>

ሰሚ ያላገኘው የኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ ጥሪ!!! (ያሬድ ሀይለማርያም)

ሰሚ ያላገኘው የኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ ጥሪ!!!

 

 

ያሬድ ሀይለማርያም
* ዛሬም የዜጎች ቤት እየፈረሰ ሕጻናት እና ሴቶች ጎዳና ላይ እንዲወድቁ እየተደረገ ነው!!!
በቅርቡ በአዲስ አበባ እና በአንዳንድ አካባቢዎች የሚፈጸሙ የነዋሪዎችን ቤቶች የማፍረስ ዘመጃ ይህ የኮቪድ ወረርሽኝ ጋብ እስኪል ድረስ መንግስት እንዲታገስ ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ ጉዳዩ የሚመለከታቸውን አካላት አሳስበው ነበር። ይሁንና ዛሬ ሌሊቱን በመሃል አዲስ አበባ ዋናው ፖስታ ቤት ጀርባ ተመሳሳይ ድርጊት በከተማው መስተዳድር ተፈጽሟል። ኮሚሽነሩ ይህን ብለው ነበር፤ ‹‹መደበኛ ያልሆነ የመሬት አያያዝ እና የቤት ግንባታ መስፋፋት አዲስ አበባን ጨምሮ በብዙ ከተሞች ትልቅ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር ነው፡፡ ሆኖም በአሁኑ #ኮቪድ19 ወቅት ቤተሰቦችን በሃይል ከመኖሪያቸው ማስወጣት ሴቶችና ሕጻናትን ጨምሮ በተለይ ለመብት ጥሰት ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች ትልቅ አደጋ አለው፡፡ አዳዲስ መደበኛ ያልሆነ የመሬት አያያዝ እና መደበኛ ያልሆነ የቤት ግንባታን መከላከል ያስፈልጋል። ነገር ግን በዚህ የአስቸካይ ጊዜ ወቅት መደበኛም ባይሆኑም ነባር ነዋሪዎችን ከመኖሪያቸው በሃይል ማስወጣት ለጊዜው እንዲታቀብ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ጥሪ ያቀርባል።››
አሁንም የሚሰማ ከተገኘ ይሕ አይነቱ እርምጃ በሌላ በኩል መንግስት ኮቪድን ለመዋጋት የሚያደርጋቸውን በጎ እርምጃዎች የሚያጠለሽም ስለሆነ የከተማው መስተዳደር ከዚህ አድራጎቱ ሊቆጠብ ይገባል። ወይም ለእነዚህ ዜጎች ሌላ የመኖሪያ አማራጭ ስፍራ በማዘጋጀት እነሱን ለደህንነታቸው አመቺ የሆነ ሥፍራ ካስቀመጠ በኋላ የማፍረስ ተግባሩን ቢከውን ዜጎች ለከፋ አደጋ ሊጋለጡ የሚችልበትን ደረጃ ይቀንሳል። የኮሚሽኑ ምክር የሰሚ ያለኽ ይላል።
Filed in: Amharic