>

አባይ ደሜ ነው!! (ተስፋዬ በየነ)

አባይ ደሜ ነው!!

ተስፋዬ በየነ

የጎልያድ ግዝፈትና የጦር  ብዛት በትንሿ የዳዊት ጠጠር ተዘርሮ ወድቆ ከመሸነፍ አላዳነውም፦
ብልኮ ቢወፍር መርፌ ነው የሚሰፋው እንዲሉ የኢትዮጵያ መንግሥት የህዳሴው ግድብ የውሀ ሙሌትን በሀምሌ ወር እንደሚጀምር  ማስታወቁን ተከትሎ ፈርኦናዊቱ ግብጽ  ከፍተኛ የሆነ ደጦር ዝግጅት ልምምድ በማድረግ ላይ  ትገኛለች፡፡ከምድር  ጦር እስከ አየር ሀይሏ ድረስ  ጭንቅ ውስጥ ተወጣጥራለች ፡፡
ያለገሉ  ተዋጊ ጀቶችን በአሜሪካው የጦር ካፖኒ እድሳት እስከ ማድረግ  ድረስ ዝግጅት ላይ ትገኛለች ፡፡ታዲያ  ይህ ሁሉ  የጦር ውጊያ ዝግጅት የሲናይ በርሀን ከእስራኤል ለማስመለስ ሳይሆን       ኢትዮጵያን ለመውረር መሆኑ ጸሀይ የሞቀው  እውነታ ነው፡፡
ግብጽ በታሪኳ 12 ጊዜ ኢትዮጵያን  የወረረች ሲሆን በለስ ቀንቷት ለመሀላ አንድ ጊዜ  እንኳ  ማሸነፍ  አልቻለችም፡፡ ሁሉም  የጦርነት ውጊያ ውሎ ድሎቹ  የኢትዮጵያ ነበሩ፡፡
ምክንያቱም ግብጽ የሌላት ብቸኛ አምላካዊ ጸጋ ኢትዮጵያ  አላት ፡፡እርሱም # የአልደፈር ባይነት ስነ ልቦናና ወኔ ” ናቸው፡፡
ዘመናዊ መሳሪያ ካፍ እስከ ገደቡ ሞልቶ ቢደረደር ተዋጊ  ስነ ልቦና (courage)ከሌለ ከንቱና ባደዶ ነው፡፡ ከእንግሊዝ እስከ ጣሊያን ፤ከቱርክ እስከ ፖርቱጋል ፤ከአሜሪካ እስከ ፈረንሳይ ኢትዮጵያን ለማንበርከክ ያሸረቡት ሴራ አልነበረም ነገር ግን ሉዓላዊ ክብሯን ከቶ ማሸነፍ ና ማንበርከክ አልቻሉም፡፡ ምክንያቱም ሲወርድ ሲወራረድ ከትውልድ ትውልድ ተሸጋግሮ የመጣ ህዝባዊ የአልደፈር ባይነት ወኔ ሞልቶ ተርፏልና፡፡
ስለዚህ  የሚዋጋው የመሳሪያና የወታደር ብዛት ብቻ ሳይሆን  “ጽኑ ልብና ህዝባዊ አንድነት” ነው፡፡ግብፅ የተለያዩ ሴራዎችን በመጠቀም የኢትዮጵያን መንግሥት ለመጠምዘዝና ለማዳከም ሞክራለች፡፡የውስጥ ቅጥረኛ ባንዳዎችን በፋይናንስ ከመደገፍ እስከ ዓለም አቀፍ  የፋይናንስ የበዳሪ ተቋማትን ተጽዕኖ እስከ ማሳደር ያልፈነቀለችው ድንጋይ አይገኝም ፡፡ግን ሁሉም ሴራዎች አልተሳኩም ፤ወደ ፊትም አይሳኩም፡፡
የውስጥና የውጭ  የተቀናጀ ተጽእኖው ቢበረታባትም  ኢትዮጵያ የህዳሴግድብ (GERD)ግንባታን ከማስቆም ያገዳት ምድራዊ ሀይል የለም ፡፡ በተያዘለት  እቅድ ለማጠናቀቅ በቁጭት  እንደቀጠለ ነው ፡፡ከልጅ እስከ አዋቂ ፤ከተናቀው እስከ ተከበረው ፤ ከሙስሊም እስከ   ክርስቲያኑ ፤ከድሀው እስከ ባለሀብቱ ፤ከአርሶ አደሩ እስከ ከተሜው ሁሉም የበከሉን ጠጠር ወርውሯል ፡፡አባይ የጋራ   የተፈጥሮ ሀብታችን  ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያዊነት በደም ያስተሳሰረ ብሄራዊ Iconናችን ነው፡፡እንደ ዓይኑ ብሌን ይጠብቀዋል ፤ይሳሳለታልም ፡፡
የመቶ አስር ሚልዬን እጆች አሻራ ያለበት የትውልዱ ታሪካዊ ቅርስ  ነው፡፡ ፍርሀትንና ድንጋጤን ጀግኖች አባቶቻችን አላወረሱንም ፡፡ይልቁንስ ጀርባን ሳይሆን ግንባርን ፤መሸሽን ሳይሆን በክብር ተፋልሞ መውደቅን  ፤ መውረርን ሳይሆን ወራሪ መከላከልን ፤መሸነፍን   ሳይሆን ማሸፍን  ወርሰናል፡፡ማሸነፍ አርማ ምልክችን unique መገለጫችን  ነው፡፡
