችግር አለ እንባላለን። በዚህ በኩል ደግሞ ስልጣን እና የጠበበ ጎሰኝነትን እናራምዳለን። በየት በኩል እንደግ?
ጋዜጠኛ፣
ክቡር ፕሬዝዳንት የሚወቅስዎት ሰዎች እኮ “የማናድገው በከፍተኛ ደረጃ የህዝብ ገንዘብ እየተበላ ስለሆነ ነው” እያሉ ነው። ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ የርስዎ አስተዳደር በሙስና ተጨማልቋል ይባላል። መልስ አልዎት?
ሙስጠፋ:
እኔ እኮ የሚርመኝ እንዲህ መሰረተ ቢስ ወሬ የሚነዙ ሰዎች ናቸው። ማን እንደሆኑ ደግሞ አውቃለሁ። እነዚህ ሰዎች ከአብዲሌ ጋር በአይን ያወጣ ሙስና የተጨማለቁ፣ የሶማሌን ህዝብ ስጋና አጥንት ሳይቀራቸው ግጠው የጨረሱ፣ የለመዱትን ሌብነት በእኔ አስተዳደር ጊዜ እየተከታተልኩ ቀድሞ የሚበሉትን ሙስና ስላስቀረሁባቸው ነው የሚያላዝኑት።
ይገርማል። ለለውጡ ከበጀ ይሁን እስቲ ብለን ዝም ብንላቸውም ሊያርፉ አለመቻላቸው ያሳፍራል። በነፃነት እየሰሩ ነው። ዘርፈው በገነቡበት ትልልቅ ሆቴልና ቤቶቻቸው ዘና ብለው እየኖሩ ነው። ግዴለም ይስሩ። ይኑሩ። ሆኖም ትናንት የለመዱትን የህዝብ ሀብት ዘርፎ መብላት እንደመንግስታዊ የተለመደ ስራ ስለሚቆጥሩት፣ እነሱ ካልዘረፉ ሌላው እየዘረፈ ማለት ነው እያሉ ያለማስረጃ ወሬ ብቻ ያወራሉ። በአማርኛ ሌባ እናት ልጇን አታምንም እንደሚባለው ነው።
እየውልህ የነውራቸው መጠንን ልንገርህ።
እኛ በዚህ በአንድ አመት ከስምንት ወር የሰራነውን እነሱ በአስር አመት አልሰሩትም። ሰባት ደረጃ አንድ አስፋልት ስራ አስጀምረናል። አምስት ሆስፒል ሰርተን፣ ሶስት ወደ ሆስፒታልነት ደረጃ ከፍ አድርገን፣ ሁለት አጠቃላይ ጥገና አድርገናል። ሰላም የፈጠርነው ከሰላሳ ሺህ በላይ ወጣቶችን ተገቢውን ስልጠና ሰጥተን፣ ትጥቅና ስንቃቸውን አሟልተን። በየገጠሩ ከአስር በላይ የገጠር ድልድይ እና ጥርጊያ መንገድ ሰርተናል። ከዚህ ቀደም የደም ባንክ ነበረ? የለም። አሁን ሶስት አለ። የተቆፈሩ የውሃ ጉድጓዶች በርካታ ናቸው። እኔ “ገና እንሰራለን፣ በዚህ አንኩራራ” ስለምል በቴሌቭዢን ከበሮ አላስደልቅም። ይህ ርካሽ ፖለቲካ ስለሆነ ነው።
እኔ ሀገር እየመራሁ ነው። ስራ አለብኝ። ለአሉባልታ እየመለስኩ ጊዜ አላባክንም። በርግጠኝነት እኔን ከአዲሳባ መጥቶ በገንዘብ የምመልሰው ሰው የለብኝም። ፈርቼ ገንዘብ እየሰጠሁት የማባብለው ባለስልጣንም ሆነ የጦር ጄኔራል የለም።
ያስቆምኩት በሞኖፖል የተያዘውን፣ በአብዲሌ ቅርብ ሰዎች የመንግስትን ስልጣን ተጠቅመው የዘረጉትን የንግድ መረብ ነው። ይህ የሚያንገበግበው ብዙ ሰው አለ። በርካታ ትግል አድርገናል ሙስና ላይ። አሁንም እያደረግን ነው።
ለምሳሌ ልንገርህ፣
የሾምኩት አንድ ባለስልጣን ነበረ። ስሙ ይለፈን። ለትምህርት ቤት ያስመጣው ወንበር እና ቁሳቁስ በጣም የወረደ ነበር። አስመረመርኩት። ሙስና አገኘሁበት። አሰርኩት። በፌስቡክ ሙስጠፋ እንደ አብዲሌ እስር ጀመረ ተብሎ ዘመቻ ከፈቱብኝ።
ሙስና ላይ ቁርጠኛ ነኝ። እየሰራን ነው።
ጋዜጠኛ፣
ከርስዎ ጋር ስላልተግባባ ስልጣን ላይ የነበረ ሰውን አንስተው ሌላ ሰው ተክተዋል።
ሙስጠፋ፣
ሀገር እየመራሁ ነው። መንግስታዊ ስራ ነው የምሰራው ከስራው አንዱ መንግስት የያዘውን እቅድ የሚያስፈፅምለትን ትክክለኛ ሰው በትክክለኛው ቦታ ማስቀመጥ ነው። አንተ ስለየትኛው ሰው እና ቦታ ነው የምትጠይቀኝ ያለኸው?
