>

እስራኤል ካቴና ከጠለቀበት በኋላ ነው የፖሊስ ኮምሽነሩ ስልክ በመደወል  "ፍቱት" የሚል ትዕዛዝ ያስተላለፈውiii (ታሪኩ አበራ)

እውን ሀገሪቱ ላይ ህግ ካለ የአዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽነር በሕግ ይጠይቅ !!!

ታሪኩ አበራ
★…ከፍርድ ቤት  የወጣውን የእስር ትዕዛዝ የፖሊስ ኮምሽነሩ ጌቱ ውድቅ አድርጎታል::
 እስራኤል ካቴና ከጠለቀበት በኋላ ነው የፖሊስ ኮምሽነሩ ስልክ በመደወል  “ፍቱት” የሚል ትዕዛዝ ያስተላለፈውiii
 
★ የዓቢይ አህመድ መንግሥት የቀማኞች ዋሻ የሌቦች መሸሻ ነው¡¡¡
  ኮምሽነሩ ጌቱ አርጋው ደበላ ይባላል ቀደም ሲል የደቡብ ክልል ዋና ከንቲባ የነበረ ሲሆን አሁን ደግሞ በአዲስ አበባ ያለው የፖሊስ ኮምሽን የበላይ አዛዥ ኮምሽነር ነው::
ይህ ግለሰብ የመንግሥትን ሥልጣን መከታ አድርጎ ለሐሰተኛ ነቢያት ከለላ በመስጠት በእምነት ስም ከፍተኛ ወንጀሎች እንዲስፋፉ ሲያደርግ የቆየ ወንጀለኛ ሰው ነው።በደቡብ ኢትዮጵያ ከንቲባ ሆኖ በርካታ ሐሰተኛ ነቢያትና አጭበርባሪ ፓስተሮች በሚስጡት ጉቦ እየተደለለ የደቡብ ሕዝብን ሲያስበዝብ የኖረ የወንጀለኞች ተባባሪና አበረታች ነው አሁን ደግሞ አዲስ አበባ ውስጥ የፓሊስ ኮሚሽነር ሆኖ ተመድቦ መጥቶ ወንጀለኛ ሐሰተኛ ነቢያትና አጭበርባሪዎች እንዳይያዙ እያደረገ ነው።
አቶ ጌቱ የኢትዮጵያን ሕዝብ ንቋል ከሐሰተኛ ነቢያት በሚሰጠው ጉቦ በሙስና የተጨማለቀ ከፍተኛ ወንጀለኛ በመሆኑ  በሕግ ሊጠይቅ ይገባል።የዓብይ አህመድ መንግሥት እንዲህ ዓይነት ኃላፊነት የጎደላቸው ስግብግብ ሰዎችን ይዞ  ሀገር መምራት  ፈጽሞ አይችልም።
እስራኤል ዳንሳ ከ20 በላይ የሞት ከ15 በላይ ሴቶችን የመድፈር ከ500 ሚሊየን በላይ ዝርፊያና ከ32 ሰው በላይ የሞራል ክስ ተመስርቶበት እየተፈለገ ነበር::
አጭበርባሪው  እስራኤል ዳንሳ ላይ የቀረበውን ከላይ የተዘረዘረውን  ክስ ከፍርድ ቤት  የወጣውን የእስር ትዕዛዝ የፖሊስ ኮምሽነሩ ጌቱ ውድቅ አድርጎታል::
ምክንያት ብሎ የሰጠውም “መንግስት በዚህ በተፈጠረው የኮረና ቫይረስ ምክንያት እስረኛ እየፈታ በመሆኑ አናስረውም” የሚል ነው::
እጅግ የሚያሳዝነው ግን ከአራት ቀን በፊት  ሚያዝያ 28 /2012 ብቻ ከ10 ሰው በላይ አስረው ወስደዋል ሌላውን ቤቱ ይቁጠረው በኮሮና ጊዜ አለማሰር ለአጭበርባሪው እስራኤል ዳንሳ እንጂ ለሌሎች ግለሰቦች ይሰራል ማለት ነው???
እስራኤል ዳንሳ በቁጥጥር ስር ውሎ በእጁ ላይ የፖሊስ ካቴና ከተደረገ በኋላ ነው የፖሊስ ኮምሽነሩ ስልክ በመደወል  “ፍቱት” የሚል ትዕዛዝ ያስተላለፈውiii
የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ!
በአገራችን በኢትዮጵያ ያሉት የሕግ ባለስልጣናት የፈለጉትን ወንጀለኛ እየፈቱ የፈለጉትንም አስረው የሚያንገላቱባት ፍትህ የሌለባት ሕግ የማይከበርባት አገር አድርገዋታል::
አሁንም በድጋሚ..
የዶ/ር አብይ መንግሥት ይሄንን የባለሥልጣናት አድሏዊ ሥራ እንዲመለከትና ወንጀለኛውም እንደ ወንጀሉ ቅጣቱን እንዲያገኝ….
ጉቦ እየተቀበሉ ፍትህን የሚያጣምሙትንም ለሕግ እንዲያቀርብልን እንጠይቃለን::
በቅርቡ እስራኤል ዳንሳ ራሱ በአንደበቱ
“ከተራው ፓሊስ እስከ ኮሚሽነር ድረስ መኪና እንዲሁም በሚሊየን የሚቆጠር ብር እየጠየቁኝ ነው ከየት አመጣለሁ”? ሲል በራሱ ሚዲያ እንደተናገረ አብዛኞቻችን ሰምተናል::
Filed in: Amharic