>

ፖለቲካ ራሱን ሲደግም!!! (ቬሮኒካ መላኩ)

ፖለቲካ ራሱን ሲደግም!!!

ቬሮኒካ መላኩ
..
አሁን ያለው መንግስት የገጠመው ፖለቲካዊ ፈተና   ከ120 አመታት በፊት አፄ ምኒልክ ከገጠማቸው ፖለቲካዊ ክስተት ጋር እጅግ ተመሳሳይ ነው፡፡  አፄ ምኒልክ ፖለቲካሊ ሱፐር ጂኒየስ ስለነበሩ  ፖለቲካውን በክህሎትና በድል ተወጥተውታል፡፡ የትግራይ ክልል ትናንት ባወጣው መግለጫ የአቢይ አህመድን መንግስት በፖለቲካዊ የቃሪያ ጥፊ አጩለውታል፡፡ ለአንድ መንግስት ነኝ ለሚል አካል ይሄ በምንም መንገድ የማይታለፍ ቀይ መስመር ነው፡፡
በ1889 አፄ ዮሀንስ መተማ ላይ ሲወድቁ አፄ ምኒልክ እንጦጦ ላይ  ቅብአ ንጉስ በመቀባት  የኢትዮጵያ ንጉስ መሆናቸውን አወጁ ፡፡ ሌላው የኢትዮጵያ ክፍል የአፄ ምኒልክን ንግስና ተቀብሎ መልካም ምኞቱን ሲገልፅ ትግራይ ግን በመአከላዊ መንግስትና በአፄ ምኒልክ ላይ በማመፅ የአገሪቱ ንጉስ ራስ መንገሻ  መሆነቸውን አወጁ ፡፡
በዚህም ወቅት ቢሆን ታዋቂው ጀግና ራስ አሉላ አባ ነጋ የምኒልክን የአገር መሪነት በመቀበልና በማመን ወደ አዲስአበባ መጥተው ነበር፡፡
አፄ ምኒልክ በወቅቱ አለም ባደነቀላቸው የድፕሎማሲ መንገድ ከድርጊታቸው እንድታቀቡ ለትግራይ መኳንንት መልእክት ላኩ፡፡ የትግራይ መኳንንቱም በእምቢታቸው ፀኑ፡፡ በመጨረሻ አፄ ምኒልክ የስልጣን ልኧላዊነታቸውን ለማስከበር ፈረሳቸውን አባ ዳኘውን ” ቼ በለው !” አሉ ፡፡ ትግራይ መቀሌ ገቡ፡፡  በመጨረሻ ጤዛ እንኳን ሳይረግፍ  አማፂያኑን የትግራይ መኳንንት በቁጥጥር ስር አውለው የሐረሩን ራስ መኮንን ወልደሚካኤልን ለትግራይ ሾመው መንግስታቸውን አፀኑ፡፡
ዱላና መላ ተፈጥሯዊ ቁርኝት (dialectical relationship) ያላቸው የአንድ መንግስት ባህሪ ናቸው፡፡  አሁን ትግራይ ቀይ መስመሩን አልፋለች ፡፡ አቢይ አህመድ ይችን አማፂ ለማስገበር ወይ ዱላ ወይም መላ መጠቀም ግድ ይለዋል፡፡
Filed in: Amharic