>
2:28 pm - Monday January 30, 2023

የብሔርተኝነት ወግ ...  (ወንድወሰን በየነ)

የብሔርተኝነት ወግ … 

ወንድወሰን በየነ
 ኦሮሞዎቹ እነ ዶክተር ገመቹ  ምንሊክ 5 ሚሊዮን ኦሮሞ ገደለ ፤ እነ አቶ ፀጋየ አራርሳ ራስ ዳርጌ ወረርሽኝ በጋቢው ይዞ መጥቶ ኦሮሞን ገደለ ሲሉ ምንም አይከነክናቸውም ።
 
* ትግሮች ለምለሚቱን ትግራይ ምንሊክ አድዋ ብሎ ዘምቶ በሰበቡ ትግራይን በመውረር ደኗን አወደመና በረሃ አደረጋት እያሉ ይቀሰቅሱ ነበር ። ይህ ዓይነቱ የተጠቂነት ብሔርተኝነት እሳቤ…
፩) የጥንቷ ሮም ረሙስና ሮሙለስ የተባሉ ማርስ ከተባለው የጦርነት አምላክ ዝርያ ያላቸው አንበሳና ነብር ባሳደጋቸው የሁለት ወንድማማቾች ምናባዊ ተረት ብሔርተኝነቷን ገንብታ ገናና ሆና ነበር ። አውሮፓውያን ሕዝባቸውን በብሔርተኝነት ለማጦዝ “አያቶቻችን አንበሳና ነብር ይገሉ ነበር” ብለው ሲቀሰቅሱ አንበሳና ነብር ግን ባገራቸው የለም ነበር ። ይህ ዓይነቱ ብሔርተኝነት አጼ የኩኖ/ይኩኑ አምላክ ቀዳማዊ አጼ ምንሊክና ሠለሞናዊ ስረዎ መንግሥት ብሎ የመሠረተው ዓይነት ነው ። ዓላማው ሌላውን ጠላት ከማድረግ ራሱን የተለየ በማድረግ ሌላው እንዲቀበለው ማድረግ ነው ።
፪) በአገራችን ኦሮሞዎቹ እነ ዶክተር ገመቹ  ምንሊክ 5 ሚሊዮን ኦሮሞ ገደለ ፤ እነ አቶ ፀጋየ አራርሳ ራስ ዳርጌ ወረርሽኝ በጋቢው ይዞ መጥቶ ኦሮሞን ገደለ ሲሉ ምንም አይከነክናቸውም ። ትግሮች ለምለሚቱን ትግራይ ምንሊክ አድዋ ብሎ ዘምቶ በሰበቡ ትግራይን በመውረር ደኗን አወደመና በረሃ አደረጋት እያሉ ይቀሰቅሱ ነበር ። ይህ ዓይነቱ የተጠቂነት ብሔርተኝነት ሰርቦች ከ600 ዓመት በፊት የነበረውን ንጉሣችንን ላዛርን የገደሉት የአሁኖቹ ቦስኖች ናቸው ብለው የላዛር አፅም ነው የሚሉትን ሰብስበው በወሰካ እያዞሩ ሕዝቡን የቀሰቀሱበት ታሪክ ጋር ይመሳሣሠላል ።
ባለጌው የሰርብ ብሔርተኝነት በኦቱማኖች ተሸንፈን ንጉሣችንን አስገድለን ባለመበቀላችን በሰርብ ኮረብታዎች ላይ ይፈነድቁ የነበሩ አበቦች አኩርፈውና ጠውለገው ቀሩ እያለ ያስተምር ነበር ። ይህ የሰርብ ብሔርተኞች የብልግና ተረት በአገራችን ተስፋየ ገብረ ዕባብ በተባለ ፀረ አማራ ተቀድቶ ምንሊክ ኦሮሞን ሲያሸንፈው ቡርቃ የተባለ አርሲ አካባቢ ያለ ወንዝ አፍሮና ተናዶ መሬት ውስጥ ተደበቀ ተብሎ ተጽፏል ። ይኸው የቡርቃ ዝምታ የሚባል መጽሐፍ ቡርቃ ተነስ አማሮች አርባጉጉ አሉልህ በቆንጨራ ቆራርጣቸው እያለ ለበቀል ይጠራል ። የሰርቦቹና የፀረ አማሮች ብሔርተኝነት የተገነባው ሌላውን በመጥላት ሲሆን ለዚህ ግብዓት ማንኛውንም ውሸት እየዋሸ ሕዝቡን ይቀሰቅሳል ።
፫) አውሮፓውያን ከሕዳሴ ዘመናቸው ቡኋላ በኢንዱስትሪው እየገሠገሡ ሲሄዱ ራሳቸውን ከሌላው ዓለም የተሻሉ ሆነው አግኝተውታል ። ይህ የኢንዱስትሪ አብዮት እየገሠገሠ ሲሄድ ከእኛ በታች ነው ያሉትን የጥቁር ጉልበት ለኢንዱስትሪ አብዮታቸው ግብዓት አድርገዋል ። የባሪያ ንግድና ቅኝ ግዛት የፈረንጅ ብሔርተኝነት ውጤት ነበሩ ።
፬) የአማራ ብሔርተኝነት በወቅታዊ ሁነት ላይ አፀፋ በመስጠት ላይ ያተኩራል ። ብሔርተኝነቱ ጠላት ብአዴን ሰርጎ ስለገባበት መጎልበት ስላልቻለ አፀፋው ከሚያርፍበት በደል ጋር እኩል አልሆነም ። ይህም ማለት for every action force there is an equal and opposite reaction force የሚለው ሕግ ላይ አልደረስንም ።
ብሔርተኝነቱ ውስጣዊ ችግሩን ፈትቶ በጠራ አቋም ላይ ሌላኛውን የትግል እርምጃ ሀ ብሎ ሲጀምር 86 አማራ ገሎ የሚጎማለል አይኖርም ። አማራን የሚያፈናቅል አመረራ ብሔርተኝነቱ ባፈራቸው ኮማንዶዎች የአፀፋ እርምጃ ይወሰድበታል ። ይህ የጊዜ ጉዳይ እንጂ የአማራ ብሔርተኝነት ራሱን የሚያስከብርበት ደረጃ ላይ መድረሱ አይቀሬ ነው ።
ነገር ግን ይህ ዓይነቱ ብሔርተኝነት በጥንቃቄ ካልተያዘና የሚፈልገውን ግብዓት ካላገኘ ወደ tal narration (ወሬ ስለቃ) ይገባል ። ልክ በተራ ቁጥር አንድ ላይ ያለውን ዓይነት ተረት ለድክመተችን መደበቂያ በማድረግ ብሔርተኝነቱ አሁን ላይ የሚጠይቀንን ግብዓት ባላየ ማለፍ እንጀምራል ። አንተ ማን ነህ ሲባል አባቴ ላልይበላን ገንብቷል የሚል ያልተጠየቀውን የሚቀባጥር ሰነፍና ጅል ብሔርተኝነት ይሆናል ። ለዚህ ሁሉ መጀመሪያው የብአዴንን ተላላኪዎች ማወቅና ማግለል ነው ።
Filed in: Amharic