>

ዳንኤል ሺበሺ ሰላም በር ላይ  በ"ማግለያ ጣቢያ"  ስም ታስሯል!!! (የትግል አጋሩ ተክሌ በቀለ) 

ዳንኤል ሺበሺ ሰላም በር ላይ  በ”ማግለያ ጣቢያ”  ስም ታስሯል!!!

የትግል አጋሩ ተክሌ በቀለ 
እንደ ህዝብ  በመታገላችን ህወሓት ከአራት ኪሎ ወጥታለች ፡፡ ጭካኔዋ ቀጥሎ በጠራራ ፀሃይ ትግራይ ላይ በኮረና ሰበብ  ሰው በጥይት እየገደለች ነው ፡፡ የትግራይ ወጣት ከበሰበሰው የድርጅቱ አመራር ጋር ትንቅንቅ ላይ ይገኛል፡፡
ህወሓት ከ 4 ኪሎ ብትወጣም ኢህአዴግ ግን  ጨርሶ አልወጣም ፡፡ ብልፅግና ውስጥ ተደብቆ እያደባ ነው ፡፡ የምናስተውለው በደል፤አድልዎ፤የሃብት ወረራ እና የግልፅነት ጉድለት የድብቁ ኃይል መገለጫ ነው ፡፡ ዶ/ር ዐብይ አህመድና ቡድናቸው  ብልፅግና የሚባል ምቹ መደበቂያ ፈጥረውለታል ፡፡ ሲጠናበት እርስ በርሱም ይባላል ፡፡ ዙሪያቸውን ከቦ ከቴክኖክራቱ ጋር እየተሸሸ እንደ ሀገር ይጫወትብናል ፡፡ በሂደትና ብፍጥነት ፓርተው ራሱን ካላጠራ  ገና ምን ሊፈጠር እንደሚችል መገመት ይከብዳል ፡፡
ወንድማችን ዳንኤል ሽበሺ ለቤተሰብ ጉዳይ በሳለፍነው ሳምንት ሓሙሰ ግንቦት 6/ 2012 ከአዲስ አበባ ወደ 400 ኪ.ሜ ርቃ ወደ ምትገኘው ወደ ደቡብ ክልል  ሰላም በር ከባለቤቱ እና ሌሎች ሁለት የቤተሰቡ አባላት ጋር ይሄዳል ፡፡ በስልክ በነገረኝ መሰረት በተለያዩ ምክንያቶች በዚያን እለት ከ 24 በላይ ሰዎች ወደ ከተማዋ ከአዲስ አበባ የገቡ ነበሩ ፡፡ ከእነዚህ ሰዎች ውስጥ ከሄዱ ከሶስት ቀናት በኃላ እሁድ እለት ወደ ማታ ላይ (12፡15) በአስቸኳይ ግዜ አዋጁ መሰረት ኳራንታይን ውስጥ መግባት አለብህ ብለው ለይተው በመውሰድ ውሃ፤መብራት እንዲሁም ከበሽታው ጋር በተያያዘ በትንሹ ሊሟሉ የሚገባቸው ነገሮች የሌሉበት ቦታ ላይ ለይተው አስቀምጠውታል (አስረውታል ቢባል ይሻላል) ፡፡
ይህን ሚያደርገው የወረዳው ም/ አስተዳዳደሪ የሆነ ከዚህ በፊትም ከዳንኤል ሽበሺ እና ተቃዋሚዎች ጋር ትንቅንቅ ላይ የነበረ ኢህአዴጋዊ ሰው መሆኑን ነግሮኛል ፡፡  ሰበብ እየፈጠሩ ብቀላ የኢህአዴግ ነባር ባህሪው ነው ፡፡
አሁን ተገልሎ ስለሚገኝበት ቦታ ሲያወራ የወባ ትንኝ፤ጉንዳኖች፤ እባብና ሌሎች  ጎጂ እንሰሳት የሚርመሰመሱበት ለጉዳት የሚዳርግ ከደረጃ በታች የሆነ  ማቆያ መሆኑን ነው ፡፡
 በተጨማሪም “ድብደባ አልተፈፀመብኝም እንጂ ወደ ሌላኛው ማእከላዊ ገባሁ ፡፡ ኃላፊነት እንደሚሰማው ሰው ፤ በፓርቲ እና በግል ወስኜ ደሜን ጨምሮ ያለኝን ሁሉ  ለወገኔ ለመስጠት እንደተዘጋጀ ሰው እስከ ዛሬ በትእግስት መጠበቅ ግድ ቢለኝም የብልፅግና ኢህአዴጎች ትእግስትን የሚፈታተን ከመሆኑም በላይ ህዝብ ይስማው የሚል ድምዳሜ ላይ ደረስኩ ይላል”  ፡፡ማናችንም ከህግ በታች ነን ፡፡ የምናወግዘው ጉዳዩ ሌላ ስለሆነ ነው ፡፡ከተመቻቸለት ዝርዝሩን ከራሱ እንሰማ ይሆናል ፡፡ ማንም የሚመለከተው አካል ሁሉ ዳንኤልን ደውሎ ማነጋገር ይችላል ፡፡
Filed in: Amharic