>
11:51 am - Sunday December 4, 2022

ጣና አይናችን እያየ ደረቅ መሬት መሆኑ ነው፤  እንድረስለት‼️(ታደለ ጥበቡ)

ጣና አይናችን እያየ ደረቅ መሬት መሆኑ ነው፤  እድረስለት‼️

ታደለ ጥበቡ

ይኼ በብዙሃ ሀብት በዩኔስኮ የተመዘገበ ሐይቅ እየደረቀ ነው።ባህላዊ ታሪካዊ፣ጂኦሎጂካዊና ሥነ ውበታዊ እሴታችን አይናችን እያየ እየከሰመ ነው።
•••
ጣና በኢትዮጵያ ትልቁ ሐይቅ ነው። በውስጡ ከ37 በላይ ደሴቶች ይገኙበታል።ግዮን አቋርጦት ያልፋል።የኖኅ መርከብ  ያረፈችበት የአራራት ተራራ፣፣ክብራን ገብርኤል፣የዳጋ ኢስጢፋኖስ፣የጣና ቂርቆስ እና ሌሎችም ገዳማት ይገኙበታል።ነገርግ   እንዲጠፋ ተፈርዶበታል‼️
•••
በታሪክ ጣና  ታቦተ ጽዮን ያረፈችበት፣ሊቀ ካህናት  አዛርያስ በክብር የተቀበረበት፣ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ ከዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር 3 ወር ከ10 ቀናት የተቀመጠችበት ሐይቅ እንደሆነ ተመዝግቧል።በ21ኛው መክዘ  ደግሞ “ጣና እምቦጭ በተባለ አረም ነው የደረቀው” የሚል ታሪክ አስቀምጠን እንዳናልፍ ስጋቴ ነው።
•••
•ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ እምቦጭ አረምን ለማጥፋት የገቡትን ቃል አላከበሩም።
• የክልሉ አካባቢ ጥበቃ ቢሮ 91% የእምቦጭ አረም ከጣና ላይ አስወግጃለሁ እያለ የሀሰት ሪፖርት ሲያቀርብ ከርሟል።
•የባህር ዳር ዩንቨርሲቲ እምቦጭን የሚያጠፋ ጢንዝዛ እያራባሁ ነው በማለት  በሚሊዮኖች  የሚቆጠሩ  ገንዘቦችን ከአባከነ በኋላ የምርምር ሥራው ዜሮ ሆኖ ቀርቷል።
•የጎንደር  ዩንቨርስቲ ደግሞ ማሽን ሰርቻለሁ ብሎ በሰበር ዜና ነግሮን ማሽኑ ወደብ ላይ ተሰብሮ ቀርቷል።
•የወልድያ ዪንቪርስቲም በምርምር አገኘሁት ያለውን ኬሚካል ሞክሮ ውጤት አልባ ሆኖ ቀርቷል።
•በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ ሰዎችግሞ ማሽን ገዝተናል ካሉ 2 አመት አለፈው።
♦ በአጠቃላይ ሁሉም ነገር ውሸት ነበረ።ከውጪም ከውስጥም የተሰበሰበው ገንዘብ ወደ ግለሰቦች ኪስ ገብቷል።አርሶ አደሩ ደግሞ ጣናን ለመታደግ በባዶ እጁ ሲደክም ይውላል።
ጣናን እንታደግ‼️
Filed in: Amharic