>

ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ከ57 ዓመታት በፊት ልክ በዛሬ እለት የአፍሪካ አንድነት ድርጅት [OAU] እንዲወለድ ያደረጉት ታሪካዊ ንግግር!  (አቻምየለህ ታምሩ)

ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ከ57 ዓመታት በፊት ልክ በዛሬ እለት የአፍሪካ አንድነት ድርጅት [OAU] እንዲወለድ ያደረጉት ታሪካዊ ንግግር!

 አቻምየለህ ታምሩ

ከታት የታተመው የግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ታሪካዊ ንግግር የአፍሪካ አንድነት ድርጅት እንዲመሰረት አዲስ አበባ  ላይ ተሰብስበው ለነበሩ ነጻ የአፍሪካ መንግሥታት መሪዎች ግንቦት 17 ቀን 1955 ዓ.ም. ያደረጉት ታሪካዊ ንግግር ነው። የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የተወለደው ግርማዊ ጃንሆይ ባደረጉት በዚህ ታሪካዊ  ንግግርና ረዳቶቻቸው ባደረጉት የረቀቀ ዲፕሎማሲ ጥረት ነው።
የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት ውልደት የንጉሠ ነገሥቱ የድካም ውጤት እንደሆነ ከኛ ከኢትዮጵያውያን በላይ የሚያውቁት አፍሪካውያን ግርማዊ ጃንሆይን «የአፍሪካ አባት» ሲሉ በክብር ይጠሯቸዋል። በአፍሪካ ኅብረት መታሰቢያ የቆመለት ዶክተር ክዋኔ ንክሩማህ ሳይቀር የአፍሪካ አንድነት ድርጅት በግርማዊ ንጉሠ ነገሥቱ ድካም  መመስረቱን ተከትሎ  በዚያው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት በተወለደበት የአፍሪካ አዳራሽ ባደረገው  ታሪካዊ ንግግር  የኢትዮጵያን አስተዋጽኦ በግጥም እንዲህ ሲል ገልጾታል፤
Ethiopia shall rise
 Ethiopia, Africa’s bright gem
 Set high among the verdant hills
 That gave birth to the unfailing
 Waters of the Nile
 Ethiopia shall rise
 Ethiopia, land of the wise;
 Ethiopia, bold cradle of Africa’s ancient rule
 And fertile school
 Of our African culture;
 Ethiopia, the wise
 Shall rise
 And remould with us the full figure
 Of Africa’s hopes
 And destiny.
ወገንተኛ ያልሆኑ አፍሪቃውያንም ታላቁን የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን «ኃይለ ሥላሴ የአፍሪቃ አባት» በማለት ያዜሙሏቸው ለአፍሪካ በዋሉት ውለታና ለአፍሪቃ አንድነት ድርጅት ባደረጉት ወደር የሌለው አስተዋጿቸው ነበር። ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን የአፍሪካ አባት አይደሉም ብሎ የተከራከረው «ከኢሳያስ አፈወርቂ ጋር አንድ ሰዓት ቁጭ ብሎ ማውራት ዩንቨርስቲ ገብቶ ተመርቆ ከመውጣት እኩል ነው፤  ከኢሳያስ አፈወርቂ ጋር መቀመጥና መነጋገር አንድ ቤተመፃሕፍት  ከመግባት ጋር እኩል ነው» ሲል የተናገረው  ነውረኛው መለስ ዜናዊ ብቻ ነበር።
ከአፍሪቃ አንድነት ድርጅት ውልደት ኀምሳ አመታት በኋላ የተመሰረተው የአፍሪካ ቨርቹዋል ዩኒቨርሲቲ፤ በቅኝ ግዛት ውስጥ ስለነበሩ አገሮች እርዳታ፤ አንድ አፍሪካ ከመመስረቱ በፊት በተለያዩ የአፍሪካ ክፍለ አሕጉራዊ አካባቢዎች ሊመሰረቱ ስለሚገባቸው ስለ AMU, CEN-SAD, COMESA, EAC, ECCAS, ECOWAS, IGAD and SADC ምክረ ኃሳብ ያቀረቡትም ግርማዊ ጃንሆይ ነበሩ።
ግርማዊ ጃንሆን በንግግራቸው መጨረሻውም አዲስ አበባ የተሰበሰቡት ነጻ የአፍሪካ መሪዎች በኢትዮጵያ የተዘጋጀውን የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ቻርተር እንዲፈርሙና ከታሪክና ትውልድ ተወቃሽነት እንዲተርፉ በእግዚያብሔር ስም ጠይቀዋቸዋል። መለስ ዜናዊ ክዋሜ ንክሩማህን የአፍሪካ አባት ያደረገው በዚህ መልክ ሞግተው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት እንዲቋቋም ያደረጉትን ታላቁን ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን ያዋረደ መስሎት ነበር።
ሆኖም ግን እውነት ይዘገያል እንጂ ተደብቆ አይቀርምና እነሆ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት እንዲመሰረትና በአዲስ አበባው ጉባኤ ድርጅቱን ሳይመሰረት የአፍሪካ መሪዎች ቢለብያዩ እያንዳንዳቸው የአፍሪካ መሪዎች በታሪክና በትውልድ ሲወቀሱ እንደሚኖሩ የሞገቱበት የጭካኔ ታላቅና ታናሽ ወንድማማቾቹ መንግሥቱ ኃይለ ማርያምና መለስ ዜናዊ ግን የደበቁበት የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሙሉ ታሪካዊ ንግግር እንዲህ ተቆፍሮ ሊወጣ ችሏል።   የአፍሪካ አንድነት  ድርጅት [OAU]  እንዲወለድ ግርማዊ ጃንሆይ  ያደረጉትን ሙሉ ንግግር ታደምጡ ዘንድ  ታሪካዊ ንግግሩን ከድምጽና ምስል ክምችት ላይበራሪያችን አውጥተን እነሆ ለጥፈነዋል።

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=3114246568597271&id=100000358765743

Filed in: Amharic