>

የአዲስ አበባ ፖሊስ  ዛሬም እስክንድር ነጋ እና ባልደረቦቹን አስረው ከሰአታት እገታ በኋላ ለቀዋቸዋል (ባልደራስ)

የአዲስ አበባ ፖሊስ  ዛሬም እስክንድር ነጋ እና ባልደረቦቹን አስረው ከሰአታት እገታ በኋላ ለቀዋቸዋል

ባልደራስ
የእስክንድር ነጋ የግል ሞባይል ስልክ በፖሊስ ከተቀማ ዛሬ 5 ቀኑን ይዟል ።
ተንቀሳቃሽ ስልኩ እንዲመለስለት ለመጠየቅ ወደ ስፍራው እስክንድር ከባልደረቦቹ ጋር ባቀናበት ወቅት ፖሊስ ስልኩን ለመመለስ ፈቃደኛ አለመሆኑን ገልጿል።
ፖሊስ የሰጠውን የእምቢተኝነት ምላሽ በወቅቱ ከስልኩ ባለቤት እስክንድር ነጋ ጠይቆ ለህዝቡ ለማድረስ የቀረፃ ስራ ስናከናውን መረጃ መስጠት አትችሉም በሚል ከልክለውናል።
ከክልከላው ባሻገር እንዲያውም ለጥያቄ እንፈልጋችኋለን በሚል በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ለሰዓታት ታግተው ቆይተዋል።
ጉዳዮ ይህ ሆኖ ሳለ ተንቀሳቃሽ ስልኩን መመለስ ሲገባቸው ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ የግል ማህደሩን አየበረበሩ ይገኛሉ።  ይህ ደግሞ ከህግ አንፃር ተገቢ ያለሆነ ጉዳይ በመሆኑ ሊመለስ ሲገባው ዛሬም ማንገላታቱን ቀጥለዋል።
ይህን ጉዳይ የኢትዮጵያ ህዝብ ሊያውቅ ይገባል።
በአሁኑ ሰዓት ከእገታውም ተለቀናው ወደ ቢሮ ተመልሰዋል።
ድል ለዲሞክራሲ! 
አዲስ አበባ ባልደራስ
Filed in: Amharic