>

በሶማሌ ክልል "ከፍተኛ ጸብና አመጽ አስተናግዷል" የተባለው የምክር ቤት ውሎ!!! (ሙክታሮቪች ኡስማኖቭ)

በሶማሌ ክልል “ከፍተኛ ጸብና አመጽ አስተናግዷል” የተባለው የምክር ቤት ውሎ!!!

(ሙክታሮቪች ኡስማኖቭ)

የሶማሌ ክልል ምክርቤት የአስራ ሁለት አባላትን ያለመከሰስ መብት አነሳ
 
* በማህበራዊ መገናኛ፣ በቲዊተርና ኢንስታግራም የሶማሌ ክልል ምክርቤት አባላቱ ስብሰባ ረግጠው በመውጣት ፕሬዝዳንት ሙስጠፌ ላይ አመጹ፣ ሊያነሱት ነው፣ ከፍተኛ ጸብ እንደነበረ፣ ሰላም እንደታወከ ተደርጎ ፍጹም ከእውነት የራቀ የውሸት ነጋሪት ሲጎሰም እንደነበረ ብዞዎቻችሁ ታዝባቹአል፡፡ በውስጥ መስመር ስለ ጉዳዩ እንድጽፍላችሁ ጠይቃችሁኝ እንደሚከተለው ያጣራሁትን እውነት አቀርብላቹሃለው፡፡ 
,
የሶማሌ ክልል የሚክርቤት አባለት መደበኛ ሰብሰባ በ ጠዋቱ ሲጀመር  ለምክርቤት አባላት ቀድሞ ምክር ቤቱ ባሳወቃቸው አጀንደዎች ላይ መክሮ ውሳኔ ለማሳለፍ ታቅዶ ነበር፡፡
አጀንዳዎቹም፤
1) የምክር ቤቱን የስደስት ወር ረፓርት መድመጥ፣
2) ከዚህ ቀደም የተካሄደውን የምክርቤቱን መደበኛ ሰብሰባ ቃለ-ጉባኤ ማፅደቅ
3) የመንግስትን የስድስት ወር ሪፓርት ማደመጥ ና መፅደቅ
4) በመንግስት ቀረቡለትን የተለያዩ ሹመቶችን ማጽደቅ
5) የምክርቤቱ አፈ-ጉባዔ ለምክርቤቱ ያስገቡትን ከሀላፊነት ለመነሳት  የመልቀቂያ ጥያቄ ላይ ለመምከርና ውሳኔ ማሳለፍ፣ እና
6)  አዲስና ማሻሸያ የተደረገባቸውን የተለያዩ መስሪያ ቤቶች አዋጆችን መርምሮ ማፅደቅ ነበሩ፡፡
ልክ ስብሰባው እንደተጀመረ፣ የጥቂት የፓርላማው አባላት ጎላ ባለ ድምጽ የፓርላማውን ስብሰባ ማወክ ጀመሩ፡፡ ስብሰባው ይቋረጥና ጉዳያቸው መደመጥ ይጀምራል፡፡ ምክርቤቱ ለዕለቱ ከያዘው አጀንዳ ውጪ የምክርቤቱ አሰራርና ህጋዊ አካሄድ ባልተከተለ መልኩ የፕሬዝዳንቱ እና የአንዳንድ አመራርን ስም እያነሱ ወቀሳ እና ግርግር ለማስነሳት ይሞክራሉ፡፡ በአጀንዳዎቹ ላይ መነጋገር ስንጀምር ቅሬታችሁ ይሰማል፣ አሁን ግን ስብሰባው እንዲጀመር የምክርቤቱ አባላት ቢማጸኗቸውም አሻፈረኝ ይላሉ፡፡
ቅሬታችን እና ሀሳባችን ካልተሰማ በማለት ግርግር እና አምባጓሮ ሲፈጥሩ ምክርቤቱ አጀንዳ ባልተያዘለት ጉዳይ ላይ መወያየት የምክር ቤቱ አሰራር አይፈቅድም ብሎ ምላሽ ይሰጣቸዋል፡፡ ስብሰባው መካሄድ የለበትም ብለው ሌሎች የምክርቤቱ አባላትን በእንቢተኝነት እንዲቀላቀሏቸው ግርግር ለማስነሳት አንባጓሮ ይከፍታሉ፡፡ መወያየት ካልፈለጋችሁ መሄድ መብታችሁ ነው፣ ምክርቤቱ ግን የያዘው አጀንዳዎች ላይ ይመክራል ይባላሉ፡፡