ጋዜጠኛ፣
በቅርቡ የፀጥታ ዘርፍ ሀላፊዎትን አንስተውታል። ለምን አነሱት?
ሙስጠፋ:
ለኔ ምክንያት አለኝ። የፀጥታ ስራው በምፈልገው ደረጃ በእስትራቴጂ እና በእቅድ ሊመራልኝ አልቻለም። ከቀን ወደ ቀን የፀጥታ ስራ እየተበላሸ ሲመጣ ታወቀኝ። የተቀናጀ እቅድና ሪፖርት አያመጣልኝም። የእሱ ስራ አጠቃላይ እኔ ላይ ወደቀ። እኔ ደግሞ የሚያግዘኝ ሰው እፈልጋለሁ። ቦታው የሚፈልገውን ግዴታዎች ሳይወጣልኝ ሲቀር ቀየርኩት። ሰላም ከተረበሸ በኋላ መጣደፍ ሳይሆን ሰላም እንዳይረበሽ በእቅድና በእስትራቴጂ መስራት ያስፈልጋል። ሰላም ከሌላ ሀገር የለም። አንተ የሶማሊያ ዜጋ ነበርክ። ሀገሪቷ ሰላሟ ስለተረበሸ ነው በስደት እንግሊዝ የገባኸው አይደል? የአንድ ሰው መነሳት ከሀገር ሰላም ጋር ማወዳደር አያስፈልግም።
ጋዜጠኛ:
እሱን የተካው ሰው ሰላም እንደሚያሰፍን በምን አረጋገጡ?
ሙስጠፋ:
መቼ አረጋግጬያለው አልሁ?
ጋዜጠኛ:
ማለቴ የተነሳው ሰው የላሳካውን ያሳካልኛል ብለው እንዴት አመኑ
ሙስጠፋ፣
በልምዱ፣ በትምህርቱ እና አጠቃላይ ባለው ምልከታ አመዛዝኜ ነው ለቦታው ይሆናል ያልኩት። ከዚህ ቀደም የሀገር መሪን የመማከር ደረጃ የስራ ልምድ አለው፣ በትምህርትም እስከ ፒኤችዲ አለው። በህብረተሰብ ጤና እና በግጭት አወጋገድ፣ conflict resolution ላይ ልምድ አለው። የአለም ፖለቲካ አካሄድ፣ የሀገራችንን ፖለቲካ እና የክልላችንን ተጨባጭ ሁኔታ በደንብ የሚያውቅ ሰው ነው።
ከዚህ ቀደም የፀጥታ ዘርፍ ከአማፂ ጋር ለመዋጋት አይነት፣ ፀጥታ ስራ እንዲሁ ትምህርት የሚያስፈልገው በማይመስል አይነት ነው የሚፈረጀው። የፀጥታ ስራ ትምህርትና ልምድ ይፈልጋል። ከዚህ ቀደም ታማኝነትና ዝምድና ይታያል። ለዚያ ነው በችግር የምንታመሰው።
እኔ ሰው ነኝ ልቦናን አልመረምርም። አላውቅም። የቀድሞም ሰው ይረዳኛል ብዬ አምኜ ነበረ። ስራው እየወረደብኝ መጣ። የሙስናም አዝማሚያ አየሁበት። ለዚያ ቀየርኩት። አሁን የምሾመውም ሰው ለግል ፍላጎቴ አይደለም የምሾመው። ህዝብን እንዲያገለግል ነው። ባመንኩት ደረጃ ካላገለገለ ሊነሳም ይችላል።
የሚመራን መርህ እና መርህ ብቻ ነው። ይህ መርህ አድሎ እና ኢፍትሃዊነት አለበት ብሎ መጠየቅ አንድ ነገር ነው። ሰው አንስተህ ተካህ እንዴት ይባላል። መጠየቅ ካለብን መንግስታዊ አሰራር ካበላሸን ነው። አሰራር ነው መጠየቅ ያለበት እንጂ ኤኬሌን አንስትህ ለምን አኬሌን አደረክ መበል የለበትም።
ጋዜጠኛ፣
አሁንም እስቲ ወደ ሙስና እና ብልሹ አሰራር ልመልሶት።
እርስዎ ሆስፒታል ሰራው እየተቀላጠፈ ነው ሲሉ፣ ፕሮጄክቱ ገና አልተጀረም ብለዋል የጤና ሚኒስትሩ ፣ ከሁለታችሁ ማነው ትክክል፣ ማነው የተሳሳተው?
