
ሰበር ዜና:

እስክንድርን ጨምሮ ሶስት የባልደራስ አመራሮች በፖሊስ ታሰሩ!!!
ህብር ራድዮ
የባልደራስ ሊቀመንበር እስክንድር ነጋን ጨምሮ የመስቀል አደባባይ ፈረሳን ለማየት የሄዱ ሶስት የፓርቲው አመራሮች ፖሊስ የፈጸመውን ክልከላ ተከትሎ በቁጥጥር ስር ውለዋል።
እነ እስክንድር ትላንት ፖስታ ቤት ጀርባ በመደበኛ ባልሆነ መንገድ ቤት ሰርተዋል የተባሉን የከተማው አስተዳደር ካፈረሰ በሁዋላ ባስፍራው ነዋሪዎቹን ለማነጋገር ሞክረው ፖሊስ ተመሳሳይ ክልከላ አድርጎባቸው ነበር።
እስክንድር ከሳምንት በፊት በኮልፌ ቤታቸው የፈረሰባቸውን ነዋሪዎች በስፍራው ሔዶ በማነጋገሩ ለሰዓታት ታስሮ የተፈታ ሲሆን ፖሊስ የወሰደበትን ስልክ ከሳምንት በሁዋላ ትላንት መመለሱን ገልጾ ነበር።
የመስቀል አደባባዩን ፕሮጀክት አስመልክቶ የኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን ማብራሪያ እንዲሰጣት መንግስትን ጠይቃ እንደነበር ይታወሳል።