>
7:15 pm - Monday May 29, 2023

የአድባራትና ገዳማት መዘጋትን ተከትሎ አገልጋዮቹና ምእመኑ ላይ የደቀነው አደጋ!!! 

የአድባራትና ገዳማት መዘጋትን ተከትሎ አገልጋዮቹና ምእመኑ ላይ የደቀነው አደጋ!!! 

 
የሰንበት ትምህርት ቤቴ ማስታዎሻና ሰንበት ትምህርት ቤቴ
 
በዓለም እንዲሁም በሀገር ደረጃ የተከሰተው የኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ወረርሽኝ እዳይስፋፋ ከሚወሰዱ እርምጃዎች አንዱ እርቀትን መጠበቅ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ለተወሰነ ጊዜ የእምነት ተቋማት ምዕመናኖቻቸውን በተቀመጠው አሰራር መሰረት እንዲቀሳቀሱ እና ስርዓት አምልኮ እንዲፈፅሙ መደረጉ ይታወቃል፡፡ ይህንና ከተወሰነ ጊዜ በኋላ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ምክንያት ሙሉ በሙሉ እዲዘጉ መደረጉ ይታወሳል፡፡ በተለይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ካላት ሥርዓተ አምልኮ አንፃር ቅዱስ ሲኖዶስ ምዕመናን መከልከል የሌለባቸውና ያለባቸው ብሎ ከፋፍሎ ምዕመናን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ቢያሳስብም በመንግስት አካላት ግን ተፈፃሚ ሊሆን አልቻለም፡፡
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ክርስትና፣ ቁርባን፣ ፍትሐት እና ሌሎችም አገልግሎቶች መቋረጥ የሌለባቸው እንደሆኑ የሚታወቅ ቢሆንም መንግት በየ ቤተክርስቲያኑ አድባራትና ገዳማት በር ላይ ያስቀመጣቸው አካላት ክርስትና ምንድን ነው፣ ቁርባኑን እዚህ ያምጡላችሁ፣ በሌላ ጊዜ ክርስትና ትነሳላችሁ/ታስነሳላችሁ፣ አለቆቹን ጳጳሳችሁን ጠይቁ  ወ.ዘ.ተ እየተባለ እምነቷ፣ ስርዓቷ መሳለቂያ ከመሆኑም በላይ በግለሰቦች መልካም ፈቃድ እየተበደለች እንደምትገኝ የአደባባይ ምሥጢር ነው፡፡ በዚህም የተነሳ ምዕመናኗ ከባድ የሆነ ችግር ውስጥ እየገባ እንደሆነና ጉዳዩ ከባድ ደረጃ ላይ እየደረሰ ከመጣ ለመንግስት አስቸጋሪ ወደሚባል ሁኔታ መሄዱ የማይቀር ነው፡፡
ይህን በእንድህ እንዳለ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሃብቷ ልጆቿ ምዕመናኖቿ ናቸው፡፡ ካለት ሀብትና ንብርት ውስጥ ከ90% በላይ የሚሆነውን ከልጆቿ የምታገኘው ቤተክርስቲያናችን በአሁኑ ሰዓት መንገድ ሳይዘጋ፣ ገበያ ሳይዘጋ፣ መጠጥ ቤቶች፣ ምግብ ቤቶች ሳይዘጉ 3 ሰው በጋራ ሆኖ መንቀሳቀስ በሚቻልበት ሰዓት ቤተክርስቲያን ሙሉ በሙሉ እንድትዘጋና ልጆቿ እንዳይገቡ በመደረጉ ለከፍተኛ የኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ እንድትወድቅ እየተደረገ ይገኛል፡፡ ይህ ደግሞ ወረርሽኙን መቆጣጠርና መከላከል የጋራ ስራ ሆኖ እያለ በፀረ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ግለሰቦች ትዕዛዝና ቤተክርስቲያንን የማዳገም ስራው በዚሁ ከቀጥል የመጀመሪያው ተጎጅ የእኛዋ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ትሆናለች፡፡ ምዕመናኑ ገብቶ መርዳትና ቤተክርስቲያንን መደገፍ ካልቻለ ከብዙ በትልሹ፡-
