>

የተገደሉት ወጣቶች ርቀት ባለመጠበቃቸው ነው!!! የክልሉ መንግስት **ኮረና ያልገደላቸውን የገደለ መንግስት ነው* የክልሉ ህዝብ

 

የተገደሉት ወጣቶች ርቀት ባለመጠበቃቸው ነው!!!
የ ክልሉ መንግስት
*ኮረና ያልገደላቸውን የገደለ ከኮረና የከፋ መንግስት ነው**
የክልሉ ህዝብ

የሻምበል ገ/እግዚአብሄር

፨ በትግራይ የሞቱት ወጣቶች ርቀት ጠብቁ ሲባሉ ፍቃደኛ ያልሆኑ ግለሰቦች እንደሆኑ በመግለጽ ለማስተባበል ወደ ሚድያ የመጡት የህወሃት ባለሥልጣናት ሲናገሩ :- በኮረና ምክንያት የተላለፈውን ህግ በመጣስ ህገወጥ ስብሰባ ያደረጉ ወጣቶች ተራርቀው ለመቆም ፍቃደኛ ባለመሆናቸው እርምጃ ተወስዶባቸዋል።
፨ በማለት በወጣቶቹን የግፍ ግድያ የተቆጣውን የህብረተሰብ ክፍል ያረጋጋልናል ያሉትን መግለጫ ሰጥተዋል።
ያም ሆኖ በርካታ ወጣቶች በክልሉ ልዩ ሃይል ሲረገጡና ሲደበደቡ ፤የተደበደቡበት ሰንበር የሚያሳይ ምስሎች ይዘው አደባባይ እየወጡ ነው፤ ኮረና ያልገደላቸውን የገደለ ከኮረና የከፋ መንግስት ነው የሚሉ የተቃውሞ ድምጾችን የሚያሰሙ ወጣቶች መንገድ በመዝጋት ድንጋይ በመወርወር ተቃውሞአቸውን በመግለጽ ላይ ናቸው።
የአዲግራት ወጣቶች በትግራይ ፖሊስ በመቀሌ ከተማ በተገደለው ሰው የተበሳጩ የአዲግራት ከተማ ነዋሪዎች ዛሬ ከጠዋት ጀምሮ አደባባይ በመውጣት በትግራይ መንግስት ላይ ተቃውሞ እያሰሙ ነው።
ወጣቶች በአዲግራት ከተማ አለ የሚባለው ትልቁ ተራራ ላይ በመውጣት ትልልቅ ቋጥኝ ድንጋዮችን ቁልቁል ወደታች አስፓልቱ ላይ በመልቀቅ ዋናውን መንገድ ዘግተውታል።
የከተማውን የፖሊስ ማዘዢያ ጣቢያም በእሳት አቃጥለውታል።
ነገሮች ሁሉ ከክልሉ አቅም በላይ እየሆነ ነው!!
ሁሉም ዲክታተሮች ለዘልአለም የሚኖሩ ይመስላቸዋል፤ የቁርጥ ቀን ሲመጣ ግን፦
እንደ ሣዳም ሁሴን ከአይጥ ጉድጓድ ተጎትቶ በእራሱ ተቀናቃኝ ገመድ በአንገቱ ይጠለቅለታል!።
ልብ ካለው!ነብስ ከያዘው እራሱን እንደ ሂትለር ገሎ ፍቅረኛውንም ጨምሮ ይዞ ይሰናበታል!።
እንደ መንግስቱ በለስ ቀንቶት ያላመለጠና በስደት የመኖር ያልታደለ!።እስር ቤት ሰብሮ ቢያመልጥም እንደ ቤኒቶ ሙሰሊኒ በገዛ ሕዝቦቹ ቁልቁል ተሰቅሎ ሞት እየናፈቀው ዘገምተኛ ሞት እንዲሞት ይገደዳል!።
የወያኔ ኦቦዎች! የኢትዬጵያን ሕዝብ በጅምላ ሲገድሉ፥ሲዘርፉና በምድር ያለ ስቃይ ሲፈጽሙ ኖረው እድላቸው የመሰሎቻቸውን ጽዋ እንዲጎነጩ አላደረጋቸውም!።
ሸሹ!።
ያ ሚስኪን የትግራይ ሕዝብ እጁን ዘርግቶ ተቀበላቸው።መደበቂያ፣መሸሸጊያ ሆናቸው!።
“የዘሬ ያንዘርዝረኝ” ነውና።አንባገነኖች ውለታ አልፈጠረባቸውም።ብታበላው፣ብትሸሽገው፣”የእኔ ነህ!”ብለህ ብታሞካሽህ አይቀርልህም!።
ይነሳብሃል!
ያሳድድሃል!።አንተን በመግደል ጭካኔውን፣ምህረት የለሽ መሆኑን ለሌሎች በማሳየት እንዲፈራ!እንዲከበርና እንዲገበር ያደርጋል!።
ኦቦዎቹ ሰሞኑን በምስኪኑ የትግራይ ወጣት ላይ የሚያራምዱት ግድያ አዲስና ከመሰል አንባገነኖች የተለየ አይደለም!።
እንዴት!?
ባለ ሁኔታ እንደሚሰናበቱ ለመገመት ይቸግራል!።ግልጹና እውነቱ ግን በኢትዬጵያ ሕዝብ ለ27 ዓመታት የፈጸሙት ግድያና ግፍ ለረጅም ጊዜ በትግራይ አይቀጥልም!።
የእጃቸውን ያገኛሉ!።

ህወሓት ትውደም! የትግራይ ሰፊ ሕዝብ የነጻነት ትግል ያቸንፋል!!

ነፃነት ለትግራይ ህዝብ።

Filed in: Amharic