>
5:13 pm - Wednesday April 19, 9567

የሚያሸጋግር ድልድይ ሰርቶ የማያውቅ የሽግግር መንግስት!!! (ዮናስ ዘውዴ)

የሚያሸጋግር ድልድይ ሰርቶ የማያውቅ የሽግግር መንግስት!!!

ዮናስ ዘውዴ

መኖር ማለት መሰቃየት ነው። በስቃይ ውስጥ ትርጉም ማግኘት መኖር ማለት ነው። ሰው እንደሚታወቀው የሚኖረው በስቃይና በደስታ መካከል ነው ይላሉ ሊቃውንቱ ። መኖር ማለት ትርጉም መሻት፣ መዳከር ነው። መኖር ማለት በመከራ፣ በሀዘን፣ በስቃይ ውስጥ ትርጉም መፈልቀቅ መበየን ነው። ግና በህይወት መኖር ትረጉም ካለ። በመሰቃየትም ትርጉም አለ። በመሞትም ትርጉም አለ። ትርጉሙን ፈልጓ ማግኘት ግን እንደ ሰውየው ሊወሰንና ሊለያይ ግን ግድ ይመስለኛል ። ኒቼ ለምን እኖራለሁ የሚለውን ካወቀ አንድ ሰው እንዴት እኖራለሁን ያውቃል ይላል። እኔ ግን በዚህ ቀመር መስማማቴን እርግጠኛ አይደለሁም።
የሚያሸጋግር ድልድይ ሰርቶ የማያውቅ የሽግግር መንግስት
እስኪ ደም ስጡ።
እስኪ ማዕድ አጋሩ ስልጣን ከመጋራት በፊት በእሱ ተለማመዱ።
እስኪ ስለ ኮረና አስተምሩ ስለ ስልጣን ተማሩ።
እስኪ ኮሮና ተመርመሩ ስለ መስከረም 30 ከምትመረምሩ።
የሚያሸጋግር ድልድይ ሰርቶ የማያውቅ የሽግግር መንግስት 
የሞት ነጋዴዎች ሰለቹን። ለሞት ቦታ ከምትሰጡ እስኪ ቅድሚያ ለህይወት ቦታ ስጡ።
እናት ልጁን ለጥይት መገበር ሰለቻት ኮረና መጥቶ እረፍት ሰጣት።
የሚያሸጋግር ድልድይ ሰርቶ የማያውቅ የሽግግር መንግስት 
ርሀብ ሰለቸን።
አሁንም ወንድምና እህቶቻችን ሽቅብና ቁልቁል እንዲሞቱብን አንፈልግም። በቃን ሰለቸን። ደከመን።
እናንተ እንደሆነ ሞትን ከለመዳችሁት ቆያችሁ ቁጥር እንጂ ህልም የሚሞት አይመስላችሁም።
ብሔር እንጃ የፈጣሪ መልክ የሚሞት አይመስላችሁም። ከ1960 ጀምራችሁ አንድም ስትገሉ። አንድም ስታስገድሉ። አልያም የመተ እያያችሁ ነው የመጣችሁት።
አንዳንዶቻችሁ እኔደ ጲላጦስ እጃችሁን ታጥባችሁ። ዐይናችሁን አፍጣችሁ። ደረታችሁን ነፍታችሁ አሁንም ከደሙ ንፁ ነኝ ትላላችሁ። በዙ የደም ጋኖች ሞልታችሁ።
የሚያሸጋግር ድልድይ ሰርቶ የማያውቅ የሽግግር መንግስት 
እባካችሁ የህግ ባለሙያ አማክሩ ከራሳችሁም ተማከሩ።
የህግ መሀይማን አትሁኑ።
የስልጣን ሱስ ሳይሆን የሰው ልጅ ህይወት ማዳን ሱስ ይሁንባችሁ።
የሚያሸጋግር ድልድይ ሰርቶ የማያውቅ የሽግግር መንግስት 
