>

እነ እስክንድርን ተለቀዋል!!! (ባልደራስ)

እነ እስክንድርን ተለቀዋል!!!

ባልደራስ
መስቀል አደባባይን ለመጎብኘት ሄደው አነጋጋሪ የሆነውን ፕሮጀክት መጎብኘትም ሆነ ፊልም መቅረጽ አትችሉም በሚል  ደንበል አካባቢ የሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ ለሰዓታት የቆዩት እስክንድር ነጋ የባልደራሱ ሊቀመንበር ፣ገለታው ዘለቀ የፓርቲው ጽ/ቤት ሀላፊ እና ስንታየሁ ቸኮል የድርጅት ጉዳይ ሲሆኑ ከሰዓታት የጣቢያ ቆይታ በሁዋላ ተፈተዋል። የመስቀል አደባባዩ ፕሮጀክት በልማት ስም ታሪክን ማጥፋት መሄኑን ገልጸዋል ።
በባልደራስ ላይ መቆሚያ ያጣዉ ጫና። “ተፈናቃዮችን ማናገር  አትችሉም መስቀል አደባባይን  መቅረፅ ፍቃድ ያስፈልጋል  ፖሊስ”
..”መስቀል አደባባይ ለመጎብኘት ሆነ ለመቅረጽ የፖሊስ ፍቃድ አያስፈልግም ለምን?  መስቀል አደባባይ ፎቶ ለማንሳት የፖሊስ ፍቃድ ተደርጎ ያውቃል ወይ?
 በዚህ አለመግባባት ደንበል ፖሊስ መምሪያ ለትንሽ ሰዓት ወስደውን በመነጋገር ተመልሰናል የፖሊስ አባላት ጥፋታቸዉን አምነው በመግባባት ተለያይተናል።  በባልደራስ ላይ የተለየ ዘመቻ እንዳለ ማሳያ ሆኗል። መስቀል አደባባይ የሃይማኖት ክብረ በዓላት የሚከበሩባቸውን ታላቅ ስፍር ነው። ይሁን እንጅ መስቀል አደባባይ አሁን ያለበት ሁኔታ በልማት ስም ታሪክና ስም የመለወጥ ተግባር ከልብ ያሳዝናል ባልደራስ ለህዝቡም መልዕክት አስተላልፏል።
” የጊዜ ጉዳይ ነው ፈጣሪ ያያል ፍርድ ይሰጣል።  ስንታየሁ ቸኮል ከአመራሮቹ አንዱ።
Filed in: Amharic