>

የግብፆች አቋም እንደ ጧት ጤዛ ረገፈ፤ ለድርድርም እጃቸውን ዘረጉ!!! (ቬሮኒካ መላኩ)

የግብፆች አቋም እንደ ጧት ጤዛ ረገፈ፤ ለድርድርም እጃቸውን ዘረጉ!!!

ቬሮኒካ መላኩ
ከአለምአቀፉ የጊዜው ፖለቲካዊ ቀኖና አንፃር ግብፅ ሳትወድ በግዷ ወደ ድርድር እንደምትመጣ ሳይታለም የታወቀ ነገር ነበር። ዛሬ ይሄው ግብፅና ሱዳን ትተውት ወደነበረው የ2015 የሶስትዮሽ ድርድር እንመለሳለን እያሉ ነው።
1. ግብፆች ” ኢትዮጵያ በገንዘብ እጥረትም ሆነ በሌላ ምክንያቶች ግድቡን መስራት አትችልም ስለዚህ በማይሆን ነገር ላይ መደራደር አያስፈልግም!” የሚለው ለዘመናት የቆየው የግብፆች አቋም እንደ ጧት ጤዛ መርገፉን አውቀዋል።
2. “ግድቡ ቢሰራም እናፈርሰዋለን”   የሚለው የግብፅ አቋምም በራሷ ላይ ኒዩክሌር የማፈንዳት ያክል አደገኛ እንደሆነ ግብቷታል።
3. ግብፅና ሱዳን በምድርና በአየር ጦርነት ቢጀምሩ ጦርነቱ ሱዳን ላይ ተጀምር ሱዳንን ድምጥማጧን በማጥፋት እንደሚጠናቀቅ በደንብ ያውቁታል።
4. የኢትዮጵያ ህዝብ ዐባይን ሲገድብ ባዶ እጁን ሆኖ እንዳልሆነና ኢትዮጵያ አሰዋንን የሚንድ አቅም ገና ዱሮ እንዳላት ኢትዮጵያ ውስጥ የሚርመሰመሱት ሰላዮቿ ያረጋገጡት ሀቅ ነው።
5.ያለንበት ዘመን የግሎባላይዜሽን ነው አንዳቸው ከአንዳቸው ጋር የሚፈልጉት ጥቅም ስላለ መደራደር እንጂ ወደ ሀይል መሄድ የሚያመጣውን ሽንፈት ካለፈ ታሪኳ ግብፅ በደንብ አውቃለች።
በጥቅሉ ከአማራ ክልል ሰከላ ከምትባል ትንሸ የምድር ገነት  መንጭቶ ትልቁን ጣና ሰንጥቆ 10 አገሮችን አቋርጦ ሜዲትራኒያን ዉስጥ የሚቀረዉ የአባይ ወንዝ  ለኢትዮጵያ በፈጣሪ የተሰጣት ንብረቷ ነው። ኢትዮጵያ በንብረቷ የአለም አቀፍ ህግን ጠብቃ ያሻትን መድረግ እንደምትችልና የአባይ ግድብን የሚያቆም ምድራዊ ሀይል እንደሌለ ገብቷታል።
Filed in: Amharic