 ያሰቡት አለመሳካቱን ሲረዱ በቀረበው አጀንዳ ላይ አንወያይም በማለት ከስብሰባው ረግጠው ይወጣሉ፡፡ በደረሰኝ መረጃ መሰረት ረግጠው የወጡት ሰባት የምክርቤት አባላት ሲሆኑ ሶስቱ ወንድና አራቱ ሴት ናቸው፡፡ አባላቱ ከወጡ በኋላ በምክርቤቱ መሰብሰቢያ ቦታ በር ጋር ብጥብጥ ለመፍጠር ያደረጉት ሙከራ በስርዓት አስከባሪዎች ከሽፎ እንዲበተኑ ተደርጎ የምክር ቤቱ ስብሰባ በሰላም ተጀመረ፡፡ ረግጠው ከወጡት ሴት የምክር ቤቱ አባላት አንደኛዋ ወደ ምክርቤቱ ስብሰባ መመለስ በመፈለጋቸው ተፈቅዶላቸው ተመልሰው ገብተዋል፡፡
በቀረቡት አንጀንዳዎች ላይ ምክርቤቱ ሰፊ ውይይት ካደረገ በኋላ በአብላጫ ድምፅ እንዳጸደቀው መረጃው ደርሶኛል፡፡ ዘርዘር ያለው የውሳኔው ይዘትን ስላላገኘሁት እዚህ ልጽፍላችሁ አልቻልኩም፡፡
,
ይህን መረጃ የማቀብላችሁ ከተለያዩ ታማኝ ምንጮች የሰበሰብኩት ነው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ እዚህ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሀሰት እና የበሬ ወለደ ፈጠራ ወሬ ተነዝቶ በውስጥ መስመር ብዙ ወዳጆች እባክህ አጣርተህ ንገረን ስላሉኝ ነው፡፡ የፈጠራው ወሬ ምንጭ እያስፔድ ተስፋዬ የሚባል ሰው መሆኑን እና ለእሱም መረጃውን ያቃበሉት ይህን የምክርቤት ስብሰባ ለማሰናከል የወጠኑ ሰዎች መሆናቸውን ለማወቅ ብዙ ምርምር ማድረግ አይፈልግም፡፡ በዚህ የፈጠራ ወሬ ዲቤ ሲመቱ እና የደስታ ሻምፓኝ ሲራጩ የነበሩት የከሰሩ የዲጂታል ወያኔ ነውር ጌጡ የፌስቡክ ሰራዊት ናቸው፡፡
ስብሰባው እክል እንዲገጥመው አንባጓሮ ፈጠሩ ሰዎችን በተመለከተ ይህም መረጃ ደርሶኛል፡-
እነዚህ የምክርቤት አባላት የሀገርና የህዝብ ጥቅምን በግል የስልጣን ጥም የሚሸጡ ናቸው፡፡ እስፖነሰር ያደረጓቸውም ከዚህ ቀደም ይዘርፉ የነበሩ ባለሀብቶች፣ ያለ ጨረታ የክልሉን የኮንስትራክሽን ስራዎች እየተቀራመቱ ሀብት ያካበቱ፣ ለሀገር ልማት ድጋፍ ከክልሉ ማይክሮ ፋይናንስ የወሰዱትን ብድር ሳይመልሱ ባለስልጣናትን በሙስና ለመግዛት የሚፈልጉ እንዲሁም ከቀድሞ የክልሉ አስተዳደር ጋር እጅና ጓንት ሆነው ሲሰሩ የነበሩ የፖለቲካ ነጋዴዎች  መሆናቸውን ለማወቅ ችያለሁ፡፡ ከዚህ ቀደም እንዲሁ የፖለቲካ አለመረጋጋት ለመፍጠር የሞከሩት ሙከራ ክፍል ሁለት ነው የዛሬው ተግባራቸው፡፡
እርግጥ ስብሰባን ረግጦ መውጣት በራሱ ወንጀል አይደለም፡፡ ምናልባት በምክርቤቱ የስብሰባ ስነ-ስርዓት መሰረት ጉዳያቸው የዲሲፕሊን ጥሰቱ ታውቆ እርምጃ ሊወሰድ ይችላል፡፡ የፖለቲካ አለመረጋጋት ለመፍጠር የሄዱበት ርቀት እና ግርግር እንዲነሳ የፈጠሩት ቅስቀሳ ግን አደገኛ ነው የኔ ስጋት ግን ከጀርባቸው ያለው አካል ነው፡፡ መንግስት በከፍተኛ ደረጅ ስረመሰረቱን መርምሮ የእርምት እርምጃ ሊወስድ የሚገባው ይመስለኛል፡፡
የነዚህ የሀገር ሰንኮፎችን በተመለከተ ሁለት ጉዳዮችን ታዝቤያለሁ፤
 