የምግብ ሱስ ይያዛችሁ። የስልጣን ሱስ ያለበት ስልጣን ቢይዝ ምን ሊያደርገን ይችላል? አየነው እኮ ባለፈው ጥቂት አመታት።
የሚያሸጋግር ድልድይ ሰርቶ የማያውቅ የሽግግር መንግስት 
ሀይማኖትና አማኝ ጠል የፓለቲካ ፓሪቲና ፓለቲከኛ የስልጣን በትር ቢጨብጥ ምን ሊያደርገንና ሊያደርግብን የሚችለውን መገመት አይከብድም።
ገና ስልጣንን ሳይዝ አማኝን የሚያንቋሽሽ፣ የሚያጥላላ፣ የሚያበሻቅጥ ፓሪቲና ፓለቲከኛ አይጠቅምም።
የሚያሸጋግር ድልድይ ሰርቶ የማያውቅ የሽግግር መንግስት 
ለህዝብ ለማሰብ። ለደሀው ለማሰብ። ለሴቶች፣ ለህፃናት ለማሰብ። ልጆቻቸው ለእናንተ የስልጣንና የደም ጥማት ለማርካት ለሚገብሩት ደጋግ እናቶችና አባቶች ለማሰብ የግድ ስልጣን መያዝ ና መንግስት መሆን ሳይሆን የሚጠይቀው ሰው መሆን ነው።
የሚያሸጋግር ድልድይ ሰርቶ የማያውቅ የሽግግር መንግስት 
የእውነት የሽግግር መንግስት ይቋቋም እንኳ ቢባል። ከእነማን ጋር ነው የሽግግር መንግስት የሚኮነው? ከእነ እንቶኔ ጋር? ማኔ ቴቄል ሆናቹሀል እኮ። ባትመዘኑ ከባዶች ናችሁ ትባላላችሁ። ኢላማ ባይኖራቹሁ አትስቱም ይባላል። ግና እናንተ እኩ በብዙ ተፈትናችሁ አንዴ አይደለም ብዙ ጊዜ ደጋግማችሁ በፊታችን ወድቃቹሀል።
የሚያሸጋግር ድልድይ ሰርቶ የማያውቅ የሽግግር መንግስት 
የአንድ ሀይማኖት፣ ብሔር፣ መንደር ፖለቲካንና ፓለቲከኛን አጥብቄ እቃወማለሁ። አሁንም የሽግግር መንግስት? ሀገር፣ ወገን፣ እርኸራየ የለም በውስጣችሁ። ደርግ የሽግግር መንግስት አለ። ያ ሁሉ ስቃይ መከራ አለፈ። ያ ሁሉ ወጣት እንደ ዛፍ ቅጠል እረገፍ፣ ሀዘን ብዙ ቤት ገባ። ብዙ እናቶች ዛሬም በብዙ ምሬት ወደ ሞት ጓዳና ነጓዱ። እየነጓዱም ነው። ከዚያ የኢሀዲግ የሽግግር መንግስት ይኸው ላለፉት በርካታ አመታት ምድሪቷ የደም ገንቦ አደረጋት። አሁንም የሽግግር መንግስት? ግን እስከ መቼ?
የሚያሸጋግር ድልድይ ሰርቶ የማያውቅ የሽግግር መንግስት 
ይኸ ደግና ጨዋ ህዝብ የላብራቶሪ እንቁራሪት መስላችሁ እንዴ? ስልጣን ቅርጫ አይደለም የበሬ ስጋ። የሚያሸጋግር ድልድይ ሰረቶ የማያውቅ የሽግግር መንግስት ሆኖ ሀገር ያሻግራል የሚል ሞኝነት የለኝም።
ሰው የሚለካው በሚያደርጋቸው ነገሮች ብቻ ሳይሆን በሚያስባቸውም ጭምር እንጂ።
ነጋድራስ ተሰማ እሸቴ :- “ሁሉን ተሸክማ የምትኖር ዓለም ከሰነፍ በስተቀር የሚከብዳት የለም” ነበር ያሉት።
Filed in: Amharic