ሙስጠፋ፣
ሆስፒታል አይደለም የደም ባንክ ነው
ጋዜጠኛ፣
ይቅርታ ልክ ነዎት የደም ባንክ ነው።
ሙስጠፋ፣
ጉዳዩ ከአዘጋገም ስህተት የተፈጠረ ነው። የደም ባንኩ አሁን አልቆ ስራው የፊኒሺን እና የውስጥ አስፈላጊ ግዢዎች አልቀው የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ ነው። ሲዘግቡት ስራ ጀምረዋል አሉ በስህተት። ሚኒስትሩ ስራው አልቆ አልተጀመረም አለ። እውነታው ስራው መጨረሻ ምዕራፍ ላይ መሆኑ ነው።
ጋዜጠኛ፣
ሚኒስትሩ የደም ባንኩ ስራ አልጀመረም ሲሉ እርስዎ የመጨረሻ ምዕራፍ እያሉ ነው፣ አብራችሁ እየሰራችሁ፣ እንዴት እንዲህ አይነት ልዪነት ይኖራል?
ሙስጠፈ፣
እኔ እና ሚኒስትሩ እኮ ሰዎች ነን።
Miss communication ነው የተፈጠረው። ሰዎች ነን። ሰው ደግሞ በበርካታ ጉዳዮች ላይ የመረጃ መዛነፍ ሊኖር ይችላል። This is normal. ስራው ማለቂያው ላይ ነው። ገንዘቡ አልተበላም።
ጋዜጠኛው፣
ልክ ነዎት ክቡር ፕሬዝዳንት ሰው ልጅ ንዎት ሚስ ኮምኒኬሽን ሊፈጠር ይችላል። ተናብባችሁ ብተሰሩ ኖሮ ተጀምሯል፣ አልተጀመረም፣ አልቋል አላለቀም አይነት ውዝግብ አይመጣም ነበረ። የደም ባንክን የመሰለ ትልቅ ጉዳይ አልቆ ስራ ጀመረ፣ ኸረ አልተጀመረም፣ እርስዎ ደግሞ አሁን በመልካም ደረጃ ነው ያለው ይሉኛል።
ይህን ጉዳይ ከረሳችሁት ሌላ ምን የረሳችሁት ነገርን አሁን አስታውሰው ለተመልካቾቻችን ሊነግሩ ይችላሉ?
ሙስጠፋ፣ (በግርምት ግንባሩን ቋጠር አድርጎ)
የረሳችሁት ካለ ንገረኝ ምን ማለት ነው? የረሳነውን አንተ የምታስታውሰው ነገር ካለ ንገረኝ እንጂ።
ስንት ጉዳይ አብራርቼ፣ ስንት ጉዳይ ተናገሬ ሳበቃ የረሳኸው ካለ ምን ማለት ነው?
(ሙስጤ መገረሙ በውስጡ ሆ! ይህ ሰውዬ አብዷል እንዴ የሚል ይመስላል )
ጋዜጠኛ፣
ክቡር ፕሬዝዳንት ማለቴ የደንብ ባንክን የመሰለ የሰው ህይወትን ለማትረፍ ትልቅ ስራ ከረሳችሁ፣ ምናልባት የውሃ ችግር ቅድም የነገሩኝን ረስታችሁትስ ቢሆን፣ ነገ ከነገ ወዲያ ደግሞ እንዲሁ የፀጥታ ጉዳይን እንደማትረሱት፣ የኤሌክትሪክ ዝርጋታ፣ የልማት ጉዳይን እንደማትረሱት ምን ዋስትና አለን ለማለት ነው?
ሙስጠፋ፣ (የታከተው መሰለ፣ አየር ስቦ አወጣ፣ በቅሬታ በለዘበ የትዝብት ቃና ባለው ድምፀት)
እባክህ አብዱልሀፊዝ፣ እባክህ እባክህ፣ ተመልካቾች ቁምነገር እየጠበቁ፣ እጅግ አንገብጋቢ ጉዳይ መጠየቅ ስትችል
ጋዜጠኛው፣ (ቆርጦ ገባ)
እጠይቃለሁ ገና ብዙ የማነሳው ነገር አለ
ሙስጠፋ፣ (ቆጣ ባለ እና ከፍ ባለ ድምፅ)
የደም ባንኩን እኮ አልረሳነውም፣ አልተረሳም፣ ብሩም አልተበላም። ሚኒስትሩ ሄደው ስራውን አዩ፣ በሚጀመር ደረጃ ነው አሉኝ። እኔ የእሳቸውን ተቀብዬ አስተላለፍኩ። ጥያቄው ወደ ዞን ሀላፊ ሲመጣ ገና አልተጀመረም አለ። ከዚያ ሚኒስትሩ አልተጀመረም መልሰው አሉ። በቃ absolutely its a minor miscommunication. ምንም የረባ ለክርክር የሚበቃ ጉዳይ አይደለም።
ጋዜጠኛው፣
እሺ የሚጀመርበትን ጊዜ በትክክል ሊነግሩኝ ይችላሉ። እንግዲህ የደም ጉዳይ
(ሙስጠፌ አቀርቅሮ ጭንቅላቱን ወዘወዘ። የደም ባንኩ ተራ ጥያቄ ደሙን ያፈላው ይመስላል)
እኔ እራሴ ደሜ ስለፈላ! ለዛሬ እዚህ ላይ ላብቃ። ሆ!
Filed in: Amharic