አንድ….. 
አዲስ አበባ ሆነው የክልሉን ሰላም ለመረበሽ የተሰባሰቡ ሰዎች አሉ፡፡ ከሳምንት በፊት የሶማሌ የጎሳ ሽማግሌዎች በጥቅም ለማታለል ያደረጉት ሙከራ አልሳካ ሲል ተራ የስም ማጥፋት ዘመቻ ጀምረው ነበረ፡፡ የክልሉ መንግስት ከሶስት ቀን በፊት ከክልሉ የጎሳ ሽማግሌዎች (ገራዶች እና ኡጋሶች ጋር) ስለክልሉ የሰላም ሁኔታ እና ስለ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ገንቢ ውይይት ማካሄዱን ተከትሎ እነዚህ ቡድኖች ከፍተኛ ብሽቀት ተሰምቶአቸዋል፡፡ የክልሉ መንግስት እና የጎሳ ሽማግሌዎቹ ለሀገር ሰላምና ለህዝብ ጤና በጋራ መቆም አናዷቸዋል፡፡
ሁለት……..
በቅርቡ ባልተለመደ መልኩ በአንድ ዞን ስር ያሉ ሁለት ጎሳዎች መካከል መጠነኛ ግጭት ተፈጥሮ የክልሉ ልዩ ኋይል ግጭቱ ሳይባባስ በቁጥጥር ስር አድርጎት ከግጭቱ ጀርባ ያሉ ግለሰቦች ላይ ምርመራ እያካሄደ ነው፡፡ በኦሮሚያ እና በሶማሌ ህዝቦች ግጭት ለመፍጠር የሚደረግ የማህበራዊ ሚዲያ እንቅስቃሴም ይስተዋላል፡፡ የቀድሞ አስተዳደር አንድ የሚታወቅበት የቢዝነስ አሰራር ግጭት እየፈበረኩ ከግጭት ገቢን መሰብሰብ ነው፡፡ የግጭት ስሱ ቦታዎችን በደንብ ያውቃቸዋል፡፡ አሁን እነዚያ ስሱ ቦታዎች ላይ የቀበሩትን ፈንጂ ለማፈንዳት ብሎም በግጭት እየታመስን ሰላም እንድናጣ የተቀናበረ ሴራ እየተካሄደ ሊሆን ስለሚችል ከፍተኛ ጥንቃቄ መደረግ አለበት፡፡
ይህ መረጃ እንደ አንድሀገሩን የሚወድ ዜጋ ደዋውየ እና የተጣራ ያልኩትን መረጃ በግል የማጋራችሁ ነው እንጂ የክልል መንግስት አቋም አይደለም፡፡ ይፋዊ የክልሉ መንግስት መግለጫም አይደለም፡፡ ሰላምን ለማወክ ቀን ከሌት በዚህ ማህበራዊ ሚዲያ ሴራ የሚሸርቡ ሰዎች አሉ፡፡ እንደ እያስፔድ ተስፋዬ አይነቱ ደግሞ በሬ ወለደ ወሬን እያስተጋባ ጭር ሲል አልወድም ይላል፡፡ ለነዚህ አካላት ምላሽ መስጠት አስፈላጊ በመሆኑ ነው ዛሬ ጊዜ ወስጄ ይህን መረጃ ያጠናቀርኩላችሁ፡፡ ‹ጦር ከፈታው ይልቅ ወሬ የፈታው› እንደሚባለው ሀሰተኛ መረጃን ሰምቶ ማቅለል ሳይሆን በትክክለኛ መረጃ መሞገት አስፈላጊ እንደሆነ አምናለሁ፡፡
የሶማሌ ክልል ምክርቤት የአስራ ሁለት አባላትን ያለመከሰስ መብት አነሳ:-
የሶማሌ ክልል ምክር ቤት ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ 12 የምክር ቤቱ አባላትን ያለመክሰስ መብት ማንሳቱ ታውቀዋል፡፡ ያለመከሰስ መብታቸው የተነሳው ከታች ስማቸው የተጠቀሰው የምክርቤት አባላት የክልሉን ሰላምና የፖለቲካ መረጋጋት ለማወክ በተጨባጭ ማስረጃ የተያዙ፣ በሙስና ተዘፍቀው የህብረተሰቡን ልማት የጎዱ እና በማህበረሰብ ውስጥ የሀሰት መረጃን በማዘዋወር አንዱን ማህበረሰብ በሌላው ላይ ለማነሳሳት እና ግጭት እንዲፈጠር ሲቀሰቅሱ የነበሩና በዛሬው ፓርላማ ግርግርና ረብሻ በማስነሳት የህዝብን ደህንነት ለአደጋ ያጋለጡ የምክርቤት አባላት እንደሆኑ የደረሰኝ መረጃ ያሳያል፡፡
ያለመከሰስ መብታቸው የተነሳ የምክር ቤት አባላት ስም ዝርዝር 
መሃመድ አህመድ ላይሊ
አህመድ አደን አህመድ
አብዲወሊ አህመድ ፋራህ
መሃድ ሃሰን መሃመድ
ሻፊ አሺር
ናዲር ዩሱፍ
አብዱርዛቅ አብዱላሂ
ዩሱፍ ኢልሚ
አህመድ ሃሰን ሂርሲ
ኒምዓን አብዱላሂ ሀመሬ
ዩስፍ አህመድ ሂርሲ
አብድረህማን ኡራግቴ
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
Filed in: Amharic