1. አድባራትና ገዳማት ለአገልጋዮቻቸው ደመወዝ መክፍል ካልቻሉ ከዚህ ጋር ተያይዞ ካህናትና የካህናት ቤተሰቦች፣ዲያቆናት ደጅ ጠኚዎችና አጠቃላይ ሰራተኞች ትልቅ አደጋ ላይ ይወድቃሉ፤ ተከራይተው የሚኖሩ አገልጋዮች ሜዳ ላይ እንዲወድቁ ይገደዳሉ፡፡
2. ከረሃብና ከችግር የተነሳ ክብረ ክህነት ይፈርሳል፤ ዲቆናትና አገልጋዮች ይፈልሳሉ፤ ጥበቃዋ ይቆማል፤
3. ቤተክርስቲያን የመዘረፍ፣ ሃብትና ንብረቷን የማጣት እድሏ ሰፊ ይሆናል፤ በተሃድሶ መናፍቃንና በሃይማኖት የለሸረ ወራሪዎች ልትያዝ ትችላለች፤
4. ክብሯን ዝቅ ለማድረግ በሚጥሩ ኃይሎች ልትደፈርና ያለ አግባብ በደልና እንግልት ሊደርስባት ይችላል፡፡
5. በተለይ አቅም የሌላቸው ብዙ ምዕመናንና ወጣቶች እየተታለሉ በእርዳትና በሌሎች ዘዴዎች ወጥመድ በመግባት በተሃድሶ መናፍቃን እየተወሰዱ መሆኑና ሌሎችም እንዳሉ የሚታይ ነው፡፡
6. ምዕመኑ ሁኔታውን ለምዶ እና በፍርሃት ተውጦ በቤቱ ሆኖ ሃይማኖት የለሽ ዜጋ እንዲፈጠር ትልቅ በር እየከፈተ ያለና ለብዙ ዘመናት ሲመኙት የኖሩት ጠላቶች ሰርገው ገብተው እየሰሩበት መሆኑ፤
እንዲሁም እንደ ሀገር ሊደርስ የሚችለውን የኢኮኖሚ ችግር ማን ሊቋቋመው ይችላል? የሀገሪቱ መንግስትስ ይህንን አስከፊ ችግር በምን መልኩ ሊቋቋመው ይችላል? ቤተክርስቲያናችንስ ይህንን የፈተና ወቅት እንደት አድርጋ ታልፈዋለች? የሚሉት ጥያቄዎችን መመለስ ከባድ እየሆነ ነው፡፡ ባለፉት 2 ቀናት ውስጥ በአዲስ አበባ ሀገረ ስከት ውስጥ ተዘዋውረን እና በስልክ የገዳማትና አድባራትን አስተዳዳሪዎች ባናገርንበት ወቅት 137 የሚሆኑ አዲባራትና ገዳማት ከ2 ወር የበለጠ ደመወዝ መክፈል እንዳማይችሉ ለመረዳት ችለናል፡፡ ለዓብነት የመንበረ መንግስት ግቢ ገብርኤል ገዳም፣ የታዕካ ነገስት በዓታ ለማርያምን ገዳም፣ ቁስቋም ማርያም ቤተክርስቲያን፣ ምስካይ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም፣ የእንጦጦ ሐመረ ኖህ ቅድስት ኪዳነምህረት ገዳም፣የየካ ኮተቤ ኪዳነ ምህርት ቤተክርስቲያን፣ ኢያቄም ወሃና ማርያም ቤተክርስቲያን፣ የሲኤምሲ የደብረ ፅባህ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን፤ የቅዱስ እስጢፋኖስ ቤ/ክን፣ የቅዱስ ያሬድ ቤ/ክን፣ ቦሌ ሚካኤል፣ ጃቲ ኪዳምህረት፣ጎፋ ገብርኤል፣ ጎላ ሚካኤል፣ ደብረ አሚን፣ ቅዱስ አማኑኤል፣ ቀጨኔ መድኃኔዓለም፣ ቅዱስ እግዘኢአብሔር አብ፣አስኮ ገብርኤል፣እንጦጦ ማርያም፣የዋሻ ቅዱስ ሚካኤል፣ ደብረ ይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሌሎችም በአጠቃላይ ከተጠቀሱት አድባራትና ገዳማት  በተጨማሪ የአንድ ወር እንኳን መከፈል የማይችሉ እንደሆኑ ለመረዳት ችለናል፡፡