ስለሆነም  በግብጽ በኩል ሊቃጣ የሚችለውን      ማንኛውም የጦርነት ትንኮሳ  ድባቅ መተንና  አይቀጡ ቅጣት ቀተን ድህነትን ሳይሆን ብልጽግናን፤ልመናን ሳይሆን ለጋሽነትን ለተተኪው ትውልድ እናወርሳለን ፡፡ በርግጥ  ሰላም ናብልጽግና  የስራና የጀም ውጤት እንጅ  በራሱ የሚታደል ችሮታ አይደለም፡፡አሜሪካ አሜሪካ ፤እስራኤል እስራኤል   የሆኑት  ከብዙ ተስፋ አሰቆራጭ ተጋድሎ ቡሗላ   እንጅ በተዓምር ከላይ  ከሰማይ በችሯታ መልክ ታደድውት  አይደለም፡፡ ምኞት  በስራ መገለጥ ይኖርበታል፡፡ነገ ሰላሟና ከክብሯ የተጠበቀ   ኢትዮጵያን  ለተተኪው ትውልድ   ለማውረስ  ዛሬን   ግድ ለሀገር ሉዐዓላዊነት ሲባል  መስዋዕትነት መክፈል ግድ ይላል ፡፡ምክንያቱም ሰላም  የስራ  ውጤት ናትና፡፡መቻቻል ፤መቻቻል እያልን እንደ እርጉዝ ሴት ቀን መቁጠር አይገባም፡፡የሀገርና ህዝብ  ሉዓላዊነት ለድርድር የሚቀርብ ጉዳይ አይደሉም፡፡የደም  የአጥንት ትልቅ ዋጋ ተከፍሎባቸዋልና  ፡፡
 ስለዘህ መንግሥት በያዘው የትግል ወኔ  ቆፍጠን ብሎ   የዲፕሎማሲ ስራውን ማስቀጠል ይኖርበታል፡፡እንደ አስፈላጊነቱ ሰርገኛ መጣ በርበሬ ቀንጠስ እንዳይሆን እንደ     የኢትዮጵያ  የቁርጥ ቀን ልጆቿን በስነ ልቦናና በስልጠና ማዘጋጀት ያስፈልጋል ፡፡ ጥላት በተዘጋጀበት ወርድና ቁመና  ልክ  መዘጋጀት ያስፈልጋል፡፡
ሌላው ሳልጠቅሰው የማላልፈው ጉዳይ ቢኖር  በኡንቨስትመንት ስም   ወደ  ኢትዮጵያ የገቡ ግብጽ  ኢንቨስተሮች( ወታደራዊ ሰላዮች) ላይ ጥብቅ  ክትትል  ቢደረግ ተገቢ   ነው፡፡ለምሳሌ  በአማራ ክልል  አባይ ዙሪያ በፕላስቲክና ፖይፕ  ማምረት ዘርፍ የተሰማሩ የግብፅ ባለሀብቶች ድብቅ ዓላማቸው  ሌላ  የደህንነት ተልዕኮ ሊሆን ስለሚችል ጥብቅ ሚስጢራዊ ክትትል ቢደረግ  መልካም ነው ባይ ነኝ፡፡ምንያቱም ከእያንዳንዱ ግብጻዊ  ጀርባ አንድ የአባይ ድብቅ ተልዕኮ አለ፡፡ጠላት የመጣብን በተለያዬ ስልትና  ታክቲክ  ሊሆን ስለሚቸችል ቀድመን   እንደ ንስር  አይን  ልቅም አድርገን ገና ከርቀት አጥርቶ ማየትና ማሰላሰል ግድ ይሏል፡፡
ከዚህ ጋር ትይዩ የሚሆነው ጉዳይ  የኮሮና ቫይረስ  ወረርሽኝን እንደ ምቹ አጋጣሚ  biological  -war በመጠቀም በቫይረሱ የተጠቁ ገለሰቦችን  ወደ ውስጥ ዘልቆ  በመበተን    ሀገራዊ    አንድነትንና የመንግሥትን አቅም ደካማ ና ልፍስፍስ  ለማድረግ ሊጠቀሙበት ስለሚችሉ    በዋና በዋና   የንግድ  ድንበሮች ጥብቅ ምርመራና ኳራታይን     መደረግ ይኖርበታል ፡፡ ምንጩ ያልታወቀ  ህገ ወጥ  የገንዘብና  የጦር መሳረያ ዝውውር ላይም  ብርቱ ጥንቃቄ ሊደረግ  ይገባል ፡፡
የባንዳውያን ከሱዳን ጽንፈኛ ጦር ጋር  የሚታየውን መፈራገጥ በተመለከተ  ለኢትዮጵያ ህዝብ  ግልጽ ጉዳይ  በመሆኑ  ከግብጽ በፊት በቅድሚያ   ውስጣቸችንን ማጥራትና  መደምሰስ ያስፈልጋል፡፡ መረጃና ማስረጃ  አይናቅም ፤ሁላችንም የግብጽን አፍራሽ  እንቅስቃሴ በንቃት  በመታተል የኢትዮጵያን ለሉዓላዊነት አክብረን ፤ እናሰከብር ፡፡
Filed in: Amharic