>

የ2.5 ቢሊዮን  ሜጋ ፕሮጀክት  ካለጨረታ መቃረጣቸው የስርአቱን ነውረኛነት አጋልጧል!!! (ቬሮኒካ መላኩ)

የ2.5 ቢሊዮን  ሜጋ ፕሮጀክት  ካለጨረታ መቃረጣቸው የስርአቱን ነውረኛነት አጋልጧል!!!

ቬሮኒካ መላኩ

1ኛ) የወያኔ አይን ያወጣ የቢዝነስ ኢምፓየር status quo ድብቅ በሆነ መልኩ መቀጠሉን  አረጋግጧል። ( ለዚህ ማስረጃው ታከለ ኡማ የለጠፈው መታወቂያ ምስክር ነው።) ወያኔ በፖለቲካ ተሸንፎ መቀሌ  ቢገባም Hidden የሆነው የቢዝነስ ኢምፓየራቸው አሁንም መቀጠሉን መረዳት ይቻላል። የወያኔ ካድሬዎች ለምን ሚስጥሩ ወጣ በማለት እየተንጫጩ መሆኑን እየተመለከትን ነው።
.
2ኛ) ተረኝነት _  ማስረጃው መስቀል አደባባይ ሲንጎማለል የነበረው ገዳ ኮንስትራክሽን ነው።
ፈረንጆች” “winner takes it all” ( ተረኛው ኃይል ሁሉንም ይወስዳል) የሚል ብሂል አላቸው።ይሄ የፖለቲካ ብሂል ሀገሪቱን በሙስና  ሲዘፍቅ ኖሯል። ይሄ ነውር አሁንም መቀጠሉን ያመለክታል።
.
3ኛ) አይን ያወጣ ብልሹ አሰራርና ሙስና ። የ2.5 ቢሊዮን ብር ፕሮጄ ካለጨረታ ተሰጠ ቢባል ማን ያምናል።ይሄ አይን ያወጣ ዘረፋ ነው። በዚህ አይነት ታከለ ኡማ እንደ  ኮንጎው ሞቡቱ ሴሲሴኮና እንደ ናይጀሪያው ሳኒ አባቻ በWhite Elephant project የናጠጠ ቱጃር ሆኖ በትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል መመዝገቡ አይቀርም።
መጀመሪያ:- የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት ገዳ የተባለ ኮንስትራክሽን ቢሰራው ምን ችግር አለው ተባለ (እውነት ነው በህጋዊ መንገድ ጨረታ ካሸነፈ ችግር የለውም )
ቀጥሎ :- ፕሮጀክቱን እሚሰራው የቻይናው CCCC ነው ገዳ ውሃ አቅራቢ ነው አሉ ።
ከዛም:- ገዳ ሚለውን ስም በቻይንኛ ፅሑፍ እስቲከር ለጥፈው  ብቅ አሉ ፤
አሁን ደግሞ:- ገዳ ንግድ ፍቃድ ያለው ድርጅት አይደለም እንዲሁም የትግራይ ተወላጅ ነው ባለቤቱ ወደሚል ጫወታ ቀየሩት ።
እኔ የምለው :-
ንግድ ፍቃድ የሌለው ድርጅትስ በምን አግባብ ይሄንን ሁሉ መኪና አሰማርቶ  በሰብ ኮንትራት ተወዳድሮ  እየሰራ ያለው ? ካልተወዳደረስ በምን መለኪያ ተመረጠ ?  ህዝብ ድምፁን ሲያሰማ ነው ከተጠያቂነት ለመዳን እንዲህ አይነት ማምታታት ውስጥ የገቡት  አመራሮቹ ?
በመጨረሻ ይሄን ድብቅ ነውር ፀሀይ እንድመታው ያደረገው እስክንድር ነጋና ባልድራስ መመስገን አለባቸው።
Filed in: Amharic