በመጨረሻም ለአጭር ጊዜ መፍትኔው ምንድን ነው ብለን ስናይ፡
1. ያለምንም ጥናትና ውይይት ያልተገባ ሥራ እየሰራ ያለው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ውስጡን በፍጥነት ፈትሾ ወደ ስራ መግባት አለበት፤ ምክንያቱም በሀገረ ስብከቱ የህግ ክፍል ኃላፊ ቀጥታ ትዕዛዝ ስለሆነ አድባራትና ገዳማት ለከፍተኛ ጉዳት የተዳረጉት መፈተሸና ስራው ማጤን አለበት፤
2. የቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ መሰረት የተባለውና 4 ሊቃነ ጳጳሳት ብቻ የፈረሙበት ሂደት በድጋሚ ሊጤንና ውስጡ ሊታይ ይገባዋል፤
3. የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ከምሽቱ 12፡30 ቢሆን ዕርዳታ ለመሰብሰብ በተወሳሰበ አሰራር የሄደበት መንግድና ቦታዎቹ የተመረጡበት ሂደት አግባብ አለመሆን በማየት ሌሎች አማራጮችን መፈለግ፤
4. እስከ አሁን ድረስ ሀገረ ስብከቱ ችግሩን እያወቀና እየተረዳ በሩን ዘግቶ መቀመጡ አግባብ አለመሆኑን በመውሰድ በፍጥነት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት በማድረግ፡
1. በሀገረ ስብከቱ ገበያ፣ መንገድ፣ የሰዎች ዝውውር፣ መጠጥ ቤትና ምግብ ቤቶች ወ.ዘ.ተ ሳይዘጉ ቤተክርስቲያን መዘጋቷ አግባብ አለመሆኑንና የሚመጣውን ችግር በመለየት ለሚመለከተው አካል ማሳወቅና እንድትከፈት ማድረግ፤
2. ለሚያዝያ ወር የሚሆን ሀገረ ስብከቱ በተቻለ መጠን በሰው ሃይላቸው መጠንና አቅማቸውን በመለየት ለአድባራትና ገዳማት የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ፤
3. የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሚጠይቀውን % ላልተወሰነ ጊዜ ማቆምና ወደ አድባራትና ገዳማት ካዝና እንድገባ ማድረግ፤
5. ቤተክርስቲያን ያላትን ሀብትና ንብረት ለመቆጣጠርና በዚህ አጋጣሚ የሚጠፋውን ለማዳን ይረዳ ዘንድ በአስቸኳይ የአያያዝና የአጠቃቀም እንዲሁም የእክብካቤ ስራን መዘርጋት አለባት፡፡
6. የህግ የበላይነት እንዲከበር ጠንከር ያለ አቋም በመያዝ ልትንቀሳቀስ ይገባል፤ ቤተክርስቲያን፣ አባቶቻችንና ተከታዮቿም በምንም መልኩ ሊሳቀቁና ሊገፉ እንደማይገባ በስፋት ልንሰራ ይገባል፡፡
7. ምዕመኑ ሁኔታውን ለምዶ እና በፍርሃት ተውጦ በቤቱ ሆኖ ሃይማኖት የለሽ ዜጋ እንዳይፈጠር በተጋት መስራትና መንቀሳቀስ፤ በተለይ ሰንበት ትምህርት ቤቶች እንዲቀሳቀሱ ማድረግና ተደራሽ ለመሆን መጣር፤
8. በፀሎት ሰዓት ላይ የሚሰጡ ስብከቶችን መለየትና ለምን ወደ ቤተክርስቲያን እንደምንሄድ ማስረዳትና መንገር አለብን፡፡
ከሞላ ጎደል ይህንን ካልን ሁላችንም ቆም በልን ልንገነዘበው ይገባል፡፡ ይህንን ፅሁፍ የምናነብ ሁላችንም አድባራትንና ገዳማትን እንርዳ፣ ለሃይማኖታችን ዘብ እንቁም፤ ቤታችንን እንጠብቅ፡፡ ካህናቱና ቤተሰባቸውን እናስብ፣ ዲያቆናቱንና አገልጋዩን እናስብ፡፡
Filed in: Amharic