>

በወያኔ ህግ ውስኪ ሠፈር ጠላ መጠጣት ያለፍርድ ያስገድላል! (ታዬ ደንደኣ)

በወያኔ ህግ ውስኪ ሠፈር ጠላ መጠጣት ያለፍርድ ያስገድላል!

ታዬ ደንደኣ
* የወያኔ እና የጓዶቹ አንድነት እና ሦስትነት
* ዉሸት፣ ክህደት እና አስመሳይነት!
* አዳግራት ላይ በህወሀት ጥይት ከተመቱት ወጣቶች አንዱ (ደረቱ ላይ የተመታው) ዛሬ ህወቱ ማለፉ ተሰምቷል
ክህደት፣ ዉሸት እና አስመሳይነት የወያኔ መለያ መሆናቸዉን ዓለም ያዉቃል። ግራዝማች ግሪሳን ጨምሮ የወያኔ ጓዶችም እነዚህን ባህሪያት ተላብሷል። በዚህ ባህሪያቸዉ ብዙዎችን አታሏል። አሁን ደግሞ ራሳቸዉን ጭምር እያታለሉ ይገኛሉ!
ትላንት መቀሌ ላይ ሁለት ወጣቶች በወያኔ መገደላቸዉ ታዉቋል። ወያኔ ግን እንደልማዱ አንዱን ክዷል። ሁለተኛዉን ደግሞ “ጠላ ስለጠጣ ገደልኩት” በማለት መግለጫ አዉጥቷል አሉ። ለካ በወያኔ ህግ ውስኪ ሠፈር ጠላ መጠጣት ያለፍርድ ያስገድላል!
ደግሞ ግራዝማች ግሪሳ ሁኔታዉን በዝምታ ማለፉ በጣም ይገርማል! ግድያዉ ባህር ዳር፣ ሀዋሳ ፣ አሶሳ፣ ጅጅጋ ፣ ሰመራ፣ ጋምቤላ ወይም አዲስ አበባ ቢሆን በOMN ትንታኔ ይሰጥበታል።
ሌላም ገራሚ ነገር አለ። ፕሮፌሰር እንዲሪያስ የወያኔ ዋነኛ ምርኩዝ እንደነበሩ ይታወቃል። እንዲያዉም አንዳንዶች “በህይወት ያለ የመለስ አካል” ይሏቸዋል! ይህ ሰዉ በ1996 ዓም በአዲስ አበባ(ፊንፊኔ) ምክንያት እኔን ጨምሮ 350 የኦሮሞ ተማሪዎችን
ያለምንም ጥፋት በፖሊስ አስቀጥቅጦ ከአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ አባሯል። ትላንት ግራዝማች ግሪሳ ፕሮፈሰር እንዲሪያስን “ታላቅ ጀግና” አድርጓል።
 በFB እና በTV ሲዘምርላቸዉ አድሯል። ከትላንት በስትያ ደግሞ በተመሳሳይ ቅላፄ ስለፊኔፊኔ ልዩ መብት ሲጨፍር ዉሏል። ግን “የፊንፊኔ ተቆርቋሪ ነኝ” የሚል ታጋይ እንዴት ፕሮፈሰር እንድሪያስን ጀግናዉ ያደርጋል? የወያኔና የጓዶቹ ማንነት
እና ምንነት እንዲህ ራሱን በራሱ ያጋልጣል። ወያኔ፣ ግራዝማች ግሪሳ እና ኦፌኮ አንድም ሦስትም ናቸዉ የምንለዉ በተጨባጭ ምክንያት ነዉ! ክህደት እና ዉሸት የተጠናወታቸዉ አስመሳዮች ናቸዉ! አሁን ባለዉ ሁኔታ ህልውናቸዉ ያሰጋል። በህይወት ይቀጥሉ ዘንድ የባህል አብዮት ያስፈልጋቸዋል!
እኛ የብልፅግና ልጆች ነን! በመደመር መንገድ ለኢትዮጵያ ብልፅግና እንጓዛለን! በእዉነት እና በእዉቀት ግፈኞችንና አስመሳዮችን
በማሸነፍ የሀገራችንን ሁሉአቀፍ ብልፅግና እንደምናረጋግጥ እርግጠኞች ነን!
Filed in: Amharic