>

"...አሁንም አማራው በጥይትና በቀስት እየተገደለ ፣ እየተሳደደ ነው! " (ግርማ አሸብር)

“…አሁንም አማራው በጥይትና በቀስት እየተገደለ ፣ እየተሳደደ ነው!”

ግርማ አሸብር

ከአምስት ሺህ በላይ ተፈናቃዮች ከድንበር እንዳይወጡ በቤንሻንጉል ፀጥታ አካላት ታግተዋል!
 
ከቤንሻንጉል ጉምዝ ተፈናቅለው በመቶዎች የሚቆጠሩ አማራዎች ባህርዳር ገብተው ሁለተኛ ቀናቸው ነው። አናግሬያቸው ነበር። ከአምስት ሺህ በላዮች ከድንበር እንዳይወጡ በቤንሻንጉል ፀጥታ አካላት ታግተዋል።
“…አሁንም አማራ በተናጠል እየተገደለ ነው። የማምቡክ ወረዳ የመንግስት አካላት ጉምዝን እያስታጠቁ ከዘራ እንኳ ባልያዝንበት እየገደሉን ነው።
የጉምዝ ታጣቂዎች ክሪሽና ቀስት ይዘው እየተንቀሳቀሱ ያልታጠቀውንም አካል እያስታጠቀ ሲያስመታን የኖረው ወረዳው ነው፤ እኛ በባዶ እጃችን ብትር እንኳ ሳንይዝ እያለማን እነሱንም እያበላን ነው የቆየነው፤ የግጉምዝ ወረዳውና የማምቡክ ታጣቂዎችና ቀስተኞች ሊያስቀምጡን አልቻሉም፤ አፈናቀሉን የሞተው ሞቶ ያቃጠሉትን አቃጥለው የዘረፉትን ዘርፈውን ጥለን መጥተናል ፤ የፍትህ ያለህ..” ይላሉ ተፈናቃዮቹ።
ትናንት (02/09/2011)ከጥዋትና ከሰዓት ርዕሰመስተዳድር ቢሮ ሄደው ሰው የለም የሚልመልስ ነው የተሰጣቸው።
ሁሉም ንብረታቸውና ወረታቸው እንደወደመና እንደተቃጠለባቸው ነግረውኛል። ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስትያንም ለማረፊያ አላስገባቸው ብለው ከደጀሰላሙ በር ላይ በግምት ከመቶ በላይ ሰዎችን እስከጓዛቸው  ተመልክቻቸዋለሁ።
የባህርዳር ወጣቶች የተገኘውን የእለት ጉርስ ይዘው የጠየቋቸው ቢሆንም ለዘላቂ መፍትሄ ግን መንግስት አለ እንደሁ ተገቢውን እገዛ ሊያደርግ ይገባል።

 

 

 

Filed in: Amharic