>

ቅዱስ ሲኖዶስ: የተዘጉ የቤተ ክርስቲያን በሮች ተከፍተው መንፈሳዊ አገልግሎቱ እንዲፈጸም አዘዘ !(ሐራ ተዋህዶ)

ቅዱስ ሲኖዶስ: የተዘጉ የቤተ ክርስቲያን በሮች ተከፍተው መንፈሳዊ አገልግሎቱ እንዲፈጸም አዘዘ !

ሐራ ተዋህዶ

 በፀረ ኮቪድ-19 እየተመራ የጥንቃቄ ተግባራት ይከወኑ!
 
• ጠቅላይ ቤተ ክህነት ከመንግሥት ጋራ በመነጋገር ትእዛዙን እንዲያስፈጽም መመሪያ ሰጠ፤
• አገልግሎቱን በጥንቃቄ ተግባራቱ መሠረት ለማስፈጸም አጥቢያዎች ሓላፊነቱን ይወስዳሉ፤
• የሰንበት ት/ቤቶችን በማስተባበር፣ መንፈሳዊ አገልግሎቱ በአግባቡ እንዲከናወን ያደርጋሉ፤
• ጥምቀቱ፣ ቊርባኑ፣ ተክሊሉ፣ ፍትሐቱ፥ርቀትን ጠብቆ በተገቢ የልኡካን ቁጥር ይፈጸማል፤
***
• ቅዱስ ሲኖዶሱ፥ የቤተ ክርስቲያን በር በግድ እየተዘጋ በፖሊስ የሚደረገውን ጥበቃ ተችቷል፤ ቋሚ ሲኖዶሱ፥ “በስሜ የተደረገ እንጂ የእኔ ውሳኔ አይደለም፤” ሲል አስተባብሏል፤
• የጠቅላይ ቤተ ክህነት ፀረ ኮቪድ-19 የተስፋ ልኡክ ዐቢይ ግብረ ኀይል፣ ሪፖርቱን ለምልዓተ ጉባኤው አቅርቧል፤
• አስቸኳይ ዐዋጁን በማስፈጸም ሰበብ፣ ፖሊስ፣ በአገልጋይ ልኡካንና ምእመናን ላይ ጥቃቶችንና ማጥላላቶችን መፈጸሙ ቅዱስ ሲኖዶሱን አሳዝኗል፤
• ማንም እገዛ ሳይጠይቃቸው በበሯ ቆመው እየተሳደቡ እና እየደበደቡ ከፍተኛ የኀይል ርምጃ መውሰዳቸው ሳያንስ፣ ሥርዐተ አምልኮዋን የሚያጥላሉ የሌላ እምነት ተከታይ ፖሊሶችም እንዳሉበት በሪፖርቱ ተገልጿል፡፡
Filed in: Amharic