>

"አዲስ አበባ ዛሬም ልጆቿን እየገበረች ነው!!!" (ከስንታየሁ ቸኮል -- ባልደራስ)

አዲስ አበባ ዛሬም ልጆቿን እየገበረች ነው!!!”

ከስንታየሁ ቸኮል /ባልደራስ/
“..ለውጥ  የለም ያለዉ የደም ግብር ነው!!!”
 /ሀዘንተኛ ቤተሰብ/
አስቸኳይ አዋጅ ከወጣ በኃላ የፌደራል ፖሊስ የሰዉ ህይወት ቀጠፈ አንድ ወጣት በጥይት ሲገድል በአንዱ ላይ ከባድ ጉዳት አደርሷል።
ከመገናኛ 24/ አሳዛኝ ዜና በኃላ የተሰማ አስደንጋጭ መረጃ የአዲስ አበባ ወጣት በልዩ ኃይል ሰራዊት ዛሬም ሰለባ እየሆነ መጥቷል።
በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 05 ቤልጂየም ኢንባሲ ጀርባ ልዩ ቦታዉ 01 መዝናኛ ክበብ ተብሎ በሚጠራው አስቸኳይ አዋጅ በወጣበት ጊዜ ወጣት አቤል ደርቡሽ የተባለ እና ሚኪያስ ደምስ  ሁለት ጓደኛሞች በፌደራል ፖሊስ በጥይት የተመቱ ሲሆን ወጣት ሚኪያስ ደምስ ጀርባው ላይ ተመቶ ወዲያዉኑ ህይወቱ እንድታልፍ ሆኗል።
 በቅርብ እርቀት የነበረው እና በአካባቢው የጥይት ድምጽ ሰምቶ ሮጦ የመጣው ጓደኛዉ_ ወጣት  አቤል ደርቡሽ ፌደራል ፖሊሱን ምንድነዉ  ብሎ ሲጠይቅ ምናገባህ በማለት ፊት ለፊት በሆዱ ላይ በመተኮስ ከፍተኛ ጉዳት አድርሰውበታል።
በአሁኑ ሰዓት አቤል ደርቡሽ በህክምና የሚገኘው ሲሆን የጓደኛውን ሞት እስካሁን እንዳይሰማ ተደርጎ የህክምና ክትትል እየተደረገለት እንደሚገኝ ከቤተሰቦቹ ለመረዳት ተችሏል።
ባልደራስ ይህን ጭፍጨፋ ከሰማ በኃላ በዛሬው እለት ሚያዚያ 19/2012 ዓ.ም ቦታው ድረስ በመሄድ የሟች ቤተሰቦችን አነጋግሯል። የሟች ሚኪያስ ደምስ ወላጆች በመሪሪ እንባ ልጃቸውን ቶኩሶ የገደለው ፌደራል ፖሊስ በባለጊዜ ስሜት አናቀውም ወንጀለኛዉን ለማጋለጥ አንተባበርም በማለት የፖሊስ አካል የሚያሳየን  አጥተናል።  ክስ እንዳንመሰርት ተደርገናል ህዝብ ይፍረደን ሲሉ ተደምጠዋል።
 ወጣት ሚኪያስ ደምስ በአካባቢው ነዋሪ ከማንም ሰዉ ጋር በባህሪዉ የሚግባባ ለጠብ የማይጋበዝ ወጣት ነበር በማለት የገለጹት ወላጆች መንግስት ያሰማራቸው ወታደሮች ልጃችንን ከመግደሉም በላይ የአካባቢው ሰዉ ድርጊቱን እንዳያይ የተገኘው ሁሉ በመደብደብ አስክሬን እንዳናነሳ ተደርገን ቆይተናል። የልጃችን ሞት ምኒልክ ሆስፒታል ተጠርተን ነው ያየነው ፍትህ እንሻለን ሲሉ በአሳዛኝ ለቅሶ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።
 የባልደራስ ፕሬዝደንት እስክንድር ነጋ ይህ ጉዳዩ ህዝብ እንደሚከታተለው ከወላጆች ጋር በመሆን  ተኩሶ የገደለ ፌደራል ፖሊስ እና አመራሩን ህግ ፊት ፍትህ እንዲያገኙ ድርጅታቸው ጥረቱን  እንደማያቋርጥ ገልጾ ባልደራስ የሟች ቤተሰብ  በማጽናናት ሁሉም ህዝብ ከጎናቸው እንዲቆም ጥሪ አስተላልፏል።
Filed in: Amharic